ልጥፎች

ከጁላይ 10, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አቤቶ ጊዜ ሲለግምም ሲቃናም ...

ምስል
ንጉሥ ሆይ! አቤቶ ጊዜ። „ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች።“ (ምዕራፍ ፩ ቊጥር ፳ ) ከሥርጉተ©ሥላሴ (11.07.2018) (ከገዳማዊቷ ሲዊዝ።) ጊዜ ሲያልፍ ጊዜን ተክቶ ጊዜ ሲያከትም ራሱን ጊዜን አትግቶ ግን ሲክድ እራስን አስከድቶ ሲመጣም ሲሄድም ጊዜ አውክቶ ተፍነክንኮ ተፈልቀልቆ … በሰነፎች አሽካክቶ በልባሞች ተመስጦ በማስተዋል ተከንድቶ። ጊዜ ሆይ! የደላው …. ልግመኛው ባለዱላው ሲመጣም ሲሄድ የማይደከመው አይታክቴው ሲያሰኘውም ከትክቶ ሲያሻውም አንኮታክቶ በስልት ማጭድ አዘናግቶ ጌዜ ጌታው ሁሉን ነስቶ፤ ሽው ይላል ኩፍስን አፍንድቶ። አቤቶ ጊዜ እንዲህ ነው … … ቅነኛነት ሲያሻውም ሁሉን አድርቶ መንፈስ ገዝቶ ካለዲካ አበርትቶ ሁሉን በመለክ አብራርቶ አብርቶ። መልካሙነን አከማችቶ ህሊናውን አጋብቶ ለጥበቧ ነፍሱን ሰቶ ጊዜ ደጉ አንቶፈንቶን ትቶ ገመናው ጋልልጦ ቁጥቋጦ አሳጥቶ ፍልስ አድርጎ አሰምቶ። የቀና ለት እጬጌው ጊዜ … በስነደዶ ሰብዞ በዛጓሎ አከናንቦ በስንድዷ አሰናድቶ ጥልፍ ሆኖ አስጠልፎ ጥበብ ሆኖ አስጠብቦ ምልዕትን መግቦ። ጊዜ ሆዬ አዘምኖ አዝምንምኖ … ሁሉ ሰጥቶ ብህትናን ለግሶ ፍቅርን ወርቦ ቀድሶ ትንሳኤን አቋድሶ።  እቴ እሱ … አያ ጊዜ ንጉሥ ጊዜ … ሲያስፈልገው ኖን ጋብዞ የሳቀ ለት የስን አሳቅፎ ሥርዬት ሆኖ ነፍስ ዘርቶ ሐሴት ሆኖ ሰናይ ቀብቶ በአናባቢው አስነብቦ ይሸልማል ድሮ ኩሎ ዕሴት ሠርቶ ሰው መሆንን አበጅቶ ባጅቶ። ዐጤ ጊዜ ሲመርቅ … አሜኑን አስቀድሞ በቅኔውም አሳምሮ ማህሌቱን በሚስጢራት አሰድምሞ አሳርጎ ማጫው...

በቦርቅቅ ቀልድ፤

ምስል
የአንባርጭቃ እንፉቅቅ። „ሰነፎች ግን ጥብበንና ተግሳጽን ይንቃሉ።“ (ምዕራፍ ፩ ቊጥር ፯ ) ከሥርጉተ©ሥላሴ (11.07.2018) (ከገዳማዊቷ ሲዊዝ።) ጠቅ ጠቅ ብትክት በቀቅ በበቀን ብርክርክ ሰክሰክ ፍርክርክ፤ ሸክሸክ ቅልሽልሽ ፈቅፈቅ ሽውድውድ፤ ተክተክ ሙርቅርቅ ብቅብቅ በጥልቅ ድብልቅልቅ ጥወልውልልልልልልልል .... ብንብን ትድለቅ ትንትን ትቀልድ በቦርቅቅ፤ የዙርግንብ ያልተገራ ቅጥ የጆፌ ቅይጥይጥ የአንባርጭቃ እንፉቅቅ። ·        ሥ ጦታ ለልቆች ልቅ። ·        ሰ ዓት። መንፈቀ ሌሊት 01.27   ·        ቀን 11.07.2018 ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር! የኔዎቹ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።

እንትንኛ!

ምስል
እንትንኛ! „አላዋቂዎች ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና ሰነፎችም ቸልተኛ መሆን ያጣፋቸዋልና።“ (ምሳሌ ምዕራፍ ፩ ቊጥር ፴፪) ከሥርጉተ ©ሥላሴ (11.07.2018) (ከገዳማዊቷ ሲዊዝ።) እንትንኛ እንቶንኛ የከትከት ሁነኛ። ምንትሶኛ ቅብጥርሶኛ የከትከት ማህበርተኛ። እንቶ ፎንቶኛ ዝልቦኛ ቀበኛ የከትከት ዘበኛ። ቀማኛ መስቃኛ ዕለትኛ የከትከት ዞበኛ። ·        ሥ ጦታ ለልቆች ልቅ። ·        ሰ ዓት። መንፈቀ ሌሊት 01.18   ·        ቀን 11.07.2018 ·          ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር! የኔዎቹ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።

ፍልሶሽ።

ምስል
የዕምል ፍልስ። "እናንተ አላዋቂዎች አስከ መቼ  አላዋቂነትን ትወድዳላችሁ? ፌዘኞች ፌዝን ይፈቅዳሉን? ሰነፎች ዕውቀትን ይጠላሉን?" (ምዕራፍ ፩ ቊጥር ፳፪) ከሥርጉተ ©ሥላሴ (11.07.2018) (ከገዳማዊቷ ሲዊዝ።) ግትልልትትትትትትል ግምልልልልልልልምምል ዝክትልልልልልልትል ልም ግምል። ሁልጊዜም ግትልትል ምንጊዜም ግምልምል የሰርኩ ዝክትልትል የንፈስ ዲል። ልል ብል ዝልዝል ዝል ዝል የዝምብሎ ዕምል። መልምልልልልልል ፍልፍልልልልልፍል ፈረፈር ለፈረፍር ግርግርግገርግር የሸር ግርርርርር የተንኮል ግግር ግርር። ሰፍ! ለተንሳፈፍ ሳፋ ስፍስፍስ በሙቅ ላይ ፍስስ የቅብጥ ቅልጥ ግምስ ቆይቶ ደግሞ አፍልስ። ምስምምስ ምስምስስ ስስስስስስስስ ብልተ ስስ መቋደሻው የሴራ ቡድስ። የተራራ ግርድስ ቡድስ ቡድስድስ የሃሳብ አዟሪት ግንድስ የለጠፍ ቁሮ ቡርድሰድስ የቁልል ቆሞስ ግርድስ። ፍልስ! ·        ሥ ጦታ ለልቆች ልቅ። ·        ሰ ዓት። መንፈቀ ሌሊት 00.57   ·        ቀን 11.07.2018 ·          ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር! የኔዎቹ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።

የኳስ ዊዲንግ ሻውር ምዕራፍ አንድ።

ምስል
ፈረንሳይን ያዬ ዛሬ ። 1 ለባዶ ቤልጀምን። „ምሕረት እና ዕውነት ከአንተ አይራቁ በአንገትህ እሰራቸው።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፫) ከሥርጉተ ሥላሴ 10.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ሜዳው ጭር ብሏል። ትንሽ እንደ ማኩረፍም ድንቡልቡሊት ሆናለች። የሠርጓን፤ ጠመልሱን፤ የቅልቅሉን፤ የማጫውን፤ የዊደንግ ሻወሩን የመረጠቸው ባዕትን ቅዳሜ ምሽት ኮከብህ አልገጠመም ብላ ስለሸኝች። ዛሬ የድንቡልቡሊት ዊዲንግ ሻውር የመጀመሪያው ዕለት ነበር። ምዕራፍ አንድ እንደማለት። ስለምን ሜዳው በጭርታ ተማታ? የራሺያ የዋንጫ መንፈስ ስለኮበለለ። የሆነ ሆኖ የዛሬ እግር ኳስ ጨዋታ የመጀመሪያው ፈረቃ ውድድር ካስን ነው የሚባለው። በዘንድሮው የእግር ኳስ ጨዋታ ራሺያ ጋር የነበሩ ግጥሚያዎች ፉክክራቸው እጅግ ዘመናዊ ነበር።  ከዚያ ውጪ እኔ በተከታተልኳቸው ጨዋታዎች እልህ አስጨራሽ የሚባሉ ነበሩ ለማለት ብዙም አልደፍርም። ኮሎንብያ እና ጃፓኖች ጥሩ ነበሩ። የግብጽና የራሺያ ግን የፋይናል ይመስል ነበር።  የኮራዚ እና የራሽያም እንዲሁ። ድንቁ ነገር የግብጽና የራሺያ ጨዋታ ገና የፊፋ የ2018 ጨዋታ አህዱ በተባለበት ሰሞናት ስለነበር ደረጃው ከጠበቅኩት በላይ ከፍ ያለ ነበር። ግብጽ ሳይቀጥል ቢቀርም እስከ አለፈው ሳምንት ድረስ ራሺያ ባገኘው ልምድ ተበረታቶ በሙሉ ደጋፊዎቹ የጀርባ አጥንትም ተጋዞ በጥንካሬው ቀጥሎ ተወዳዳሪዎቹን በሚያሰድምም ብቃት እያሸነፈ፤ ታዳሚዎችን እያስጨበጨበ ቀጥሎ በኮራዝን እልህ አስጨራሽ እጅግም አስገራሚ ጨዋታ በአገሩ በራሺያ ተስዶ በተመልካችነት እንዲቀመጥ ተገዷል። እርግጥ ነው ያን የመሰለ ብቃት ከመባቻው የነበረው የእኛው ወዛችን አፍሪካዊ መሃምድ ሳ...

እባካችሁን አትበጥብጡን!

ምስል
እኔ ያዬሁት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ  አዲሱን ነው ! ስለዚህም ግንኙነቱ መሠረት ይዞ ትውልድ ፍቅርን  ይወርስ ዘንድ ተግቼ እሠራለሁኝ !          „በነገር እዬተራቀቀ ራሱን የሚያስጠላ ሰው አለ። እግዚአብሄር የዕንቁውን መወደድ አይሰጠውም እና፤ ከጥበቡም ሁሉ ወጥቷል እና፤“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ  ፴፯ ቁጥር፲፱“) ከሥርጉተ ሥላሴ 10.08.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        መቅድም። የመካብራችሁ እንዴት ናችሁ እነ አይታክቴ አሁን ደግሞ የአብይ ገናና መንፈስ ታግለው ታግለው፤ አጣድፈው አጣድፈው፤ መፈናነፈኛ ነስተው አልሳካ ሲላቸው ደግሞ ወደ አዲሱ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ የሰላም የፍቅር ብሥራት ዞር ተብሏል። ስለዚህም እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ዬትኛውም ዓለም እናቶች ጉዳይ ጭንቄ ስለሆነ የእናቶች ዕንባ ስለመድረቁ ጉዳዬም ስለሆነ እተጋለሁኝ። ስለዚህም የኤርትራ እናቶች ደስታና የእኔም ነው። የኤርትራ እናቶች ደስ ብሏቸዋል። እነሱን ደስ ያሰኘው ነገር ሁሉ እኔንም ደስ ያሰኛኛል።  እኔ ስለ ኢትዮጵያ እናቶች ብቻ እምተጋ ቢሆን ኖሮ የዓለም ጉምነት አስጨንቆኝ በ2015 የፍቅርን ተፈጥሮ በመደበኛ ትምህርት ለልጆች የሚሰጥበት ካሪክለም ዓለም መንደፍ አለባት የሚል የአጭር እና የረጅም ጊዜ ትልም የመነሻ ሃሳቦች፤ ሲናሪዮ አዘጋጅቼ ለተባባሩት መንግስታት የዛን ጊዜ ጸሐፊ ለደጉ አቶ ኪምሙን እና ለሌሎችም ባላኩኝ ነበር። በ2017 የጀመርኩት የቃላት ፖስተር ቻናሌም ለዚህው መሠረታው ጉዳይ ነው። እናት የትም ዓለም ትኑር እናት ናት። Sergute Selassie YouTube...