ልጥፎች

ከኤፕሪል 12, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

መደራጀት ሊፈራ አይገባውም።

ምስል
  ይህ ግርባው ብአዴን ዬወጣቱን መንፈስ ሲያደነዝዝ በነበረበት በ2011 ዬጻፍኩት ነው። መደራጀት ሊፈራ አይገባውም።   • እፍታ። መደራጀት ኃይል ነው። መደራጀት አቅም ነው። መደራጀት ስንዱነት ነው። መደራጀት ፍቅር ነው። መደራጀት አብነት ነው። መደራጀት የታማኝነት ማስፈጸሚያ ነው። መደራጀት የህሊና መቅኖ ነው። መደራጀት ዓላማና ግብ ያለው ሰብዕና ማለት ነው።መደራጀት የአብሮነትም አንባ ነው። መደራጀት የሥን - ልቦና ቅዬሳ ተቋም ነው ለአዎንታዊ ከተጠቀምንበት። ይህችን ለመግቢያ ከከሽንኳት በኋላ እምጠቅሰው በመደራጀት ዙሪያ ያሉ ጥቂት ነገሮችን ነው። በጽንሰ ሃሳቡ ዙሪያ ሌላ ጊዜ ብመለስበትም ትንሽ የአማራ ወጣቶች በገጠማው አንኳር ችግር የምለው ይኖረኛል። • ወግ። የአማራ ወጣቶች እዬተደራጁ ነው። ማህበራቸው ነፃ እና ገለልተኛ ነው። ማህበራቸው ዓላማ እና ግብ አለው። ዓለማ እና ግብ ደግሞ የአንድ ድርጅት መሰረታዊ ጉዳይ ነው። የአማራ ወጣቶች መደራጀት የአዳማን ሥርዕዎ መንግሥት አላስደሰተም። ስለሆነም እውቅና እንዲነፈገው ተደርጓል። ከሰኔ 15 በፊት በነበረው ሰንበት የደብረታቦር ወጣቶች ኢንጂነር ይልቃልን ጌትነትን ጋብዘው ነበር ነገር ግን ታግደዋል። ይህ መቼም እኔ እብደት ነው የምለው። ሰው ያበደ ዕለት ጋብቻን ያግዳል። ልክ እንደ ባቢሎን ግንብ ቀያሹ እንደ አቶ በቀለ ገርባ ማለት ነው። ነፍሳቸውን ይማረውና ዶር አንባቸው መኮነን በመሩት ጉባኤ ደብረታቦር ላይ የወጣቶች ጉባኤ ነበር። አቶ ዮኋንስ ቧያለውም ተገኘተው ነበር። ሁለተኛ የወጣት ድርጅት አስፈላጊ አለመሆኑ በአጽህኖት ሲገልጹ ሰምቻለሁኝ። በፖለቲካ በሳል ከሆኑ አንድ የፖለቲካ ሊሂቅ የማልጠብቀው ገለጻ ነበር። በተፎካካሪያቸው በአብን ላይም የነበራቸው ምልከታ ጤናማ አልነበረም። ፖለቲካ በ...

ድምጽ አልባዋ የአማራ እናት ዓመት ይዞ እስከ አመት የልጅ ማገዶ ታቀርባለች።

• ድምጽ አልባዋ የአማራ እናት ዓመት ይዞ እስከ አመት የልጅ ማገዶ ታቀርባለች። • ይህም ዬግብሩ ልክ ነው። ሁሉም ብሎጌ ላይ አለ በወቅቱ ለአምንስቲ፥ ለተመድ ሰባዕዊ መብት አስከባሪ ኃይል ተልኳል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ታስረው የሚገኙ ሰዎች ዝርዝር! 1 በሪሁን አዳነ 2 ጌታቸው አምባቸው 3 ምሥጋና ጌታቸው 4 ማስተዋል አረጋ 5 ታመነ ክንዱ 6 አለምነህ ሙሉ 7 ውዱ ሲሳይ 8 ሻለቃ አያሌው ዓሊ 9 ፈለቀ ሀብቱ 10 በለጠ ካሣ 11 ክርስቲያን ታደለ 12 የሺዋስ አሞኘ 13 አንተነህ ስለሺ 14 ፋንታሁን ሞላ 15 ሲያምር ጌቴ 16 ዮናስ አሰፋ 17 አማረ ካሴ 18 ንጉሥ ይልቃል 19 ሺገዛ ሙሉጌታ 20 ሞላልኝ መለሰ 21 ፍስሃ ገነቱ 22 በዕውቀቱ አግደው 23 ጓዴ ደረጃው 24 ቤዛ በኃይሉ 25 ዮሴፍ ገበየሁ 26 አለነ ጥላሁን 27 ዮናስ ወንድአጥር 28 በዕውቀቱ በላቸው 29 ይበልጣል ፈረደ 30 እንየው ህብስቱ 31 ሻምበል ጋሻው ምሕረት 32 ፶ አለቃ ጀማል ሀሰን 33 ፶ አለቃ ግዛቸው ሞላ 34 ፶ አለቃ ሞላልኝ ዘለቀ 35 ዮሐንስ ካሣው 36 ብሩክ መኮንን 37 ቢንያም አንማው 38 ደጀኔ ሸዋረጋ 39 አበበ እሸቱ 40 ፶ አለቃ አይተነው ታረቀኝ 41 ካሣ ዘገየ 42 ስጦታው ካሣሁን 43 ሻምበል ታደሰ ወ/ገብርኤል 44 አባትነህ ሰውነት 45 ፲ አለቃ ዓለሙ ሙሌ 46 ፲ አለቃ ጌታሁን ፍቅሬ 47 ፲ አለቃ ይማም መሐመድ 48 እንዳለ ካሣ 49 ኮንስታብል ዓባይ አዲስ 50 ፶ አለቃ አምባዬ ገላዬ 51 ቦጋለ ጌታሁን 52 ዋና ሳጅን ሞገስ ደጀኔ 53 ሳጅን ገረመው ሙሉነህ 54 ሲሳይ አልታሰብ 55 አየለ አስማረ 56 አስጠራው ከበደ 57 ስንታየሁ ቸኮል 58 መርከቡ ኃይሌ 59 በኃይሉ ማሞ 60 ምንውየለት ባወቀ 61 ሮዛ ሰለሞን 62 ታከለ በቀለ 63 ኅሩይ ባየ 64 ዳኛቸው ...

የልዩ ኃይሎችን ትጥቅ መፍታት ውሳኔን በሚመለከት!

#በሙሉ ልቤ የማምነው ወጣት ዕይታ። እጅግ እምሳሳለት ወጣት ነው። Stolz. የገባው ብቸኛ ወጣት ነው። ተፎካካሪ፤ ተዋህጅ አካሄጅ፤ ተቃዋሚ ሁሉም እሱ የሚያነሳውን ሃቅ አይደፍሩትም። በትክክል በእኔ ሴል ውስጥ የታተመውን ዬታገልኩለትንም ቁልጭ አድርጎ ይገልፃል። ለማተቡም ቀናዕይ ነው። ከዘሃበሻ ፔጅ ያገኜሁት። "Yosef Ketema Hordofaa Lomi የልዩ ኃይሎችን ትጥቅ መፍታት ውሳኔን በሚመለከት! ጉዳዩን ከሚደግፉ ወገኖች ውስጥ ነበርኩ! ነበርኩ ማለት አሁን አይደለሁም ማለት ነው፡፡ ለምንʔ ?????????????????????????????? 1ኛ ብልጽግና እንደ ስብስብ ሕዝብን በእኩል የማያይ፣ በብሔርና በሃይማኖትም በተለይ የኦርቶዶክስና የአማራን ጥፋት የሚሻ መሆኑን በግልጽ እያሳየ በመምጣቱ ነው፡፡ ይሄንንም ባለፉት አምስት አመታት አንድም እልቂታቸውን ባለማስቆም፣ እራሱም ደግሞ የሚገድልና የሚረሽን ሆኖ አሁን ደርሷል፡፡ 2ኛ ኢትዮጵያውያንን በሃይኖትና በዘር ለይተው የሚጨፈጭፉ የሚያፈናቅሉ ኃይሎች ትጥቅ አልፈቱም፣ የበለጠ እየተጠናከሩ ነው፡፡ 3ኛ እራሱ መንግሥት ከየአካባቢው፣ በተለይም በአዲስ አበባ ዙርያ የዘር ማጥፊያ ከተማ መሥርቶ የኢትዮጵያን ብዝኃነት እያጠፋ /በሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም ጉዳዩ ዘርን መሠረት ያደረገ መሆኑ መረጋገጠኑን ልብ ይልዋል/፣ መቶ ሺህዎችን እያፈናቀለ የዘር ማጥፋት ፕሮጀክቱን በይፋ እየተገበረ ነው፡፡ 4ኛ አማራ የተባለውን ክልል በተለየ መልኩ ለማጥፋት እንደሚፈልጉ የብልጽግና ፖለቲካ ልሂቃን፣ በተለያየ ፓርቲ ስም ያሉ ግለሰቦች፣ በኦሮሞ ስም የሚነግዱ በዘር ማጥፋት ፍላጎት የተሳከሩ አክቲቪስቶች ወዘተ. እየዛቱና ያንኑ በተግባር እያሳዩ በመሆኑ፣ 5ኛ መከላከያውን በጄኔራል ኢታማዦር ሹምነት የሚመሩት ሰውዬ ተtረኝነትን የሚ...

መንፈስን ሳያሻቅሉ መሰረታዊ ትግልን ይጠይቃል።

ምስል
  መንፈስን ሳያሻቅሉ መሰረታዊ ትግልን ይጠይቃል።      መለያ ኮዱ አማራነት የሆነ ዬ10 ሺህ የጅምላ እስር በአዲስ አበባ። ከ10 ሺህ ያላነሱ የአማራ ተወላጆች በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ታፍነዋል፤ ታግተዋል። እስር ቤቶች በሙሉ ሞልተዋል። የወጣቶች፤ የበጎ አድራጎት ድርጅት፤ የሚዲያ መሪወች፤ ሙሁራን፤ ሊሂቃን በሙሉ ታፍነዋል። ዬዜናው ጭብጥ ዬአንከር ሚዲያ ነው። ይህ እንግዲህ ወያኔ ይወገድ እንጂ ትርፋ ገብስ ነው ሲሉ ለነበሩ ዘመን አመጣሽ ፖለቲከኞች ምን ሊሉት እንደሚችሉ አድራሻ ቢስ ዕሳቤውን በመና ያወራርደዋል። በሌላ በኩል አዲስ አበባ ላይ አቅሙን አጠናክሮ ለፖለቲካ ሥልጣን ያልበቃው ዬአማራ ብቸኛ ዬፖለቲካ ድርጅት አብን ፀፀቱ ዕለታዊ ስንቅ እንደሚሆነው አስባለሁ። አማራን እታደጋለሁ ብሎ ዬተነሳ ድርጅት በደብዳቤው መጨረሻ አዲስ አበባ ሽዋ ዬሚለው ህልምነትን አወራርዷል። ይህን በበላይነት የመሩ ያስተዳደሩ ለስውር ፍላጎታቸው አቅም ዬሆኑ የዲሲ ስውር ድርጅትም ተልዕኳቸውን አሳክተዋል። ለፖለቲካ ስልጣን አልታገልኩም ያለው ቲም ገዱም በፎርፌ አጨብጭቦ መራራ ስንብት አድርጓል። በዚህ ማህል አማራ መሃል ላይ ብቻውን ሰርክ በመገበር ላይ ይገኛል። ዘመነ ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊን ለመታገል ፈርሶ በሚሰራ የእነ ቶሎ ተሎ ቤት ወይንም በኮፒ ራይት ሽሚያ ሊሆን አይገባም። ዬሰከነ ሙሁራዊ ዕውቀትን ይጠይቃል። መከራው በላይ በላይ ቢሆንም በቅደም ተከተል ሊሠሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ መንፈስን ሳይበቱኑ ወይንም ሳያሻቅሉ መትጋትን ይጠይቃል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 11/04/2023 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። Author Sergute Selassie

በተስፋ ማጣት ውስጥ ተስፋ አይገኝም።

ምስል
  በተስፋ ማጣት ውስጥ ተስፋ አይገኝም። "ዬሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱)     ተስፋ እግዚአብሄር ነው። ተስፋ የእዮር ስጦታ ነው። ተስፋ የአቅም መክሊት ነው። ተስፋ የማግስት የችሎት አደባባይ ነው። ተስፋ መፈጠራችን ነው። ተስፋ ትናንት፤ ዛሬ እና ነገም ነው። ሰከንዳት፤ ደቂቃት፤ ሰዓታት፤ ወራት፤ ዓመታት፤ ዘመናት ሁሉ በተስፋ ይኖራሉ ይተማሉ ይፀድቃሉ። ፍጥረታት በተስፋ ተፈጥረው ተስፋ ይሆናሉ። ዓላማ በተስፋ ተፀንሰው የግብ ሠራዊት ይሆናሉ። ተስፋ እና ተስፈኛው ሰክነው መነጋገር፤ መወያዬት መምከር ከቻሉ ተስፋ ለድል ይበቃል። ተስፋ ፈንታዚ አይደለም። ይልቁንም ከእግዚአብሄር ተስፋ ይሰጥ፤ ተስፋውን እሱ ይመራው ዘንድ መፍቀድ። መፍቀዱ በትህትና እና በአክብሮት በጥሞና እና በመታመን ከሆነ ተስፋን የፈጠረ አምላክ ለሰጠው ስጦታ ተፈፃሚነት ይቆማል። አብሶ ቅን ሆኖ፤ ግልጽ ሆኖ፤ ደግ ሆኖ ሰዋዊ እና ተፈጥሯዊ የሆነ ጉዞ ተስፋውን ያገኛል። የሚያገኜው ተስፋም የፀና ይሆናል። ተስፋን ለሰው ሲሰጥ ወጣ ገባ ነው። ተስፋን ለፈጣሪ ከሰጡት ግን ባለቤቱ ይከውነዋል። አሁንም በአባ እዮብ አማራዬ ላይ ተስፋዬን ለተስፋ ፈጣሪ ለአምላኬ ነው እምተወው። ተስፋዬ በፍጡራን አቅም፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ዘንድ አላደርግም። አብሮ መዛል፤ አብሮ መበተን መሆኑን አስተውያለሁኝ። ዬሚገርመው ትግል አቆምኩ ሲል አንድ ነፍስ ያ ሁሉ ተስፈኛ ለበሽታ፤ ለመከራ ሸልሞ መሆኑ አይታዬወም። ምንጊዜም ጥገኝነታችን ለፈጣሪ እንዲሆን እመኛለሁኝ። ህዝባችን ተሰቃይቷል። ዛሬም እንደ ትናንቱ ለጫማ እንኳን አልበቃም። ሊቃናቱ ሊሂቃኑ ከፍም ዝቅም ቢሉ እንብዛም አይጎዱም። ህዝባችን ግን ተጎሳቁሏል። ይህን እናስተካክላለን ብለው ዬ...

እመ ቅኒት ልዕልት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዘመቻው እሷንም ያለመ መሆኑን አውቃው ይሆን???

እመ ቅኒት ልዕልት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዘመቻው እሷንም ያለመ መሆኑን አውቃው ይሆን??? #ድምፃችን ይሰማም ተመልሶ አይመጣም የሚል ዕምነት ዬለኝም። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ሰነፍ አድርጎ የሚያይ ብዙ ሰው አለ። እሳቸው ዕድሜ ዘመናቸውን ሁሉ ፕላን ሠርተው የተሰናዱትን እዬፈፀሙ ነው። ዝልኛቸውን አልወጠኑትም። መቼ ይህን ዕድል እንደሚያገኙ ቀኑን፤ ዘመኑን ባያውቁትም ከንግግራቸው ጀምሮ በስልት፤ በብልጠት፤ በማዘናጋት፤ በማተራመስ እራሳቸውን አሰልጥነው ሙሉ መሰናዶ አድርገውበታል። ደራሽነቱ ለእኛ ብቻ ነው። ለዚህ ነው እኔ ለአፍሪካ፤ ለቀንዱም ለመካከለኛውም ለዓለም እጅግ አስቸጋሪ አሳቻ መሪ ናቸው እምለው። ይህን ሃሳብ ተግ አድርጌ አሁን አዲስ አበባ ብቻ 10 ሺህ እስረኛ በህማማት እና በሮመዳን አዲስ አበባ ብቻ አለ። ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ዕምቅ አቅም የመስበር እስትራቴጂ መሆኑን ቤተክርስትያናችን ልብ ልትለው ይገባታል። ፐርሰንቱን ማውጣ ባልችልም አብዛኞቹ የቤቷ ልጆች ናቸው። በቀጥታ ሳይሆን በስውር ሰልፋ ቢቀርም በአማራነት ኮድ ፀጥ ያለ ጦርነት ተከፍቶባታል። ይህ የሚሆን የጀርባ አጥንቷ በሆነው ዬአማራ ክልልንም ያካታል። ከ14 ሺህ በላይ ፋኖ ሲታሠር እሧም ታስራለች፤ 18 ወጣቶች ሲታገቱ እሷም ታግታለች። 12983 ተማሪወች ከፈተና ውጪ ሲሆኑ እሷም አለችበት። በፓርላማ፤ በካቢኔ ውስጥ ልጆቿ ሲገለሉ እሷም አቅመ ቢስ እንድትሆን ተበይኖባታል። ዙሪያ ገባው እሷን ሆስቴጅ የማድረግ ተልዕኮ ስለመሆኑ በጥልቀት አስባ ሳትዘናጋ ከዓለም አብያተ ቤተክርስትያናት ጋር በደራሽ ችግሮች ሳይሆን በዘላቂ የህልውና ጉዳይ ልትተጋበት ይገባል። ይህን ስል ወንዝ ቁልቁል እንጂ ወደ ላይ ስለማይፈስ አሻቅቤ ልናገራት አስቤ አይደ...

Abiy Ahmed Ali of Ethiopia waged another round of war against his own people, and this time it is against the Amhara people. As a leader, it is his constitutional responsibility to protect his people from

Henok Abebe Human Rights Activist "Abiy Ahmed Ali of Ethiopia waged another round of war against his own people, and this time it is against the Amhara people. As a leader, it is his constitutional responsibility to protect his people from war, conflict, and lawlessness. However, Abiy’s actions suggest that he is not prioritizing peace and stability in his country, and words like peace and stability do not seem to be in his dictionary. Since he comes into power, Ethiopia has become a place of suffering, particularly for the Amhara people. The two-year-long war has left the Tigray people devastated. Unfortunately, the toll of the Northern War has also impacted the Amhara people, who have been killed and displaced in several regions too, including Somalie, Benshanguel Gumuz, and Sidama, during Abiy’s premiership. Ethnic-based attacks, displacement, mass arrests, and harassment have been rampant in the Oromia region, Addis Ababa city, and the Amhara region itself against the people o...