የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲከኛ ሃያሲን ሊደፍር ይገባል።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲከኛ ሃያሲን ሊደፍር ይገባል። "ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፦ ለወለደችውም ምሬት ነው" (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፳፭) እንዴናችሁ ማህበረ ቅንነት? ልዕልት ኢትዮጵያስ እንዴት አለሽልኝ? የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲኮኞቹ ሃያሲን ይፈራሉ፤ ያሳዳሉ፤ ያሳድማሉ፤ ሲቻላቸውም ያጠፋሉ። ይህ የጋራ ባህሪያቸው ነው። ለምን? ሁሉም የግራ ዘመም ርዕዮት ተጠማቂ ስለሆነ። አንድ ፖለቲከኛ ሲሞግት ይቆይ እና እሱ ሞጋች ሲገጥመው ያብዳል። ሁልጊዜ እሱ ከሰማዬ ሰማያት የወረደ ቅዱስ እና ብፁዑ አድርጎ ስለሚወስን። የሚገርመው ሃያሲ የሚሳደደው፤ የሚወገረው በደቦ ወይንም በወበራ ነው። ይህም ሬድሜድ ነው። በፖለቲካ ህይወት ውስጥ ሃያሲ ተፈርቶ ተስፋ ጥግ ያገኛል ተብሎ አይጠበቅም። ሃያሲያን ሲሳደዱ የመተንፈሻ ቧንቧ ሲፈልጉ አንድ ቀን በለስ ከቀናቸው አሳዳጃቸውን የሚጎዳ ተግባር ሊፈጽሙ ያችላሉ። ለትውልድ፤ ለአገር የሚታሰብ ቢሆን ደፍረው ወጥተው ሳይከፈላቸው የሚሰማቸውን ግልጽ እና ቀጥተኛ ሆነው ሳያሽሞነሙኑ የሚያሄሱ ወገኖች ሊከበሩ ይገባል ባይ ነኝ። መዳኛው መንገድ ያ ብቻ ስለሆነ። ኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ ለግራ ፖለቲካ የተመቸ አይደለም። "ዕውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር "የሚለው ብህሊ እንቅጭ እንቅጩን ተነጋግረን ዕውነትን እናፍልቅ ነው። ሌላም አለ እከሌ አቶ ሀ የግንባር ሥጋ ነው ይባላል። ያ ማለት ዕውነት ይደፍራል፤ ለዓላማው ሟች ነው ማለት ነው። #አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ …… ሀ) ደጋፊ አለ። ለ) ተጠማኝ አለ። ሐ) ተደማሪ አለ። መ) ተዋህጂ አለ። ሠ) ተቀናቃኝ አለ። ረ) ተፎካካሪ አለ። ሰ) ተቃዋሚ አለ። #የተሳትፎ ደረጃ 1) ቀጥተኛ ተሳታፊ። 2) ተዘዋሪ ተሳታፊ። 3) ተመልካች። 4) ተቀ...