ልጥፎች

ከጁን 24, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#የኩርፊያ #ፖሊሲ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።

  #የኩርፊያ #ፖሊሲ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።   "ለተከፋ ማጭድ አታውሰው።"    "ከፍትፍቱ ፊቱ።" "እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው።" የጤና ባለሙያወች ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጋር የነበራቸው መቅድመ ግንኙነት እነኝህ ይተባህሎች ይገልጡልኛል።    "ጥበብን ከወደድሃት ትዕዛዙን ጠብቅ እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጥሃል።" (መጽሐፍ ሲራክ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፳፭)     ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ከማህበረ ቅንነት የጤና ባለሙያወች ጋር የሚያደርጉትን ውይይት በጥንቃቄ ስጠብቀው ነበር። ሕይወት፤ እስትንፋስ፤ ነፍስ፤ ሩህ፤ ሥጋ፤ ሰው፤ መኖር፤ ተስፋ ከእግዚአብሄር በታች ከሙያው ጋር በእጅጉ የተዋህዱ ስለሆነ በብርቱ ጥንቃቄ እና ማስተዋል ከጤና ጋር የተያያዙ ክስተቶች ሊያዙ ይገባል ባይም ነኝ።   በኢትዮጵያ የጤና ባለሙያወች ታሪክ ውስጥ " #እራበን ፤ ባለቤቴን #በሽሮ አረስኩ፤" ወዘተ የሚሉ የሁላችንም የህሊና ጓዳ የፈተኑ ክስተታዊ ሁነቶችን መከታተል የተገባ ስለነበር ተከታትየዋለሁኝ። በዚህ ዙሪያ በሌላ መድረክ "እኔም የደሞዝ ጥያቄ አለኝ" የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሳስታውሳት #ውሽክ የምታደርግ ተረባዊ አገላለጽም ስትገርመኝ ሰነባብታለች።   እሳቸውም፤ ባለቤታቸው ቀዳሚ እመቤቱትም፤ እንዲሁም የካቢኔ አባሎቻቸውም #የሞድ ዲዛይነር ሲሳይ ሆነው እንደባጁ ልባቸው ያውቀዋል። ቤተመንግሥታቸው ፕሮቶኮሉ የአመጋገብ ሥርዓቱ ቡፌ ነው። የሰርክ ቡፌ። በሌላ በኩል ክብራቸው ተጠብቆ፤ በፈለጉት ጊዜ ለአጫጭር አገራዊ ጉዞ ኤሊኮፍተር፤ ረጅም ጉዞውን በአውሮፕላን ዓለምን እያዳረሱ የሚገኙት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ፤ የኖቤል ተሸላሚ፥ እኔም የደሞዝ ...