ልጥፎች

ከጁን 17, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ አባት አቶ አህመድ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተደመጠ።

ምስል
„መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ“ የጠቅላይ ሚ / ር አብይ አህመድ አባት የ ዕድሜ ባለጸጋው አቶ አህመድ አሊ በ 105 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ አሁን ዜና ዘሃበሻ አዳምጥኩኝ። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማር። አሜን! ወቅትን መሻማት ከጸጸት ይታደጋል። ሁላችንም እንማርበት ዘንድ ፈጣሪ ይህን የትምህርት ተቋም በብሄራዊ ደረጃ ከፍቶልናል። መቅደም ያለበትን እናስቀድም ዘንድ። ጠ / ሚር አብይ አህመድን ጨምሮ ለልጆቻቸው፤ ለቤተዘመዶቻቸው፤ ለመላ ቤተሰባቸው ሁሉ መጽናናቱን ፈጣሪ ይስጥ። አሜን ! አቶ አህመድ አሊ ቀደም ባለው ጊዜ እንደተረዳሁት ለህዝባዊ አገልግሎት መሬታቸውን በፈቃዳቸው የሚሰጡ ለአገር እና ለህዝብ አሳቢ እና ተቆርቋሪ እንደሆኑ አንድ ቃለ ምልልስ ላይ አዳምጫለሁኝ። ስለሆነም በዕድሜያቸው ለአገራቸው የሚገባውን በማድረጋቸው በሥጋ ቢለዩም በነፍስ ግን ዘላለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። እጓጓ የነበረው አንድ ቀን በቤተ መንግሥት ደስ ብሏቸው ለማዬት እፈቅድ ነበር። ብቻ ሰው ካሰበው እግዚአብሄር ያሰብው ሆነና የተመኘሁትን አላገኘሁም። እኔ እንዲህ በዕድሜያቸው የገፉ ሰዎችን ሐሤት፤ ተስፋ፤ ሰናይ ማዬት በእጅጉ የሚናፍቀኝ ነገር ነበር። * ፎቶ ከቢቢሲ አማርኛው ዝግጅት የተወሰደ። ፈጣሪ በምንማርበት መስክ ሁሉ ጠቃሚ ትምህርትን ህሊናችን ይፈቅድ ዘንድ ይርዳን። አሜን ሥርጉተ ሥላሴ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

የአሉታዊው የዴሞግራፊ ዕሳቤ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የታዘዘ የጢስ አይዎሎጂ ነው። {የወግ ገበታ 17.06.2019}

ምስል