ልጥፎች

ከጃንዋሪ 29, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ህወሃት እና የአዝመራ #ዘረፋው በወርሃ የካቲት ትውፊቱ ነው። ህዋህታዊነትስ - ምን #ጠቀመ፤ ምን አከሰረ?

  ህወሃት እና የአዝመራ #ዘረፋው በወርሃ የካቲት ትውፊቱ ነው። ህዋህታዊነትስ - ምን #ጠቀመ ፤ ምን አከሰረ?   "ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘለዓለም ሲያለቅስ ይኖራል።" መጥኒ ላንች እቴጌ ጎንደር። ልብ በአቅል ግዢ ከአጤወችሽ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰። ዘለግ ያለን ትዕግሥት እና ማስተዋል የናፈቀው የወግ ገበታ ነው ለማህበረ ቅንነት።    #መቅድመ ፍሬ ነገር።   ጤና ይስጥልኝ የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ከእኛ ቅዝቃዜውም ለክፋ አይሰጥም። ካናዳ እና አገረ አሜሪካ ያሉ ወገኖቻችን ከቶ እንደምን አድረው ይሆን?   በውነቱ ህወሃትን በሚመለከት ምንም ለማለት ፈጽሞ አልፈልግም ነበር። ከምል "ሙያ በልብን" ብከውን የተሻለ ቀና መንገድም ነው ብዬ አምናለሁኝ። ለዛውም እኔ የልቤ ደርሶ፤ መሻቴ ተሳክቶ #የጃርት ጉባኤው የህወሃት ተንጠራርቶ፤ ተወራኜቶ #አራጦ የመግዛት ዘመኑ #እርሾ አልባው ክትመቱን ከማዬት በላይ መታደል ስለለ ግራ ቀኙን በትዝብት፤ በዝምታ ማየቱ ምርጫያ ነው።   ነገር ግን ዘመኑን ሁሉ በድንጋጤ፤ በጭንቀት እና በስጋት እንዲኖር የተፈቀደበት፤ የተፈረደበትም ሁነትን አስመልክቶ ለአዲሱ ትውልድ ትንሽ መረጃ ብሰጠው አይከፋም በሚል ነው አመጣጤ። ህወሃትን መንገድ መሪነት የተቃጠለ፤ ኤክስፓየርድ ያደረገ የአስተሳሰብ ድህነት ነው። የህወሃት ጉዞ በየትኛውም ሁነት ሊገታ ይገባል።   " #ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል፤ ዘለዓለም ሲያለቅስ ይውላል።"   ወርኃ የካቲት የስሜን ጎንደር ገራገር ንጹህ ገበሬ ዓመቱን ሙሉ የለፋበት አእዝርቶቹን ሳይዘራ፤ ሳያርም፤ ሳያጭድ፤ ሳይወቃ የኖረ #ሰ...