ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦
ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦ አዲስ አበባ። "ጎለመስኩ አረጀሁም፤ ፃድቅ ሲጣል፦ ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።" (መዝሙረ ዳዊት ም ፴፮ ቁ ፳፭) ዶር ዳንኤል ሆይ! በቅድሚያ እንደምን ሰነበቱ? ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የሊቀ ሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው ዬዬኔታ ቤት ሰፊ ሰቆቃ እዬደረሰበት ነው። ብዙ የቆሎ ተማሪወች ህይወታቸውን አጥተው ሰማዕትነትን መቀበላቸውን በተለያዬ ጊዜ ይደመጣል። በሌላ በኩል የቆሎ ተማሪወች በእስር እንግልት ላይ መሆናቸውንም ባለፈው ሳምንት በላስታ ላሊበላ ቅርስ ችግር ላይ ከተወያዬው ጉባኤ ተገንዝቤያለሁኝ። 1) የታሰሩ የቆሎ ተማሪወች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ እንዲረዱን እሻለሁኝ። በእንተ ሥመ ለማርያም ብለው ለምነው፤ ከውሻ ጋር ተጋፍተው፤ እራፊ ጨርቅ ሌት እና ቀን ተላብሰው ቀለም ሊማሩ የሄዱ ንፁኃን እንደምን በእስር ይንገላታሉ? ይህን ጉዳይ ድርጅተወት በይፋ ዕውቅና ቢሰጠው እና ክትትል ያደርግበት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ። 2) በድሮን የሚከወነው ጥቃት በአብያተ ቤተክርስትያን፤በገዳማት፤ ሰብሰብ ብለው በሚገኙ ንፁኃን ላይ ስለመሆኑም አዳምጣለሁኝ። እንደምን አንድ ምራኝ ብሎ የተመረጠ መንግሥት በህዝቡ ላይ ይህን መሰል አረመኔያዊ ተግባር ይፈጽማል??? መቼ ነውስ የሚቆመው? ለዓለም ሰላም ወዳድ ኃያላን አገሮች እና ስለ ሰው የሚገዳቸው ሉላዊ ተቋማትም በሚገባቸው ቋንቋ ጉዳዩን ማሳወቅ የሚገባ ይመስለኛል። ሰው እኮ ዳንቴል አይደለም። 3) የላሊበላ አብያተ ትውፊቶች፤ እና በሌሎችም ያሉ አብያተ ቤተ ክርስትያናት እንደ ትውልድ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ሲገባ የጥቃቱ ሰለባ፤ ዒላማም ሆነዋል። ለምን?...