መንፈስን ሳያሻቅሉ መሰረታዊ ትግልን ይጠይቃል።

 

መንፈስን ሳያሻቅሉ መሰረታዊ ትግልን ይጠይቃል። 
 

 
መለያ ኮዱ አማራነት የሆነ ዬ10 ሺህ የጅምላ እስር በአዲስ አበባ።
ከ10 ሺህ ያላነሱ የአማራ ተወላጆች በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ታፍነዋል፤ ታግተዋል። እስር ቤቶች በሙሉ ሞልተዋል። የወጣቶች፤ የበጎ አድራጎት ድርጅት፤ የሚዲያ መሪወች፤ ሙሁራን፤ ሊሂቃን በሙሉ ታፍነዋል። ዬዜናው ጭብጥ ዬአንከር ሚዲያ ነው።
ይህ እንግዲህ ወያኔ ይወገድ እንጂ ትርፋ ገብስ ነው ሲሉ ለነበሩ ዘመን አመጣሽ ፖለቲከኞች ምን ሊሉት እንደሚችሉ አድራሻ ቢስ ዕሳቤውን በመና ያወራርደዋል።
በሌላ በኩል አዲስ አበባ ላይ አቅሙን አጠናክሮ ለፖለቲካ ሥልጣን ያልበቃው ዬአማራ ብቸኛ ዬፖለቲካ ድርጅት አብን ፀፀቱ ዕለታዊ ስንቅ እንደሚሆነው አስባለሁ። አማራን እታደጋለሁ ብሎ ዬተነሳ ድርጅት በደብዳቤው መጨረሻ አዲስ አበባ ሽዋ ዬሚለው ህልምነትን አወራርዷል።
ይህን በበላይነት የመሩ ያስተዳደሩ ለስውር ፍላጎታቸው አቅም ዬሆኑ የዲሲ ስውር ድርጅትም ተልዕኳቸውን አሳክተዋል። ለፖለቲካ ስልጣን አልታገልኩም ያለው ቲም ገዱም በፎርፌ አጨብጭቦ መራራ ስንብት አድርጓል። በዚህ ማህል አማራ መሃል ላይ ብቻውን ሰርክ በመገበር ላይ ይገኛል።
ዘመነ ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊን ለመታገል ፈርሶ በሚሰራ የእነ ቶሎ ተሎ ቤት ወይንም በኮፒ ራይት ሽሚያ ሊሆን አይገባም። ዬሰከነ ሙሁራዊ ዕውቀትን ይጠይቃል። መከራው በላይ በላይ ቢሆንም በቅደም ተከተል ሊሠሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ መንፈስን ሳይበቱኑ ወይንም ሳያሻቅሉ መትጋትን ይጠይቃል።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11/04/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።