የዕውቀት ባለፀጎች ኢንፍሌንሽን ኢትዮጵያን እንዳይገጥማት እሰጋለሁኝ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
አገር የሰፈር የእድር ማህበር አይደለም። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ደጋፊያን እዬጠቀሟቸው አይደለም። ምንም አይነት የእርምት ዕይታ እንዳይኖር ጠቃሚ ሃሳቦችን በደቦ እያስበረገጉ ነው። ይህ ደግሞ ቁልቁለት ዳጥ እና ምጥ ያዋልዳል።
በሌላ በኩል በተለያዬ ሙያ ፕሮፌሽናል የሆኑ ኢትዮጵውያን ወጀብ ፈርተው አንገታቸውን ደፍተው መጠበቅ እናት አገርን መካድ ይመስለኛል። ይህም ብቻ አይደለም የሙያ ሊቀ ሊቃውን ከሙያዊ፤ ከዕውቀታዊ ማዕቀፋቸው ወጥተው ፕሮፖጋንዳውን ከተቀላቀሉም ሰፊ የሆነ የአዋቂወች በረከተ ፀጋ ኢንፍሌንሽን ኢትዮጵያ ሊገጥማት ይችላል።
የኢትዮጵያ የስድስት ዓመቱ ችግር የተጋገር ችግር ነው። ስለሆነም ያልሰከኑ ቦጅቧጃ ፍላጎቶች ትውልድንም አገርንም ማዳን አይቻልም። በሌላ በኩል የአገር እና የትውልድ ክብር እና ልዕልናም ከግለሰቦች ሙገሳ፤ ውደሳ ዝቅ ካለ ይህም የሚያስፈራ አደጋ ይመስለኛል።
ውዶቼ እንደምን እዬሆናችሁልኝ ይሆን?
ቸር ሁኑልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
4/12/2023
ፈላስፊት ኢትዮጵያ ይቅናሽ። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ