ልጥፎች

ከኦክቶበር 11, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

• #ትህትናዊ ዓለም ለመፍጠር የተጉ የዘመናችን ጀግና! #ጀግንነትን #በጀግንነት #ቀደሱት ፓለቲከኛዋ ክብርት ማሪያ ኩሪያ ማቻዶ! ብሩክ! # ዓለማችን ከኖቤል የሽልማት ተቋም ጋር የሚለካካ፤ ሚዛን አስጠባቂ፤ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ #አዲስ የሽልማት ተቋም ልትፈጥር ይገባል።

ምስል
  • #ትህትናዊ ዓለም ለመፍጠር የተጉ የዘመናችን ጀግና! #ጀግንነትን #በጀግንነት #ቀደሱት ፓለቲከኛዋ ክብርት ማሪያ ኩሪያ ማቻዶ! ብሩክ! # ዓለማችን ከኖቤል የሽልማት ተቋም ጋር የሚለካካ፤ ሚዛን አስጠባቂ፤ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ #አዲስ የሽልማት ተቋም ልትፈጥር ይገባል።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፯     #መቅድም ።   ህውከትም፤ ጩኽትም፤ ዕልቂትም፤ ውድመትም ባባከናት ዓለማችን እረፍት የሚሰጥ #ትህትናዊ ጉዞ እያዬሁ ነው። የትራንፒዝም ብርቱ ደጋፊ የነበሩ የአንድ ወጣት አሜሪካዊ ሰማዕት ህልፈትን አስመልክቶ ክብርት ባለቤታቸው፤ በመግደል ወንጀል ለተጠረጠረው ወገናቸው #የምህረት ቃል ያሰሙት በቅርቡ ነበር። ዛሬ ደግሞ ሌላ ትሁት፤ ፍጹም ቅን የሆነ ውስኔ ከቬንዞላዊቷ የፖለቲካ መሪ ክብርት ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ተደመጠ።    ክብርቷ ከዘንድሮ የኖቤል ተሸላሚ ለመሆን ከታጩት ውስጥ አንዷ ነበሩ። አሸነፋ። ማሸነፋቸውን፤ ከደስታ በላይ ሐሤታቸውን፤ ግርማቸውን፤ ሞገሳቸውን፤ ተቀባይነታቸውን ለቬንዞላ ህዝብ እና ለተከበሩ ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕ እንዲሆን ወሰኑ፤ ፈቀዱ። መሪነት ይሄ ነው። ከራስ ጥቅም፤ ከራስ ክብር የሚበልጠውን መዝኖ ጸጋውን ለሚበልጥ ሰብዕና ወይንም ዓላማ፤ ወይንም ግብ ፈቅዶ መስጠት። ታምራት እና ታላቅ ግሎባል የምሥራችም ነው ለቤተ ሰላም ቤተኞች።   #በምልሰት ስሜቴን ሳጋራ።   ወደ ኋላ ተመልሼ የአርጀንቲናዋን ቀዳማዊት እመቤትን ኢፋ / ኢቢታ ፔሩን አሰብኩኝ። በሳቸው ሁልጊዜ እንደተመሰጥኩ ነው። ከጋብቻ ውጪ በመወለዳቸው ነውር በነበረበት በዛን ወቅት ከአንድ ዝቅተኛ ቤተሰብ ነበር የተወለዱት። እናታቸው ተሳቀው ነበር ያሳደጓቸ...