#ሰላም #ይመረቅልን። አሜን። #ይቅናን። አሜን።
#ሰላም #ይመረቅልን ። አሜን። # ይቅናን። አሜን። የዛሬ ሁለት ዓመት ለእኛ የፆመ ጽጌ በር ዕለት መስከረም 26፣ በአውሮፓውያኑ #ጥቅምት ፯ ቀን ማት እስራኤል ላይ በጋዛ አጥቂወች ተፈጸመ። ያን ዕለት ተከትሎ በግራ ቀኙ ስንት ህይወት፣ ስንት መኖር፣ ስንት ተስፋ #አረረ ? መፈጠር ተኮማተረ። ደም ፈሰሰ። ዕንባ ፈሰሰ። ዛሬ በዚህች #ቅጽበት ሁለቱ በአገረ ግብጽ በተከበሩ ፕሬዚዳንት ትራፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አነሳሽነት ድርድር ላይ ናቸው። ይቅናቸው። አሜን። ጦርነት ትውልድ ሊረከብ አይገባም። ጦርነት ትውፊት ሊሆን አይገባም። ስጋት የትውልድ መኖርን ሊያሰቃየው አይገባም። ፍልስጤማውያን #አገር #ይገባቸዋል ። የእስራኤልን አገርነትንም ፍልስጤማውያን እና አጋሮቻቸው #ሊቀበሉት ይገባል። በመጨረሻም፣ ስምምነቱ ያለ #እንከን ይፈጸም ዘንድ ምኞቴ ነው። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፈጠርልኝ።" አሜን። ይህ የጭስ ፎቶ አንድ ልጅ ሰላምን እየለመነ ይመስለኛል። በወቅቱ ዜና እያዳመጥኩ የቀረጽኩት ነው። እግዚአብሄር አምላክ፣ አላህ ለዓለማችን #ሰላም #ይመርቅልን ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 07/10/2025 በቃ ጦርነት። በቃ መገዳደል። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነ ው