#የዳነ #ሃሳብ #ቀድሞ ራስን #ያድናል፤ #ትውልድን #ያድናል፤ #አገር #ያድናል #ቅዱስ #ነውና!
#የዳነ #ሃሳብ #ቀድሞ ራስን #ያድናል ፤ #ትውልድን #ያድናል ፤ #አገር #ያድናል #ቅዱስ #ነውና ! #የዳነ ~ሃሳብ ለእኔ ሰማዕትም ነው። #የዳነ ~ ሃሳብ ብዙ ይፈተናል። #የዳነ ~ ሃሳብ በወጀብ፤ በብዙ ጦሮ፤ በብዙ ማዕበል ይፈተናል። ግን ህውከቱን ጸጥ አድርጎ ብስጩውን አየር ሳይቀር #ፈውሶ ያሸንፋል። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ምዕራፍ ፲፯ #በር ። የሥርጉትሻ ቤተ - ቅንነት ውድ ቤተኞች እንደምን አላችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ በጣም ደህ ነኝ። ዕለተ ሰንበትን #ከዳነ ~ ሃሳብ ፍልስፍናዬ ጋር እንወያይ ዘንድ ፈቀድሁኝ። የዳነ ~ ሃሳብ ጋር ስሆን የሚኖረኝ የማሰብ አቅም እና የጤናዬ ሁኔታ፤ ከብስጩ ሃሳብ ጋር ስቆይ የሚገጥመኝ የጤና እክልን ለረጅም ጊዜ በህይወቴ መረመርኩት። እርግጥ ነው የሚያበሳጨኝ ነገር እኔ ዕውነት ሲንገላታ ነው፤ መርኽ እክል ሲገጥመው። ዕውነትም መርኽም እንደ አቅርቦታችን ስለሚለያይ እኔ መርህ ዕውነት በምላቸው ጥሰት ተፈጽሟል ብዬ ሳስብ ነው በሰጨኝ የሚመጣው። ሙሉ ዕድሜ ላይ እንኳን ስክነቱ በራሱ ይቆጣጠራል። የተፈጥሮ ጸጥታ አስከባሪ ስለሚሆን አይቸግርም። እኔ አብዛኛውን ጊዜየን እማሳልፈው በአገራዊ ጉዳይ ነው። በመፃፍ፤ ሌሎችን በጥሞና በማድመጥ እና በትጋትም በመሞገት። እራሱን #አንቱ ያለ፤ ወይንም በሌላው አንቱ የተባለ ዕውነት በሆነ አቅም ላይ ምስክርነት ለመስጠት ይሳነዋል። ቆጥቋጣ ነው። ሌላውን ሲያስተልቅ እሱን የሚያሳንስ ይመስለዋል። ደፍሮም አስተያዬት በሚታወቅ ሥሙ ለመስጠትም ራድ የሚይዘው ይመስለኛል። በሌላ በኩል ከክብሩ ዝቅ ያለም ይመስለዋል። በእኔ ቤት ...