ልጥፎች

ከማርች 17, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ውድ የአገሬ ልጆች አትጨነቁ፤ አላዛሯ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና፤

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ውድ የአገሬ ልጆች አትጨነቁ አላዛሯ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና። „ወደ ህይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆቿዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ፤ ልብሳቸውን የሚያጥቡ፤ ብፁዕን ናቸው፤ አምስቱ ውሾች ግን ከዚያች አገር ወጥተው ይሄዳሉ።“ የዮሖንስ ወንጌል ፳፪ ቁጥር ፲፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                                           አምላክ አለው! ቅኖቹ የጹሑፌ ታዳሚዎች እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ እዚህ ደመንመን ብሏለኝ። አላዛሯ ኢትዮጵያስ? ያን ግዙፍ መከራ ካስተናገድን ጉዳያችን ቅርባችን ላደርግን ወገኖች ዛሬ 8ኛ ቀኑ ነው። የሰውም ግፍ ስላለው ስለገጠመው መከራ ለመርሳት ጊዜው ገና ልጅ ነው። ምልክቱ ግን እዮራዊ ነው።   በአላዛሯ ኢትዮጵያ ብዙ ቃለ ምልልሶችን ሌሉትን ሙሉ አዳመጥኩኝ። ያው ይህ የበራራ አደጋ በመንፈሴ ውስጥ ትንሽ ተገስ እስኪል ድርስ እንዲህ ነኝ - እንቅልፍ አጣለሁኝ። አንድ ጊዜ አውሮፕላን አደጋ ከደረሰ በኋዋላም ተከታይ ይኖራል ብዬ ስለማስብ ይጨንቀኛል። ሌላው ደግሞ እዛው ኢትዮጵያ መሬት ላይ ተፈጽሞ እንኳን ምንም አይመስለውም። ወደ ተነሳሁበት ስመለስ ብዙ ሰው መስጋት ብቻ ሳይሆን ልክ በቅንጅት ጊዜ የተሰማው ዓይነት በመንፈስ፤ በተስፋ መሟሸሽ አያለሁኝ። አገር እኮ አትሸመትም አትቀናም። ይህም ምን ማለት ነው? ለመሸመትም ለማቅናትም ፈቃደ እግዚአብሄር አለበት ማለት ነው።  ብላክ ቦክሱ እኮ አልተነበበም ገና ወደ ሦስት ወር ይጣይቃል ይላሉ ባለሙያዎች፤ የመጀመሪያ ደረጃ ንባቡ ለማድመጥ ለዛው