አቤቶ ጊዜ ሲለግምም ሲቃናም ...

ንጉሥ ሆይ! አቤቶ ጊዜ።
„ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች።“
(ምዕራፍ ፩ ቊጥር ፳ )
ከሥርጉተ©ሥላሴ
(11.07.2018)
(ከገዳማዊቷ ሲዊዝ።)

ጊዜ ሲያልፍ ጊዜን ተክቶ
ጊዜ ሲያከትም ራሱን ጊዜን አትግቶ
ግን ሲክድ እራስን አስከድቶ
ሲመጣም ሲሄድም ጊዜ አውክቶ
ተፍነክንኮ ተፈልቀልቆ …
በሰነፎች አሽካክቶ
በልባሞች ተመስጦ
በማስተዋል ተከንድቶ።

ጊዜ ሆይ! የደላው

…. ልግመኛው ባለዱላው
ሲመጣም ሲሄድ የማይደከመው
አይታክቴው ሲያሰኘውም ከትክቶ
ሲያሻውም አንኮታክቶ
በስልት ማጭድ አዘናግቶ
ጌዜ ጌታው ሁሉን ነስቶ፤
ሽው ይላል ኩፍስን አፍንድቶ።

አቤቶ ጊዜ እንዲህ ነው …

… ቅነኛነት ሲያሻውም ሁሉን አድርቶ
መንፈስ ገዝቶ ካለዲካ አበርትቶ
ሁሉን በመለክ አብራርቶ
አብርቶ።

መልካሙነን አከማችቶ ህሊናውን አጋብቶ
ለጥበቧ ነፍሱን ሰቶ
ጊዜ ደጉ አንቶፈንቶን ትቶ
ገመናው ጋልልጦ ቁጥቋጦ አሳጥቶ
ፍልስ አድርጎ አሰምቶ።

የቀና ለት እጬጌው ጊዜ …

በስነደዶ ሰብዞ
በዛጓሎ አከናንቦ
በስንድዷ አሰናድቶ
ጥልፍ ሆኖ አስጠልፎ
ጥበብ ሆኖ አስጠብቦ
ምልዕትን መግቦ።

ጊዜ ሆዬ አዘምኖ አዝምንምኖ …

ሁሉ ሰጥቶ ብህትናን ለግሶ
ፍቅርን ወርቦ ቀድሶ
ትንሳኤን አቋድሶ።

 እቴ እሱ … አያ ጊዜ ንጉሥ ጊዜ

… ሲያስፈልገው ኖን ጋብዞ
የሳቀ ለት የስን አሳቅፎ
ሥርዬት ሆኖ ነፍስ ዘርቶ
ሐሴት ሆኖ ሰናይ ቀብቶ
በአናባቢው አስነብቦ
ይሸልማል ድሮ ኩሎ ዕሴት ሠርቶ
ሰው መሆንን አበጅቶ ባጅቶ።

ዐጤ ጊዜ ሲመርቅ …

አሜኑን አስቀድሞ በቅኔውም አሳምሮ
ማህሌቱን በሚስጢራት አሰድምሞ አሳርጎ
ማጫውንም አዋውሎ
ኪዳን በቃል ወልውሎ።

·       ሰዓት። መንፈቀ ሌሊት 01.55 
·       ቀን 11.07.2018
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።








አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።