ልጥፎች

ከጁላይ 1, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ክፍል አራት ርትህ።

ምስል
ርትህ። ክፍል አራት። ከሥርጉተ © ሥላሴ 01.06.2018 (ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።) „የሚምሩ ብብፁዓን ናቸው ይማራሉ እና“ (የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯) ·        መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_WVc5bXyb5c ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar ·        የወግ ገበታ። ውዶቼ ቀደም ሲል የነሳ ኋ ዋቸው ከክፍል አንድ እስከ ሦስት ድረስ ለመነሻ መዳረሻ የሚሆኑትን ብቻ ስለነበር ሊንኩ አለጠፍኩትም ነበር። አሁን በዚህ በክፍል አራት የምናዬው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሠመራ በነበረው ጉባኤ ላይ የሰጡትን መልስ አስኳል ጉዳዮችን ማዬት ስለሚያስፈልግ ነው። በዚህ ክፍል እስከ መግቢያዋ ላይ ያለችውን ጥላቻን ብቻን ማዬት ብንችል ብያለሁኝ አሁን። እንዳይበዛ እንዲሁም አሰልቺም እንዳይሆን። „ሰው ጠልተህ መተኛት አትችልም። ሌሊቱን ሰውዬው በሌለበት ስትቃጠል ነው የምታድረው። እሱ አያይህም። ያለህበትን ሁኔታ አያውቅም። አንተ ግን ስትቃጠል ታድራለህ። ከዚህ ውጪ መወጣት አለበት። ሰውን ለመጥላት መሮጥ ነገርን ለማሰብ  አዕምሮአችን ማበላሸት የለብንም! ጊዜያችን ማጥፋት የለብንም! እኛ ምን እንደርጋለን? ሰው እንወዳለን! ሰው እናቀርባለን! እስከተቻለን ድረስ ሰውን እንረዳለን። ነገር ግን የሚጠሉን ሰዎች እንደሚኖሩ እናውቃለን። ዓለም እንዲህ ስለሆነች። ሰዎች ሲጠሉህ አንተም ቁልቁል ተመልሰህ ጥላቻ ውስጥ ከገባህ በእነሱ ሜዳ ውስጥ ገብተህ እዬተጫወትክ ነው ማለት ነው። የጦር ሜዳው

ክፍል ሦስት - ርትህ።

ምስል
ርትህ። ርት ክፍል ሦስት። ከሥርጉተ © ሥላሴ 30.06.2018  (ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።) „በመንፈስ ደሃ የሆኑ ሰዎች ብጹዓን ናቸው፤      መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና“ (የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፫) ·        የ እኔ ክብረቶቼ ውዶቼ … ቀደም ባለው ጊዜ ቅኑ እና ደጉ ሳተናው ብዙ ደንበኛ ስላለው አበዛበታለሁ በማለት የምዘላቸው ብዙ ጉዳዮች ነበሩ። አሁን በራሴ ብሎግ ላይ ስለምሰራ አባዛለሁኝ የሚል ሰቀቀን ስለሌበኝ በሙሉ አቅሜ እሰራለሁኝ ብያለሁኝ ከፈጣሪ ጋር። የምዋሳው ሆነ ከሌላ የምጠብቀው የብዕር የህሊና ምርት የግብይት ሥርዓት ስሌለበኝም እራሴው የሚሰማኝን እንደ ገባኝ እጠፈዋለሁኝ። ማንዘርዘሪያ ወንፊቱ ደግሞ የእናንተ የመንፈስ አዱኛዎቼ ነው።  ባፈው ሳምንት ለጋዜጠኛ መሳይ መከነን „አንዳንዶቹ ባይደመሩስ“ በሚል  መጣጥፍ ላይ ስሞግት እኔ ስለማጠሪያ፤ ማንዘርዘሪያ ወንፊት ዓይነ ጠባቦች የመደመርን ፍልስፍና ያሰተነጋዱበት ጠንጋር ዕሳቤ፤ መደመርንም እኛ እንምራው ዓይነት ጉዞ ስጥፍ ተናግሬ ነበር። ዛሬ በሠመራው ጉባኤ ይኸውኑን ጠ/ ሚሩ ሲናገሩት ሰማሁኝ። ቅንነት ካለ ሳትነጋገሩ፤ ሳትተዋወቁ፤  አንዱ አፍሪካ ሌላው አውሮፓ ላይ ሆኖ አንድ በሚያደርገው የሃስብ ሃዲድ ትገናኛለችሁ ካለ ድርጅታዊ ሥር ማለት ነው። ካለ ካድሬያዊ ፕሮፖጋንዲስት ወይንም የፕሮቶኮል ጣጣ ምንጣጣ ማለት ነው። መደመር አብሮ መደመር ነገር ግን ቅሬት አካሎች ሳንክን ፈጣሪ ከሆኑ በማጣሪያው ተግባር ይጣለላሉ ማለት ነው።  የሆነ ሆኖ አሁን ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን ከሥር ከሥር መሥራት የሚያሳቅቀኝ ነገር ዛሬ ላይ የለበትም። ስለዚህም የአፋርን ዕድምታ ሠመራን መነሻ በማድረግ ምእራፍ አንድ እና ሁለትን ጽፌያለሁኝ የጉዞ