ልጥፎች

ከዲሴምበር 12, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የጠራ የትግል መስመር የድል መባቻ ነው!

ምስል
የአማራን ተጋድሎ መደገፍ ሰውን ማዕከል ማድረግን ብቻ ይጠይቃል። የአማራን ተጋድሎ ማጣጣል  ሰብዕዊነትን መርገጥ ይሆናል  - ለእኔ ። „ራህብን የሚያውቀው  የተራበው ብቻ ነው„ - አሁንም - ለእኔ። „በምድር ላይ የሰው ህይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?“ መጽሐፈ እዮብ ፯ ቁጥር ፩ v   ይድረስ ለተከበሩ ፕሮፌስር ዓለምአንተ ገ/ሥላሴ እና v  እንዲሁም ለዶር. ደመቀ ገሰሰ። ከሥርጉተ© ሥላሴ   09.11.2016 (ሲዊዘርላንድ -  ዙሪክ) ·        መ ቅድም። ውዶቼ ይህም ጹሁፍ በዘመነ አማራ ተጋድሎ 09.11.2016 ላይ የተጸፋ ነው። ሦስት እርዕሰ ጉዳይን በአንድ ጥምረት የሠራሁት ነበር። አማራ መከራህን ዋጥ አድርገህ በሰጠንህ ልክ ታገል በተባለበት ዘመን፤ ተጋድሎው ፊት በተነሳበት ወቅት የተጣፈ ነው። የጎንደር ህብረት እና የጎጃም ህብረት ግንባር ቀደምቶቹ ነበሩ። እነሱን ሞግቼ የጻፍኩት ነው። እንዲያውም የወሎ፤ የሽዋ፤ የባሌ፤ የአርሲ እያለ እንደሚቀጥል በልበ ሙሉነት ይናገሩ ነበር፤ ለዛም ተግተዋል፤ ብቻ  የውርንጫ ድካም ሆኖ ቀረላቸው እንጂ። ጹሑፉ የተጋድሎው ሁነኛ ደጋፊዎቹ ጥቂት በነበሩበት ወቅት የተሠራ ነው። ቀንበጥ ታሪኩን በታሪኩ ከርስ ውስጥ ባለርስት ማድረግ ስላለባት እንሆ ሳተናው/ ኢትዮ ሪጅሰተር በዛን ጊዜ ፖስት ያደረገውን ለውጥ ስለሚባለው መሰረታዊ ትንፋሽ አማራ ስለፈከፈለው መስዋዕትነት እና ስለነበረበት ወጀብ ታሪኩ ስለሆነ በድጋሚ ቀርቧል። ያላነበባችሁት እንድታነቡት፤ ያነባባችሁት ደግሞ ያን ጊዜ እኔ የጻፍኩት የጭብጥ መሰረ...

ሃቅን አትፍሩ!

ምስል
ቁሞ ዬሚጠብቅ ( stagnant) ዬሆነ ዬአመክንዮ ድንጋጌ - ዓለም አስተናግዳ አታውቅም! „በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡  ናስ፡ ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽ ው ፡ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ፥  ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡  ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡  ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡  ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም። " (ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት  ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫) ከሥርጉተ©ሥላሴ (Sergute©Selassie) 23.12.2016 (ዙሪክ - ሲዊዘርላንድ)                                                      ቆዬት ያለ የሥርጉትሻ ፎቶ።   ·        ጠበታ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ሰሞናቱን በምልሰት የተሠሩ ነገሮችን በቀንበጥ ብሎጌ መቀመጥ አለባቸው ብዬ ያሰብኳቸውን በምልሰት ቅኝት እያደረግን ነው። ዘመነ 2018ን ሸኛኝቶ ዘመነ 2019ኝን ለማቀብል የ አውሮፓዎቹ ቃናት ሌት ተቀን እዬተጉ ነው። ኢትዮጵያ ላይ ነሐሴ እና ጳጉሚት ላይ እንዳለው ነው አሁን አዬሩ። ገብያው ደርቷል። ፓስታ ቤቱም ...