• #ትህትናዊ ዓለም ለመፍጠር የተጉ የዘመናችን ጀግና! #ጀግንነትን #በጀግንነት #ቀደሱት ፓለቲከኛዋ ክብርት ማሪያ ኩሪያ ማቻዶ! ብሩክ! # ዓለማችን ከኖቤል የሽልማት ተቋም ጋር የሚለካካ፤ ሚዛን አስጠባቂ፤ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ #አዲስ የሽልማት ተቋም ልትፈጥር ይገባል።

 

#ትህትናዊ ዓለም ለመፍጠር የተጉ የዘመናችን ጀግና!
#ጀግንነትን #በጀግንነት #ቀደሱት ፓለቲከኛዋ ክብርት ማሪያ ኩሪያ ማቻዶ! ብሩክ!
# ዓለማችን ከኖቤል የሽልማት ተቋም ጋር የሚለካካ፤ ሚዛን አስጠባቂ፤ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ #አዲስ የሽልማት ተቋም ልትፈጥር ይገባል።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
 
ህውከትም፤ ጩኽትም፤ ዕልቂትም፤ ውድመትም ባባከናት ዓለማችን እረፍት የሚሰጥ #ትህትናዊ ጉዞ እያዬሁ ነው። የትራንፒዝም ብርቱ ደጋፊ የነበሩ የአንድ ወጣት አሜሪካዊ ሰማዕት ህልፈትን አስመልክቶ ክብርት ባለቤታቸው፤ በመግደል ወንጀል ለተጠረጠረው ወገናቸው #የምህረት ቃል ያሰሙት በቅርቡ ነበር። ዛሬ ደግሞ ሌላ ትሁት፤ ፍጹም ቅን የሆነ ውስኔ ከቬንዞላዊቷ የፖለቲካ መሪ ክብርት ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ተደመጠ። 
 
ክብርቷ ከዘንድሮ የኖቤል ተሸላሚ ለመሆን ከታጩት ውስጥ አንዷ ነበሩ። አሸነፋ። ማሸነፋቸውን፤ ከደስታ በላይ ሐሤታቸውን፤ ግርማቸውን፤ ሞገሳቸውን፤ ተቀባይነታቸውን ለቬንዞላ ህዝብ እና ለተከበሩ ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕ እንዲሆን ወሰኑ፤ ፈቀዱ። መሪነት ይሄ ነው። ከራስ ጥቅም፤ ከራስ ክብር የሚበልጠውን መዝኖ ጸጋውን ለሚበልጥ ሰብዕና ወይንም ዓላማ፤ ወይንም ግብ ፈቅዶ መስጠት። ታምራት እና ታላቅ ግሎባል የምሥራችም ነው ለቤተ ሰላም ቤተኞች።
 
#በምልሰት ስሜቴን ሳጋራ።
 
ወደ ኋላ ተመልሼ የአርጀንቲናዋን ቀዳማዊት እመቤትን ኢፋ / ኢቢታ ፔሩን አሰብኩኝ። በሳቸው ሁልጊዜ እንደተመሰጥኩ ነው። ከጋብቻ ውጪ በመወለዳቸው ነውር በነበረበት በዛን ወቅት ከአንድ ዝቅተኛ ቤተሰብ ነበር የተወለዱት። እናታቸው ተሳቀው ነበር ያሳደጓቸው። የዘመኑን ሽሙጥ ሁሉ ችለው። መገለልንም አስታግሰው። ክብርት ኢቢታ / ህይዋን አስተዳደጋቸው መከራ የበዛበት የጎዳና ህይወትንም ያስተናገደ ነበር። ለሴቶች እጅግ ፈታኝ የሚባለውን የፆታ የሥራ መስክንም ቀምሰውታል።
 
……… ከዛ የቲያትር ክበብ አባልነትን አገኙ። ቀጥሎም የራዲዮ ጋዜጠኝነት ተፈቀደ በፈጣሪ እርዳታ። አልፎም የሠራተኛ ማህበር መሪነት ታከለላቸው። የደመቀው እና የከበረውን የሰብዓዊ መብት ሞጋችነትንም ተቀዳጁ። በማስከተልም ሙዚቃ እና የዳንስ ኤክስፐርትነትን በጥበብ ተቀመሩ። በኋላም የአርጀንቲና ፕሬዚዳንት ፔሩን የትዳር አጋርነት ተመረቀላቸው። 
 
ይህም ብቻ አይደለም፤ እንደ አለት የጸና የሴቶች እኩልነትን ማህበራዊ መሠረት በማስያዝ #በህግ ተደግፎ ከደም ጋር እንዲዋህድ ማስደረግ ቻሉ። አርመን ላይ የሴቶች እኩልነት በህግ ድጋፍ ያገኜ ነው። በሌሎች አገሮችም እኩልነቱ ሊኖር ይችላል። የኢቢታ ማኒፌስቶ ግን በወረቀት ላይ ሳይሆን ድንጋጌወቹ በአዕምሮ የተቀረጹ ናቸው። በማህበረሰቡ ህሊና ሴት ሙሉ አቅም ያላት የተፈጥሮ ጸጋ ናት የሚለው አስተምህሮ ማህተሙ ተፈጥሯዊ እንዲሆን ነው ያስደረጉት። በአርጀንቲና የሴት የበታችነት ከሥሩ ነው የተነቀለው። ሪቮልሽን ነበር ያካሄዱት ለዛውም በሙሉ የህዝብ ድምጽ ተደግፎ። 
 
ክብርት ኢፋ/ ኢቢታ በእኛ ህይዋን ፔሩን በመጨረሻም ለአገር መሪነት ውድድር እጩ ሆነው ቀረቡ። ……… ግን ሞት ቀደማቸው። ያን ቀን በመላ አርጀንቲና አበባ ሱቅ ውስጥ የሚሸጥ አበባ #አልነበረም ይላል ገድለ ታሪካቸው። በጀርመን፤ በእንግሊዝ፤ በፈረንሳይ በጥበቡ ዘርፍ ላበረከቱት ልቅና ቋሚ መታሰቢያ አላቸው። ዝርዝሩን ጉግል ቢጠየቅ ስለሚሰጣችሁ አንብቡት።
 
#ድንቅ ሴቶች በየዘመኑ ለሚሰጠን አምላኬ ይክበር ይመስገንልኝ። አሜን።
 
ዛሬም ዓለማችን ድንቅ ሴቶችን አላጣችም። የቀድሞ የጀርመን ካንስለር ክብርት ዶር አንጌላ ሜርኪል፤ የሶርያውያን ብቻ ሳይሆኑ፤ የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ አባሽ፤ አጽናኝ፤ አይዟችሁ ባይ ቅን እና ዕንባን አድማጭ ናቸው። እንዲሁም የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት ክብርት ወ/ሮ ሚሺያል ኦባማ ለሴቶች የዕንባ ጥያቄ እጅግ #ቅርብ ነበሩ። 
 
በዕንባ ዘመናችን፤ በተከፋንባቸው ወቅቶች አብረውን ነበሩ። እኔ እንዲያውም፤ በተደጋጋሚም ቀጣዩ የተመድ ቁንጮ ክብርት ዶር አንጊላ ሜርክል እንዲሆኑ እመኛለሁኝ። የተፈተኑ፤ ነጥረው የወጡ ከወርቅም በላይ ዕንቁ ናቸውና። ሰባዕዊም ናቸው። ጥንካሪያቸው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነው። 
 
ዛሬ ያሉት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊቃናት ከሚኒስተርነት ጀምር፤ በተለያዬ ቁልፍ ኃላፊነት የሚገኙት የብልጽግና ተሿሚ ሴቶች ዕድሉን በችሮታ አላገኙበት። ያለመሰልቸት በተከታታይ እና በትጋት ተሰርቶበታል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከገበርዲን እና ከከረባት አምልኮ እንዲወጣ። ስለሆነም የብልጽግና ሴት ባለሥልጣናት #ዕድሉንም ሳያፈሱ ለኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ እና መከፋት ቅርብ ቢሆኑ ጥሩ ነው። ይህ ክብር የተገኜው ድምጽ አልባወቹ የኢትዮጵያ ሴቶች ዕንባ #ኢንቬስት ተደርጎበት ነውና። 
 
ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ ውስጤን አድሬስ ያደረገ ትሁት፤ ፍጹም ቅን ፖለቲከኛዋ ክብርት ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ክብራቸውን "ለእኔ አይገባም፦ ለህዝቤ እና ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ለክቡር ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕ ይሁንልኝ" ሲሉ የሰጡት አስደማሚ፤ ፍጹም ንጹህ ቃል ለግሎባሉ ዓለም አዲስ የትምህርት #ካሪክለም ነው። 
 
የተከበሩ ፕሬዚዳንት ትራንፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ብዙም ግሎባሉ ዓለም ትኩረት ያልሰጠው " #ሽብርተኝነት " አውሮፓን እንደዛ ሲንጠው በተለይ ፈረንሳይ፤ እና የአውሮፓ ህብረትን መቀመጫ ብራስልስን ሲያለፋው ያስታገሱት፤ ረብ ያስደረጉት እሳቸው የተከበሩ ፕሬዚዳንት ትራንፕ ነበሩ። 
 
ይህን የዓለማችን ፖለቲካ እንኳንስ ሊያመሳጥረው፤ ሊተረጉመው እንኳን አልተቻለውም ነበር። "እኔ ሥልጣን ላይ ብኖር የዩክሬን እና የራሺያ ጦርነት አይነሳም ነበር" ያሉትን ሚስተር ፕሬዚዳንት ከልቤ ነው እምቀበለው። የቀድሞዋ የጀርመን ካንስለር ክብርት ወ/ሮ አንጌላ ሜርክል (ዶክተር) እሳቸው ሥልጣን ላይ ቢኖሩም ራሺያ እና ዩክሬን እንዲህ ካለ እልቂት ውስጥ አይገቡ ይሆናል የሚል የግል ዕይታም አለኝ። ቅብዓ ደጀን ስለሚሆን። የእያንዳንዱ ቅብዓ ጸጋው ወጥ #ላይሆን ይችላል። በተመሳሳይ ደረጃ ተሁኖ ስኬት እና ዕሳቤው በአንፃራዊነት ስለሚለያይ። መሰጠት እንደ ጸጋው ይተረጎማልና። 
 
የተከበሩ ፕሬዚዳንት ትራንፕ ሞትን አሸንፈው፤ ምርጫውንም አሸንፈው ወደ ሁለተኛ የሥራ ዘመናቸው ከመጡ በኋላ፤ በውድድራቸው ጊዜም "#ሰላም " የፊደል ገበታቸው ነበር። ባለቤታቸው ቀዳማይ እመቤት ወሮ ሜላኒያም ትራንፕም በመጽሐፋቸው ዙሪያ በነበራቸው ቃለ ምልልስ በአጽህኖቴ የገለጹት "ሰላም" ነበር። በሰላም ላይ ሊሠራ ይገባል ተደሟዊ ቃላቸው ነበር።
 
አገረ አሜሪካ ለግሎባሉ ዓለም ቀንዲልም ቀንድም አገር ነው። " #ሰላም " አጀንዳው የሆነ መሪ ሲገኝ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሪ አስቀያሪ ቅዱስ መንፈስ ያመነጫል። በቅዱስ መንፈስ ውስጥ ቅዱስ እግዚአብሄር፤ ቅዱሳን መላዕክት፤ ቅዱሳን ሐዋርያት፤ ነብያት፤ ሰማዕታት እና ፃድቃን በምግባራቸው የከበሩ ይገኛሉ። መመረቅ፤ መባረክም የሚቀዳው ከዚህ መሰል ንጹህ ፃዓዳ መንፈስ ነው።
 
እኔ የዩክሬን እና የራሺያ ትውልድ እጅግ ያሳዝነኛል። የአውሮፓውያን ትውልድ ጦርነት ሳይሆን አብሮነትን ቢወርስ ፈቃዴ ነው። የራሺያ የጥበብ ወጣቶች #በኢሮቪዥን ሶንግ ኮንቴስት ዓመታዊ ውድድር አይሳተፋም። ታግደዋል። ራሺያውያን እስፖርተኞች በአውሮፓ እና በዓለም ዓቀፍ ማናቸውም የስፖርት ውድድር አይሳተፋም። ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። የእኔ ቅን ታዳሚወች #የተቋረጠ ነገር አይታያችሁምን? የፖለቲካ ሊቃናት ሳይስማሙ ሲቀሩ በርደኑ የሚያርፈው ከትውልድ ላይ ነው።
 
ቀላል ነገር ነበር። ራሺያ ሰግቻለሁ ሲል፤ ዩክሬን ስጋቱን ቢያደምጥ ይህ ሁሉ ድቀት ይቀር ነበር። ቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ እኮ የአውሮፓ ህብረት፤ የኔቶም አባል አገር አይደለችም። ዩክሬን በስፋት እና በጥልቀት መክሮ ቢሆን ኖሮ፤ በጦርነት ምክንያት የትውልድ መለያዬት፤ የሥልጣኔ መስተጓጎል እና ውድመትም አይመጣም ነበር። መደማመጥ በመከባባር ቢኖር ኖሮ። ቸገረኝ፤ ሰጋሁ ያለን ማድመጥ ምኑ ይከብዳል? 
 
በሌላ በኩልም ለወደፊቱ ዓለማችንም በድፍረት ክፋ ሃሳብ የሚያራምዱትን ሳይቀር ሳታርቅ፤ ሳታገል #አቅርባ ብታወያይ፤ ታግሳ በሆደ ሰፊነት ብታነጋግር ብዙ ታተርፋለች። ቻይና በብዙ ሁኔታ ይህን መንገድ ብትመርጥ መልካም ይመስለኛል። መፈቃቀድን ማስቀደም። ጤናማ ፋክክርን ማፋፋት። ዕድልን በቅንነት ማየትን፤ ዘለግ ያለ አድማጭነትን ባህል ማድረግ ትውልድን ያተርፋል። 
 
እኔ አገረ - ራሺያ ከገጠመው ግሎባል መገለል ያወጣው፤ በክብር ላይ ያስቀመጠውን የፕሬዚዳንት ትራንፕን ያን የመሰለ ታምር የሚመስል ልዩ የአቀባበል፤ የማድመጥ ክህሎት እና ስጦታ ቸል ብሎ በራሱ መንገድ መጓዝ መፍቃደ የእግዚአብሄርን ታምር እንደመጠቅጠቅ እቆጥረዋለሁኝ። ሰላም ነው የሚያተርፈው። ቀን ሲጎድል መሰበር አለና።
 
አገረ ራሺያ ዕድሉን ስላፈሰሰ በዚህ ሂደት የአውሮፓ ህብረት አትራፊ ነው። አገረ ራሺያ ከስሯል ብየ አስባለሁኝ። ጥበብም፤ ብልህነትም የራሺያ የፖለቲካ ሊቃናት አንሷቸዋል ባይም ነኝ። ያን በመሰለ #የአላስካ ዲያመንድን ዕድል አፈሰሱት - ራሺያኖች። የብዙ የዓለም ጭምት ህዝብን (silent majority) የሰላም ድንቅ ተስፋንም አጠወለጉት። በመሸነፍ ውስጥ #ማሸነፍ እንደሚገኝም አልተረዱትም ራሺያኖች። "የሚመካ ቢኖር በእግዚአብሄር ይመካ።"
 
ራሺያ እና ዩክሬንን ለማስማማት የተከበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ደፋሩ ዶናል ትራንፕ የከፈሉትን መስዋዕትነት ራሺያኖች ቢደፋትም፤ ፕሬዚዳንቱ ጥረታቸውን ቀጥለው ለዘመናት የዓለም የስጋት ቁንጮ የሆነውን በእስራኤል እና በጋዛ የመንፈስም፤ የአካልም ጦርነት የትራንፕ ባለ 20 ነጥብ #ማኒፌስቶ የመጀመሪያ ምዕራፋ ስምምነት በመልካምነት ተቋጬ። ጠቅላላ ሂደቱ ሆሊውድ ስንት እስክሪፕት ሊሠራበት እንደሚችል ሳስበው ነበር ያደርኩት።
 
ሁለት ጊዜ ሞትን ያሸነፋት ጀግና ፕሬዚዳንት ትራንፕ፤ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከሞት የተረፋበት ጉልህ #ሚስጢር ለእኔ ለሰላም የተሰጠ ሰማያዊ ታምራት ነው ብየ ማሰብ እወዳለሁኝ። "ደፋር እና ጭስ መውጫ አያጣም" ዕውን ሆነ። ዛሬ በጋዛም፤ በእስራኤልም አፈሙዝ፤ ባሩድ፤ ሮኬት፤ ስጋት፤ ፍርሃት፤ የአደጋ ጊዜ ደወል፤ መፈናቀል ቀጥ! ሰጥ! ብሏል። ተመስገን። ለሰላም ወዳዱ ግሎባሉ ዓለም በዕል ዓውደዓመት ነው ብየ አስባለሁኝ። የየሰከንዱ የሰው ልጅ የጭንቅ ድምጽ ስንቱ ታለፈ???? ተመስገን #ትራንፒዝም
 
ይህ ሲገርመኝ፤ ይህ ሲደንቀኝ፤ ይህ ሲመስጠኝ አድሮ እና ውሎ ዛሬ የሰማሁት ታላቅ የምስራች የኖቤል ኮሜቴ የገፋውን ታላቅ ቅን የሰላም #ሰንደቅ የቬንዞላ ብቻ ሳይሆን የዓለም ክብርት በሆኑት ማርያ ኮሪና ማቻዱ ጀግንነትን በትህትና ዕውነትን ቀደሱት። "የኖቬል ሽልማቴ ለቬንዞላ ህዝብ እና ለተከበሩ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕ ይሁንልኝ አሉ። "እኔ ታናሽ ነኝ። እሳቸው ይበልጡኛል።" እንደማለት ነው። ዓለማችን የሚያስፈልጋት ቅንነት - ቸርነት - ቀናነት - ይኽው ነው። ይሄ ሂደት በራሱ የክፋትን - የተንኮልን - የሸርን - የምቀኝነትን- የሴራ እና የኢንትሪግን ቅናታዊ እጭ ወደ መቃብር ይልካል። " አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"
 
#ሂደቱ ………
 
1) የዓለም ፖለቲከኞች ከውስጥ የመደማመጥ አስፈላጊነትን በአዲስ መልክ ይቀርፃል። ። የፖለቲከኞች ቅንነት በመፈቃቀድ እንዲሆን አናባቢ እርምጃ ነውና። ለኖቤል ኮሚቲውም አዲስ እሸት ትምህርት ቤት ተከፍቶለታል።
2) የሰላም ክብር እና ልዕልና በልቅና በህብራዊነት ያቀልመዋል።
3) እናትነት ሰማዕትነት ስለመሆኑም በቅኔ ያመሳጥራል።
4) የትውልድ ተስፋ በሳቅ እና በራስ መተማመን ያበራል።
5) የተመድ ዓላማ እና ተግባር በሰወች ህሊና ውስጥ እንደምን መፈጸም እንደሚያስችል ቁሞ ያስተምራል። የአንድ ቅን ሰብ ተቋምነቱን ያሳያል። አዲስ የሰላም ትሁት ምዕራፍ፤ የአዲስ ዘመን በር ፏ አድርጎ ከፍቷልና።
6) ዕድሉን በሳቢያ ሲያፈስ ለኖረ የሰው ልጅ አዲስ የተግባር የተራራ ስብከትም ነው። ዕድልን ማክበር ስኬትም ነውና።
7) መልካምነት የራስን ኢጎ አሸንፎ መነሳት ስለመሆኑ ሐዋርያ ሆኖ ያስተምራል።
 
በዚህ ውስጥ ፈጣሪ አምላካችን፤ እኛን የሰጠን እግዚአብሄር ሐሤት ያደርጋል። ዓለማችን ሁለት የትምህርት ካሪክለም ተነድፎላታል። እነሱም።
 
1) የትራንፕ ባለ 20 ነጥብ የሰላም ግሎባል #ማኒፌስቶ። ትራንፒዝም።
2) የማሪያ የግል ኢጎን የቀበረ የትህትና አስተምህሮ ማኒፌስቶ። ማሪያይዝም።
 
#ክወና።
 
ሌሊት ሳስብ ያደርኩት ዓለማችን በአዲስ ተፈጥሯዊ፤ ሰዋዊ፤ ዕውነትን ያላገለለ፤ በንፁህ መንፈስ የተቀረጸ ሚዛን አስጠባቂ የኖቤል የሽልማት ተቋም ልትፈጥር ይገባታል ብየ ሁሉ አሰብኩኝ። ከፖለቲካ ነፃ የሆነ የኖቤል የሽልማት ተቋም ያስፈልጋታል - ፕላኔታችን። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን። ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
የእኔ ቅኖች ቅንነትን እያዬን ነው። ተመስገን። ትህትናንም እያስተዋልን ነው። ተመስገን። ሰላም ቀን ሲወጣለትም ለማየት ታደልን። ተመስገን። እኛም እራሳችን ለመለወጥ እንሰናዳ። መማር በመለወጥ ይስከን። አሜን። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergure©Selassie
11/10/2025
 
መኖራችን ካንፓሳችን፤ ህይወታችን ኮንፓሳችን።
 
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የትጉኃኑ የBBC ዜና እንሆ።
«ቬኔዙዌላዊቷ ፖለቲከኛ ማሪያ ኩሪና ማቻዶ የትራምፕን ተስፋ በማጨናገፍ የኖቤል ተሸላሚ ሆኑ»
«ቬኔዙዌላዊቷ ፖለቲከኛ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ»
10 ጥቅምት 2025
«ቬኔዙዌላዊቷ የተቃውሞ ፖለቲካ መሪ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የ2025 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ። የቬንዝዌላ ተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ የሆኑት ማሪያ ኮሪና ማቻዶ በአገራቸው ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማቀንቀናቸው እና አገራቸው ወደ ዲሞክራሲ ሽግግር እንድታደረግ በመታገላቸው የዚህ ዓመት የኖቤል ሽልማትን ማሸነፋቸውን ኮሚቴው አስታውቋል።
የተቃውሞ ፖለቲካ መሪዋ ማቻዶ፣ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ ሽልማቱ እንደሚገባቸው ቢናገሩም፣ በአገራቸው ያለውን አምባገነን መንግሥት በመታገላቸው ለሽልማት መብቃታቸው ተገልጿል።
የኖቤል ኮሚቴ ሰብሳቢው ፖለቲከኛዋ ማሸነፋቸውን ሲገልጹ፣ በ2025 የኖቤል የሰላም ሽልማት "እየጨመረ በመጣው ጨለማ ውስጥ የዴሞክራሲን ነበልባል ለምታስቀጥል ሴት" መሰጠቱን ተናግረዋል።
"አምባገነኖች ሥልጣን ሲይዙ ተነስተው የሚገዳደሩ ልበ ሙሉ የነጻነት ጠበቃዎችን ዕውቅና መስጠት ይገባል" ሲሉም አክለዋል።
ኮሚቴው ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በላቲን አሜሪካ ካሉት እጅግ "የተለዩ ተምሳሌቶች" አንዷ በመሆን የኖቤል የሰላም ሽልማትን መሸለናቸውን ገልጿል።
የኮሚቴው ሰብሳቢ በንግግራቸው ላይ ማቻዶ "ዋና የአንድነት ምሳሌ ሆና ቆይታለች" ብለዋል። "በዲሞክራሲ ማዕከላዊነት ላይ የተቀመጠው ይህ ነው። ባንስማማም እንኳን በሕዝብ የበላይነት መመራት አለበት የሚለውን መርሆዎ ለመከላከል ያለን ፍላጎት ነው።ዴሞክራሲ አደጋ ላይ በወደቀበት በዚህ ወቅት ይህንን የጋራ አቋም መከላከል ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው።"
የ58 ዓመቷ ኢንጂነር፣ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የአገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንዳይሳተፉ በፍርድ ቤት ታግደዋል።
ምርጫው በዓለም አቀፍ ደረጃ ነፃም ሆነ ፍትሃዊም አይደለም በሚል ውድቅ ተደርጓል። ምንም እንኳ በምርጫው እንደሚያሸንፉ ትንበያዎች ቢያሳዩም እንዳይሳተፉ በመደረጉ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ለሦስተኛ ጊዜ አሸናፊ ሆነው በሥልጣን ላይ ቀጥለዋል።
ከምርጫ ውጤት በኋላ በመላ አገሪቱ የተቃውሞ ሠልፎች የተካሄዱ ቢሆንም መንግሥት ግን ሙሉ በሙሉ መቆጣጣር እና ዝም ማሰኘት ችሏል።
በማዱሮ በዓለ ሲመት ዕለት በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ለጥቂት ጊዜ የታዩት ማቻዶ፣ ከዚያ በኋላ ግን እስከዛሬ ድረስ ተደብቀው ይገኛሉ።
ለአጭር ጊዜ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የተቃውሞ ፖለቲካ መሪዋ ወዲያው ተለቅቀዋል።
ማቻዶ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፋቸውን በተደበቁበት ሆነው ሲሰሙ " በጣም ደንግጫለሁ. . . በደስታ ብዛት ደንግጫለሁ" ብለዋል።
የዋይት ሐውስ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ስቴቨን ቼኡንግ ትራምፕ "የሰላም ስምምነቶችን ማድረግ፣ ጦርነቶችን ማስቆም እና ሕይወቶችን ማዳናቸውን ይቀጥላሉ" ብለዋል። ቼኡንግ "ለሰብዓዊነት ልብ አላቸው፣ እንዲሁም እንደርሱ ያለ በፈቃዱ ተራራን ማንቀሳቀስ የሚችል ማንም የለም፥ የኖቤል ኮሚቴ ከሰለም ይልቅ ፖለቲካን እንደሚያስቀድም አረጋግጧል" ሲሉ ጽፈዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ሥልጣናቸውን ከተረከቡ ጊዜ ጀምሮ ለኖቤል የሰላም ሽልማት በበርካታ አገራት መሪዎች ዕጩ ተደርገው ተመርጠዋል። ይሁን እንጂ ተሸላሚ ዕጩዎችን ማቅረቢያ ጊዜው የሚያበቃው ጥር 31 በመሆኑ በዚህ ዓመት ምርጫ ላይ ሊካተቱ አይችሉም ማለት ነው።
የኖቤል ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ማቻዶ ለነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ፣ ከጠብ መንጃ ይልቅ በምርጫ ሳጥን ሥልጣን እንዲገኝ ከ20 ዓመት በፊት መታገል መጀመራቸውን ተናግረዋል። አክለውም ለነጻነት ስትሰራ ዓመታትን አሳልፋለች ብለዋል። ኮሚቴው "ለቬንዙዌላ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማስፈን እና ፍትሃዊ እና ሰላማዊ፤ ከአምባገነንነት ወደ ዲሞክራሲ ለመሸጋገር ባደረገችው ትግል" ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንደሰጣት በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።
የኖቤል ኮሚቴ በዚህ ዓመት በተደጋጋሚ ሽልማቱ ይገባኛል ሲሉ የነበሩትን የአሜሪካው ፕሬዚዳንትን በመተው ቬንዚዌላ ላይ ማተኮር መርጧል። የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸነፊ ከሜዳሊያ እና ምስክር ወረቀት ባሻገር 11 ሚሊዮን የሲውዲን ክሮነር (1.2 ሚሊዮን ገደማ) ተሸላሚ ይሆናል።
የኖቤል ሽልማት በሲውዲናዊው የፈጠራ ባለሙያ፣ ሳይንቲስት፣ የንግድ ሰው አልፍሬድ ኖቤል ነው የተመሰረተው።
የኖቤል አሸናፊዎች ሽልማት ሥነ ስርዓት የሚካሄደው አልፍሬድ ኖቤል በ1896 በሞተበት ቀን ታሕሳስ 10 (ዴሴምበር 10) ይሆናል።»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።