በቀል፦ አመድ፤ እና ጥላቻ ለማፈስ አትሽቀዳደሙ። #እባካችሁ - ተው! #እረፋም! የጦርነት ድግስ ይቁም! የዶር ሙላቱ ተሾመ ትጋት #ለኖቤል ሽልማቱ ጥበቃ ነው። #ዘብአደርነት።
በቀል፦ አመድ፤ እና ጥላቻ ለማፈስ አትሽቀዳደሙ። #እባካችሁ - ተው! #እረፋም ! የጦርነት ድግስ ይቁም! የዶር ሙላቱ ተሾመ ትጋት #ለኖቤል ሽልማቱ ጥበቃ ነው። #ዘብአደርነት ። ከሞያሌ እስከ አባይ ምንጭ፤ ከአባይ ምንጭ እስከ ሮኃ ለመስፋፋት ለአወጄ ኃይል እራስን? መታመንን? ቅንነትን ለመገበር ወረፋ መያዝ ጅልነት ወይንስ ድብነት????? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ፖለቲካ ማለት ጥፋት መናፈቅ፤ ፖለቲካ ማለት እራስን ማንደድ፦ ፖለቲካ ማለት ትውልድን ሰርክ ለባሩድ መማገድ፤ ፖለቲካ ማለት በኋላቀርነት መቀጠልን መፍቀድ - መናፈቅ፤ ፖለቲካ ማለት ለሥልጣኔ ፀር መሆን፤ ፖለቲካ ማለት በቀውስ ውስጥ መዳከር፤ ፖለቲካ ማለት ለጥፋት መጣደፍ፤ ፖለቲካ ማለት ትውልድን ማቆራረጥ፤ ፖለቲካ ማለት ስጋትን ዲል ባለ ሆታ ማቆላመጥ፤ ፖለቲካ ማለት ህዝብን ከሰቀቀን ጋር ማፋለም አይደለም። ሊሆንም አይችልም። ፖለቲካ ለህዝብ የመኖር ዋስትና ዝቅ ብሎ፦ ሎሌ ሆኖ መትጋት ማለት ነው። በቀላል አገላለጽ የህዝብን የመኖር ዘይቤ በአስተዳደር ጥበብ ማቅለል፤ ማሻሻል፤ ህዝብ መኖሩን ይወደው ዘንድ አስቻይ ሁኔታወችን በቅንነት ማመቻቸት ማለት ነው። ወደ ውስብስቡ የሳይንስ እና የፍልስፍና ተፈጥሮው ሳንዘልቅ። ቀላሉን የህዝብ የማስተዳደር ተግባር ለመከወን ደግሞ ህዝብን በሰርክ ማገዶነት ማቅርብ ሳይሆን፦ መኖሩን ያለስጋት የሚከውንበት ፈሊጥ ተግቶ ማሰናዳት ነው። ይህ ሲያቅት ነው ብዙ ጊዜ የቀውስ ናፍቆት የሚመጣው። ለስሜን ህዝብ ጦርነት ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ አስተናግዷል። ቢያንስ አሁን ይበቃዋል - ጦርነት። ስሜናውያን በቃን ጦርነት ብለው በህብረት ሊነሱ ይገባል። በዚህ ጦርነት ኦሮምያ፤ ደቡብ፤...