እባካችሁን አትበጥብጡን!
እኔ ያዬሁት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ
አዲሱን ነው!ስለዚህም ግንኙነቱ
አዲሱን ነው!ስለዚህም ግንኙነቱ
መሠረት ይዞ ትውልድ ፍቅርን
ይወርስ ዘንድ ተግቼ እሠራለሁኝ!
ይወርስ ዘንድ ተግቼ እሠራለሁኝ!
„በነገር እዬተራቀቀ ራሱን የሚያስጠላ ሰው አለ።
እግዚአብሄር የዕንቁውን መወደድ አይሰጠውም እና፤
ከጥበቡም ሁሉ ወጥቷል እና፤“
(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፯ ቁጥር፲፱“)
ከሥርጉተ ሥላሴ 10.08.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
- · መቅድም።
የመካብራችሁ እንዴት ናችሁ እነ አይታክቴ አሁን ደግሞ የአብይ ገናና መንፈስ ታግለው ታግለው፤ አጣድፈው አጣድፈው፤ መፈናነፈኛ ነስተው አልሳካ ሲላቸው ደግሞ ወደ አዲሱ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ የሰላም የፍቅር ብሥራት ዞር ተብሏል።
ስለዚህም እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ዬትኛውም ዓለም እናቶች ጉዳይ ጭንቄ ስለሆነ የእናቶች ዕንባ ስለመድረቁ ጉዳዬም ስለሆነ እተጋለሁኝ። ስለዚህም የኤርትራ እናቶች ደስታና የእኔም ነው። የኤርትራ እናቶች ደስ ብሏቸዋል።
እነሱን ደስ ያሰኘው ነገር ሁሉ እኔንም ደስ ያሰኛኛል።
እኔ ስለ ኢትዮጵያ እናቶች ብቻ እምተጋ ቢሆን ኖሮ የዓለም ጉምነት አስጨንቆኝ በ2015 የፍቅርን ተፈጥሮ በመደበኛ ትምህርት ለልጆች የሚሰጥበት ካሪክለም ዓለም መንደፍ አለባት የሚል የአጭር እና የረጅም ጊዜ ትልም የመነሻ ሃሳቦች፤ ሲናሪዮ አዘጋጅቼ ለተባባሩት መንግስታት የዛን ጊዜ ጸሐፊ ለደጉ አቶ ኪምሙን እና ለሌሎችም ባላኩኝ ነበር። በ2017 የጀመርኩት የቃላት ፖስተር ቻናሌም ለዚህው መሠረታው ጉዳይ ነው። እናት የትም ዓለም ትኑር እናት ናት።
Sergute Selassie YouTube እሱን ማዬት ይቻላል ወይንም ፓርቶች ስለሚበዙ የተጠቃለሉትን ኮንፓክቱን እና ሳመሪውን sergute selassie - Google plus ማዬት ይቻላል።
- · መነሻዬ።
„ኢሳያስ ኢሳያስ ነው!“ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው።
- · የወግ ገበታ።
ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በነፃነት አረበኛ አስረኞቻችን ላይ ደፋር ዘገባ የሚቀርብ እኔ እንዲያውም የሚሊዮኖች ድምጽ የምለው ጋዜጠኛ ነው። ትጋቱ እና ቁርጠኝነቱ፤ ድፍረቱ እና ወቅታዊነቱ ከማደንቃቸው ወጣት ጋዜጠኞች እንዲያውም የምስጋና ቀን ከሚያስፈልጋቸው ትጉሃን መካከል አንዱ ነው ብዬ አስባለሁኝ። አዎንታዊነት ግን ያንሰዋል።
የሆነ ሆኖ የጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ችግር የመጣው ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ የሹመት እርምጃ ጋር የኢህአዴግ ቀጣይነት በመንፈሱ የተገባውን ቦታ ለመስጠት የተቸገረ ይመስለኛል። ነፃነት ይፍልጋል፤ ለውጥ ይፈልጋል ግን የለውጡን መሪዎች መንፈስ ደግሞ አይፈልግም። ይህን ማስታረቅ የሚችለው ተመክሮ ብቻ ነው። ይህን ማስታረቅ የሚቻለው በተለይ በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ባሉ ሥነ - ምግባሮች ላይ የህግ አፈጻጻም ራሱን የቻለ ልዩ ኮርስ መውሰድ ሲቻል ብቻ ይመስለኛል።
ይህም ብቻ ሳይሆን ወጣትነትም በራሱ ፈተና መሆኑን ለጋዜጠኝነት ህይወት እያስተዋልኩኝ ነው። ሁሉም ጋዜጠኛ የፖለቲካ ጋዜጠኛ ነውና። ወጣት የፖለቲካ ጋዜጠኛ ለመሆን ሲታሰብ ከወጣትነት ጋር ተፋቶ እንደ አንድ ሙሉ ዕድሜ ላይ እንዳለ ጎልማሳ ለመሆን መወሰን፤ መቆረጥ ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ ጋዜጠኛ ደረቅ መሆን የለበትም። ግትር የሆነ አቋም ለጋዜጠኝነት ህይወት የሙያውን ለዛ ያደርቀዋል፤ ቃናውን ያጠነዝለዋል፤ ያፈልሰዋልም።
አብሶ በወጣትነታቸው ትልቅ ሃላፊንት የሚወስዱ ወጣቶች በመጀመረያ ሊያደርጉት የሚገባው ቁም ነገር የወጣትንት ካባቸውን ማውለቅ አለባቸው። ከምንም ጋር ንክኪ የሆኑ ጉዳዮችን ሁሉ ጋር መፋታት አለባቸው። ወጣትነት ጠቀሜታ ቢኖረውም ፈተናም አለበት። ዕድሜው እራሱ የሚፈጣረው ተጽዕኖ። ከአንድ የድርጅት አባል ለቀህ ወደ ሌላው ስተገባም ያው ተከትሎህ ስለመትመጣ ያው ባለዬለት የጎሸ የስሜት ወገሚት መናጥ የግድ ይሆናል።
ችግሩ አብሮ የሚታመሰው የኢትዮጵያ እናቶ ዕንባ መሆኑ ነው። ከእነኝህ ነገሮች መታረም ካልተቻለ አንድ ስንዝር መራምድ አይችሉም እንደዚህ እጣጫ ቢስ እምስ ቁሊቶች፤ በዬፌርማታው ይንጠባጠባሉ። የወቅት አታሞ ከፍ ብሎ ሊደምቅ ይችላል፤ ግን ውሎ አድሮ ጭብጨባው አስጨብጭቦ ያጨበጭባል።
ምክንያቱም በልምድ፤ በተመክሮ፤ በዕድሜ፤ በዕውቀት፤ በመክሊት እና በጸጋ የሚበልጧቸው ሰዎች በሥራቸው እንደ አንድ አድማጭ እንደ አሉ አውቀው ማዕከላዊ የዕድሜ የአስተሳሰብ መንፈስን አምጠው መወለድ አለባቸው። ወጣቶች ወደ አንድ የህዝብ ሃላፊነት ራሳቸውን ሲያመጡ፤ አክቲቢስትም፤ ጋዜጠኛም፤ ተንታኝም፤ መሪም ሲሆኑ። ያ ካልሆን ባይጀመሩት ይሻላቸዋል።
ችግሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን መንፈስ ወደ ማዕከል ማምጣት የሚያስችል ክህሎታዊ አቅም ያለው ተቋም የለም ሥርዓቱም አይፈቅድም። ሥርዓቱ የሚፈቅደው እንዲህ አራባ እና ቆቦ የሚረግጥ መንፈስን መፍጠር ብቻ ነው። ውጪ አገርም ቢታሰብ አውሬው የፖለቲካ መንፈስ አያወላዳም። እኔ የወጠንኳቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ።
ለምሳሌ በቀን አንድ ብር ያሉትን ጠ/ ሚር አብይ አህምድ እኔ በወር አንድ ብር አንድ አክስዮን ለማቋቋም ሁሉ ነገር ከተሰናዳ በኋዋላ በዛው ቀን እዛው አዳራሽ የግንቦት 7 ስብሰባ ተጠራ። 8ክለብ በአንድ ማህበር ነበር እርእሱ „ቁራሽ እንጀራ“ ይል ነበር። ክለቦቹ „ብራና ርትህ ጉልማ“ ወዘተ ይባሉ ነበር … በኋዋላ አማራ ሚዲያ „ብራና“ የሚል ሥም ይዞ ወጥቶ ነበር። እኔ ግን ከተጋድሎው በፊት ያወጣሁት ሥም ነበር ለሥነ ጥበብ ዕድምታ ክለብ።
ለዚህ ማህበር ነፃ የህግ ባለሙያ፤ ነፃ ፕሬስ፤ ነጻ የራዲዮ አዬር ጊዜ፤ አባል የሚሆኑ የሌላ አገር ዜጎች ሁሉ አግኝቼ በመንግሥት የታወቀ አካል ዓመታዊ ጉባኤ አዳራሽ እና አማካሪ መድቦልኝ በቃ መክኖ ቀረ።
ኪዚህም ሌላ ልጆችን በጋዜጠኝነት ሙያ በ2006/8 ማሰልጠን ጀምሬ ሁሉ ነበር … ከዛ የወያኔ ሃርነት አይፈቅድም ከዚህ ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ትውልዳዊ ተግባራትን ለመከወን ተቋማትን ለመፍጠር ግንቦት 7 አይፈቅድም፤ ቢጀመር እንኳን ከሦስት ተርትረው ያምክኑታል፤ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ካልቻሉ፤ ከበተኑ በኋዋላ ጠንካራዎችንም ወደ ራሳቸው ያደርጋሉ። ከፍርሰቱ እኔ ግን ብዙም ሳልደክም ወዲያውኑ አቆምኩት፤ ይሄን ነበር ተሜ ናፈቀኝ ሲል አንድ ቃለ ምልልስ ላይ ያደመጥኩት … አሁን ፈጣሪ ታድጎናል …
- · አጋጣሚ እና ስጦታ።
በሌላ በኩልም በፖለቲካ ህይወት ለሚፈቅዱት አጋጣሚውም ስለማይፈቅድ ይመስለኛል። አሁን አኔ የታደልኩ ስለነበርኩኝ ምራቃቸውን የዋጡ አለቆች ነበሩኝ። በዛ ዘመን የአገር ውስጥን ንግድ ሚኒስተር ቋሚ ተጠሪ የቅርብ አለቃዬ ሆነ። ገና ሲዬኝ ነበር ቀልቡ ያረፈብኝ። አብሬ ለመሥራትም ዕድሉ ገጠመኝ። እጅግ ጠንካራ ሠራተኛ hard worker, clever, decent ነበር። ከእሱ ጋር በመሥራቴ ከጓድ ገ/ መድህን በርጋ ወጣትነቴን ሳላወቀው ነበር ያለፈው። ሥራ አገር ነው የሚሆነው። እንዲያውም አንድ መጸሐፌ ላይ መተለላፌን ጽፌዋለሁኝ ከወጣትነቴ ጋር። አላውቀውም ወጣትነት ምን እንደሁነ።
የማውቀው ሠርቻ የማልደክም፤ ጥራት፤ ብቃት፤ ፈጠራ ያለው ተግባር ለመከወን መታተሬን፤ ለማወቅ የነበረኝ ጉጉት፤ የሚሰጠኝን ሁሉ በህሊና ለማብቀል የነበረኝ ተነሳሽነት፤ ዝግጁነት፤ አጋጣሚዎችን ላለማሽሎክ የነበረኝ ጥረት ነው።
በግል ህይወቴ የቀረቡኝ የገሃዱ ዓለም ጉዳዮች ቢኖርም በህሊናዬ ግን ቀረብኝ የምለው አንዳችም ነገር የለም። ዩንቨርስቲም ብገባ ከዚህ በላይ ሊሄድ ስለማልችል። ባላ አቅም እና ችሎታ አለቆቼ ሁሉንም ሰጥተው ስላሳደጉኝ አብቅለውኛል፤ አጸድቀውኛል፤ ፖለቲካዊ ህይወቴን አንጸውታል። ጓድ ገ/ መድህን በርጋ፤ ጓድ ወንደወስን ሃይሉ፤ ጓድ አበባ በዳዳ፤ ኮ/ አሰፋ ሞሲሳ፤ ጓድ ስለሺ መንገሻ፤ ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ደክመዋል ስለ እኔ ፖለቲካው የብቃት ሰብዕና።
ፓርቲዬ ኢሠፓ የሚኳራብኝ በሞራልም፤ በቁጥብነቴ ብቻ ሳይሆን ሃላፊነትን በወጣትም ሆነ በተገኘሁበት ቦታ ሁሉ ምስክርነታቸውን የማላሳፍር በመሆኔም ጭምር ነው። ወጥ አቋም ነበር የነበራቸው። ቀጥ አድርገው ነበር ያወጡኝ። ያስተማሩኝ አዎንታዊነትን፤ ሥራ እና ቅንነትን ብቻ ነው። አሁንም አያልቅብኝም። ስለምን?
ዕድሉ ገጥሞኝ ከመልካም ሰዎች ጋር በቅርበት ስለሰራሁኝ። አሁን የእኔን ዕድል ያለገኙት እና እኔ በዛ ዘመን ከነበርን ወጣት ፖለቲከኞች የእኔ የአቅም አገነባብ እና የእነሱ ፍጹም የተለዬ ነው። ያዘለቀኝም ይሄው ነው። ሌላው ቢቀር ድፍረቱን፤ ጽናቱን፤ በራስ መተማመኑን ቤት ውስጥ ሳድግም ቤተሰቦቼ የቤት ሥራቸውን ሠርታዋል ያም ነበር እርሾው፤ እርሾውን ወደ ህሊና እንጀራ የለወጡት ደግሞ አለቆቼ ነበሩ።
እኔን በእኔ ውስጥ አደራጁኝ። በተለያዬ ኮርሶች፤ ሰሚናሮችም፤ ሃላፊነቶችም በማሰማራት የበለጠ ነጥሬ፤ ሠልጥኔ እንድወጣ አደረጉኝ። መኖሬን ተቋም ፈጠሩለት።
የዛሬ ወጣቶች ይህን ዕድል አላገኙም። መማር ብቻውን ፖለቲካ ሳይንስ ምንም ነው። ዲግሪ ቢኖርህም። ስለምን? ዲግሪ ያላቸው የፖለቲካ ሳይንስ ወጣት ሙሁራን የአብይን የለማን የገዱኑን መንፈስ ቀድመው ለመረዳት አቅማቸው ስስ ነው በጣም ስስ። ምክንያቱም ንድፈሃሳባዊ ትምህርት መሬት ላይ ወርዶ ተግባራዊ ሊሆን ሲችል በቅርበት በተመክሮ የበቀሉ መሪዎች ካልገጠሙ ወና ነው የሚሆነው።
በሌላ በኩል ዕድሜ ልኩን በፖለቲካል ሳይንስ ያስተማረ ግን የቀበሌ ሊቀመንበር ሆነ ህዝባዊ አገልግሎት ለመሰጥት ዕድሉን ያለገኘም ከሆነም ያው ነው ….
መማር አንድ ተፈላጊ ነገር ነው። ሁለተኛው የተማሩትን በተማሩበት ሙያ መሬት ላይ መሥራት ሌላ ጉዳይ ነው፤ ሦስተኛው የቅርብ አለቃ ወሳኝ ነው። አራተኛው የራስ ሰብዕና ማንነት እና ያደጉበት ቤተሰብ፤ የኖሩበት ማህበረሰብ አካባቢ እነዚህ ሁሉ አስፈለጊ ነገሮች ናቸው።
ከዚህ ውጪ እንደ ተመረቀ ውጪ አገር ለሚወጣ አንድ የፖለቲካል ሳይንስ ምሩቅ ባለበት እንዲረግጥ ይሆናል። ማህበራዊ ትስስሩ ተቆርጧል። ለዚህ ነው አንድ ሊሂቅ - አንድ ተንታኝ - አንድ ሚዲያ - አንድ ጸሐፊ ቀድሞ ይህን ዘመን ይመጣል ብሎ ለማሰብ ያደገተው። ሌላው እያወቁም የሚበልጥን ለመቀበል መሳን የልግመኛው የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፈተና ነበር። እያዩ አለዬነም አልሰማነም ማለትም አለበት።
ከዚህ ሌላ ሰዎችን ፖለቲከኛ የሚያደርጓቸው፤ ጋዜጠኛ የሚደርጓቸው ሳቢያዎችም ሥር ሰደድን ፍላጎት፤ ክህሎት፤ ዲስፒሊን ጋር በቅጡ ሳይዋህዱ ስለሚሆኑ አደጋው ሰፍቶ ይታያል። በኢትዮጵያ ያለው መከራም ይሄው ነው። አንድ ቲያትር ትተውናለህ ከዛ ላይ ትውጣለህ፤ አንድ ጹሁፍ ትጽፋለህ ትታሰራለህ ሽልማት ይጎርፋል ከዛ አንተ ሌላ ሰው ነህ። ይሄን ለመግራት ብዙ ተግባር ከፊት ለፊት አለ። አንድ በበቀለ መኖር ውስጥ ያለ ሰብዕና ለደቂቃ የሚያገኘው ሰው ሁሉ ለመማር የሚፈቅድ ሰው ከተገኜ ተምሮ ይሄደብታል።
ከጠቅላላ አለባብሱ ጀምሮ ምርጫው የተለዬ ነው፤ የቤቱ አደረጃጃት የተለዬ ነው በእንግድነት የመጣው ሰው ያን ቀድቶ ወዲያውኑ የእሱ ለማድረግ ይታትራል። ስለምን? ከውስጥ የበቀለ የሰለጠነ ብቁ ማንነት ስላለው እስተናጋጁ። በሥራ ልምድ ውስጥ ከበሳል ሰዎች ጋር መሥራት ጠቀሜታው ይሄው ነው። አሁን አገር ቤት ያሉ ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጋር የመሥራት አጋጣሚ ያገኙ ሰዎች ሁሉ ይህን ዕድል በወጉ ሊጠቀሙበት ይገባል። ዘርክራኮቹ እንኳን ቢሆኑ ይሻሻላሉ።
አሁን ሽግግር ላይ ስለሆን ምንም ላይመስለን ይችላል ግን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ኢትዮጵያ ስትመጣ ግን ታዩታላችሁ። ይሄ አሁን የምታዩት ቅርንጫፍ ነገር ነው። ከሥር መሠረቱ ትውልዱ በዚህ መሰል ሁለገብ፤ ሁለንትና ብቃት ለማብቀል ያለመ ነው የአብይ መንፈስ። ጓድ ገ/ መድህን በርጋ የአገር መሪነት ደረጃ አግኝቶ ቢሆን ኖሮ ይህን መሰል ተግባር ይከውን ነበር። ማብቃት ነበር መርሁ። ሲያበቃ ደግሞ ከግል ህይወት ጀምሮ አብቅሎ አደራጅቶ አጠንክሮ እንደ ብረት ነው።
የጠ/ ሚር አብይ አህመድን የማብቃት አቅም ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የተመሰጡበት ይመስለኛል። ይህም ልባምነት ነው። ይህን እንዲወርስ የፈቀዱ ይመሰልኛል ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ከልጃቸው ጋር ጓደኝነት እንዲኖር የመጀመሪያውን እርምጃ ለመወስድ የተገደዱት። አብይ ልጄ ቢሆንልኝ የማለት ህልም ሁሉ በዚህ የቤተሰብ ግንኙነት አይቻለሁኝ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ።
ለወደፊት ከሳቸው ይልቅ ልጃቸው ይህን ልምድ እንዲያበቅል ያደርጋሉ ብዬ ሁሉ አስባለሁኝ። ረጋ ያለ፤ እንደ ባህሉ ለመኖር የፈቀደ ወጣት ነው ያዬሁት ልጀቸው። በጣም ነው የተመሰጥኩበት። እኔ ውስጥን ነው የማዬው። አሁን የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ዋና አንኳር ጉዳይ ልጃቸው እና ዶር አብይ አህመድ የጠበቀ ትስስር እንዲኖራቸው፤ የልምድ የተመክሮ ሁኔታ እንዲመቻችለት ሊያደርጉ ሁሉ ይችላሉ። ጠብቁት። ይህን ሃብት ኢትዮጵያ ያለው ጋዜጠኛ ማምከን ይሻል ሌላው ደግሞ በዬት ባገኘነው ይላል።
የሆኖ ሆኖ እኔ የኢሳቱን ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙን ስሞግት በዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጭንቅላት ውስጥ ብሄራዊ ቀን የሚያስውስን ቁምነገር አለ ያልኩት እንዳትረሱት፤ ኢትዮጵያዊ ማርቲን ሉተርም ነው ብያለሁኝ። ለእኛ ብቻ አይደለም ለውጪ አገር መሪዎችም እንዲህ ብዬ ጽፌያለሁኝ። አብይ ኬኛን ክፍል ስድስትን ማጠቃለያውን እዚኸው ስላለ ማንበብ ትችላላችሁ።
- · ተንሳፋፊነት።
ዛሬ በሁሉም ዘርፍ የሚታዩ ጉዳዮች የተንሳፈፈ ዕውቀት ስለሆነ አቋሙም፤ ውሳኔውም የተነሳፈፈ ነው። ወረቀት ላይ፤ አዬር ላይ፤ ሞገድ ላይ እና መሬት ላይ ያለው ዕውነት የተለዬ ነው። ያ የሚታወቀው ታች ከህዝብ ጋር የቀበሌ ተመራጭ ሆኖ መሥራት ሲጀመር ነው። አከብረን መነሳት እንኳን አልቻልነም።
አንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ „አንተ እና አንቺ“ እያለ ነው የሚወያዬው፤ እሰቡት አንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ? ጀርመኖች ይህን ቢያውቁ ምን ይታዘቡን? የአክብሮት እራሱን የቻለ የስዋሰው ደንብ እና ህግጋት ስላላቸው። ፊደሎቹ የአክብሮት በትልቁ ነው የሚጻፉት።
አሁን አንቺ እና እርስዎ Sie // sie። አክብሮታዊ ርባታም ይሉታል። እኛ ግን ከከበረ ከሰነቀ ከደረጀ ከትፊውታችን ወጥተን ስለ ጠላነው ብቻ እንቺና አንተ የተለመደ ነው።
ለዛውም ዲግሪውንም ተሸክመን፤ መምህርም ተብለን ነው። አልጀመርነውም የታታሪነት፤ የተንታኝትን የጋዜጠኝነትን አስተምህሮ።
ወደ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሸፈራው ስመጣ … ጹሑፉን ብቻ ነው የማነበው፤ በአካል አላውቀውም። የማይደክመው ታታሪ መሆኑን ግን እረዳለሁ።
አሉታዊ ዘመም መሆኑም ከስሜቱ ጋር የቀረቡ ነገሮች ያገኜ አይመስለኝም በለውጡ። እሱ 12 ሐዋርያት መሬት ላይ እንዲወርዱ ያለመ ይመስለኛል። ይህ ከእስር የተፈቱት ሁሉ የሚጋሩት መንፈስ ነው። እንደ እኔ ሁሉንም አቅም ቢፈትሹት ግን ሱባኤ ይገቡለታል ለዚህ ቅዱስ ዘመን። ከዴሞክራሲ በላይ ነው። ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ቤተሰብኛም ነው።
- · ምልሰት።
…. ወጣቶች ሚሊዬነም አዳራሽ ሲጠሩ „አብይ ደክሞታል፤ የሰንበት እረፍት አሰኝቶታል ኑልኝ ከዚህ ብሏል ከእንግዲህ ወደ አማራ መሬት አይሄድም“ ብሎ ጻፈ፤ ጎንደር ሲሄዱበት ደግሞ „የጎንደር ህዝብ አብይ እዬተናገረ አደባባዩን ጥሎ ሄደ፤ አብይንም እነ ገዱ ሹልክ አድርገው ጎሓ ወሰዱት“ አለን፤ ማዕከላዊ ሲዘጋ „አልተዘጋም አለን፤“ በሌላ ጊዜ ደግሞ „መተቸት መብቴ ነው መደገፍ ገዴታ የለብኝም“ አለ … ሌላም ሌላም ሌላም … አሁን ደግሞ „ኢሳያስ ኢሳያስ ነው“ ይለናል።
በዛን ሰሞን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቦሌ ላይ የትኬት ይለፍ ዘበኛ እንዲሆኑ፤ ለእነ ኦቦ በቀለ ገርባ ደግሞ አሜሪካ ኢንባሲ የቢዛ ሠራተኛ በመሆን አገልግሎት እንዲያበረክቱ ነበር የተፈለገው። ወዲያው ደግሞ „ጋዜጠኛ አስክንድር አምስተርዳም ገባ፤ ኦቦ በቀለ ገርባ ቢዛ ተመታለት“ ቀጠለ … ስክነት የነሳው መንፈስ ... መጋለብ ብቻ …
የሆነ ሆነ ያ ሲያብጠለጥለው የከረመውን የአብይን መንፈስ በሌላም አጋጣሚ በባህርዳሩ ህዝባዊ ጉባኤ ከምን መነሻ የሽግግር መንግሥት ጥያቄ እንዲነሳ መደረጉን ሥርጉተ ሥላሴ አስተርጓሚ አትሻም። ምንጩን አሳምራ ስለምታውቀው። አሁን ደግሞ ቅንነት መፈጠሩ የታወጀበት ዕለት ነበር ኤርትራ ላይ የነበረው ቅዱስ መንፈስ። ያን ለመበከል ደግሞ ይህቺን ጫሪ ሃሳብ አንስቷል። ለምን እንታረቃለን የሚሉ ወጣቶችን ደግሞ ከሆነ ስበሰባ ላይ እንዲነሱ ይደረጋል። ወይም መፈክር ይዘው እንዲወጡ። ይሄው ነው አቅማችን የነፃነት፤ የፍቅር፤ የሰላም የእናቶች እንባ መቆም አሳቢነታችን።
- · ሰላም የወል እንጂ የተናጠል ትርፍ አይደለም።
ሰላም በአንድ ሰው ጥረት አይመጣም። ፍቅር በአንድ ሰው ጥረት አይገኝም። ቅንነት በአንድ ሰው ጥረት አይገኝም። አዎንታዊነት በአንድ ሰው ፍላጎት አይገኝም። እኔ ሁሉንም ማድረግ የሚያስችል አቅም ነበረኝ። ግን ተሰካልኝ? አልተሳካልኝም። ሳልችል ስቀር መጸሐፍ ጻፍኩኝ። እሱም መጋዝን ያሞቃል። አቅሜ ባክኖ ነው የቀረው። የአንድ ጥሩ፤ የአንድ ሰው ቅንነት፤ የአንድ ሰው ፍቅር ፈላጊነት አድማጭ፣ አጋዥ - ረዳት - ተቀባይ - አብቃይ ካላገኝ ምድረበዳ የበቀለ ዕጽዋት ነው። በቃ። ደርቆ ነው የሚቀረው።
የገዱ መንፈስ የለማን መንፈስ ተቀብሎ በቅንነት ባያስተናግደው ዛሬው ይህ ሁሉ ድል ኤርትራን፤ የአፍሪካ ቀንድን፤ የመካካለኛው አፍሪካን ዓለምንም ያስደሰተ ውጤት አይገኝም ነበር። የተባበሩት መንግስታት የወቅቱ ጸሐፊ እኮ ለሁለቱ መንግሥታት የሚጠይቁትን ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርግ ገለጸ። ነገ ተሸላሚዎች ናቸው ሁለቱም።
ይህን ያደረገው የገዱ መንፈስ የለማን መንፈስ ፈቅዶ ሳይጠራጠር ስለመቀበሉ ነው። የለማ መንፈስ ይህን ያደረገው ደግሞ „የኦህዴድ ሞተር ማን ነው?“ የሚለውን የቅኑ ጋዜጠኛ ፍቅር ስንታዬሁን ጹሑፍ የጋዜጠኛ ሃኒ ሰለሞንን የቀደሙ ጹሑፎች ስታነቡ የለማ መንፈስ የአብይን ቅን መንፈስ ለመቀብል፤ ዕውቅና ለመስጠት፤ ወደፊት ለማምጣት የፈቀደበት መንገዱን ምንጩን ታገኛላችሁ።
https://www.facebook.com/afaanoromoline/posts
የጠ/ ሚር አብይ አህመድን ቅንነት፤ ፍቅር፤ ሰላም ፈላጊነት፤ ንጽህና ለመቀበል ባይፈቅዱ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ማን ጌታ ነበረባቸው። ማን ያስገድዳቸዋል? እሳቸውም እኮ ፍቅር - ቅንነት - ንጽህና ተፈጥሮላቸዋል ልክ እንደ እኛ፤ እንደ ማንኛውም የሰው ልጅ። ስለዚህ ግጣማቸውን ሲገኙ ያን ተፈጠሯቸውን ፈቀዱለት። የተከደነው ሰብዕናቸው አደባባይ ወጣ። እናም ሆኑበት እናም አማራባቻው። ሳቃቸውን አገኙት። ከውስጣቸው ጋር ተደመሩ!
ያለፉትን ነገሮች እኛ ከምንቆሰቁሳቸው፤ ያለፉት መለዬቶች እንዲህ በፍቅር በንጽህና እንዲመጡ ህዝቡ መልስ ሰጥቶበታል። ያን ያዬ የዓለም ህዝብ ኤርትራ ሄዶ ህዝቡን ለማዬት የማይጓጓ ማን ነውና? ፍቅር እኮ በእግሩ ቆሞ ሲሄድ አይተናል። መሪው ባይፈቅዱ ጠበንጃ ቢደግኑ፤ አትወጡ ባይሉ ይቻላቸዋል። መብት አላቸው።
እኔ ባዬሁት ነገር ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ዘመን የተጫነው ቅንነት እንዳለቸው ተረድቻለሁኝ። ቤተሰባዊም ናቸው እኮ። ቤተሰባዊነት ደግሞ የአብይ መንፈስ ልዩ መለያ ነው። ይህ መንፈስ በመሯቸው ቦታዎች ሁሉ መጀመሪያ የሚያሰፍነው ይህንኑ ነውና። እህቴ እዚህ ስትመጣ አዝናለች። በተለያዬ ሁኔታ በአጋጣሚ መጠቃት በራሱ ብቻ መሆንን፤ መገደምን ያስመኛችኋዋል። እኔ ቤቴ ለሚያደሩ 10 ጓደኞቼ አስር ትራስ እና 10 ፒጃማ ዬራሳቸው ነበረኝ።
ከጓደኞቼም ስሄድ ሠራተኞቻቸው ግቢውን ሲክፉቱ መጀመሪያ የሚያደርጉት ፖርሳዬን ተቀብለው መቆለፍ ነው። እንድሰነብት። ግን ሲዊዝ ስመጣ ሁሉም ነገር ተቀዬረ። የምቀርበው ሁሉ የመጀመሪያው መታመኑን ይቆረጥማል፤ በመቀጠል ልቡን ገጥሞ እንዳሻው ማድረግ ይፈልጋል፤ ነይ ሲለኝ እንድሄድ አትሂጂ ሲለኝ እንድቀር፤ የራሱ የግል ዕቃው ማድረግ ይሻል፤ ይህ ደግሞ የማይሆን ህልም ነው።
አንደኛው አፈጣጠሬ ወጣ ያለ ነው፤ ሁለተኛው አስተዳደጌ፤ ሦስተኛው የተመክሮዬ ሁኔታ፤ አራተኛው የመክሊቶቼ ዓይነት፤ አምስተኛው ቁጥብነቴ በጠቅላላ የሰብዕና አገነባቤን አይውቅም ሰው የተከደንኩ ስለሆንኩ። እና ዘሎ ቁብ ማለት ይመኛል።
ስለዚህ ዘግቶ መቀመጥ ግድ አለ። አሁን ፕ/ አሳያስ አፈወርቂ የገጠማቸው ይሄ ይመስለኛል። በረጅም ጊዜ በትጥቅ ትግል፤ በደህንነት ውስጥ መሥራት ራሱ ደግሞ ሲጨመርበት ሰብዕናውን የማይደፈር አደረገው እንጂ እኔ ከዶር አብይ አህመድ ጋር የነባራቸው የአቀራረብ ሁኔታ በዬትኛውም ዓለም ያሉ መሪዎች ያለደረጉትን የመሪነት የቤተሰባዊነት ሁኔታ ነው ያሳዩት።
ተነስተው ሁሉ አስተናግደዋቸዋል እኮ። መንገድ ለጠበቃቸው ህዝብ አብረው እያጨበጨቡ ተቀላቅለዋል፤ የታናሽ ወንድማቸውን እጃቸውን እንዳያምልጧቸው እንደ አዲስ ፍቅረኛ ጥብቅ አድርገው ይዘው እኮ ነው ሲራመዱ የነበሩት። ሲሾኟቸው ከእናት በላይ ነበር ተመስጧቸው። ደህና ድረስልኝ ወደይዓይነት።
ይህን ፍጹም ቅን፤ ፍጹም ርህርህናው የሚገዛ፤ ንጽህናው ጥልቅ የሆነን መንፈስ የትሜና ጣሉት፤ አታቅርቡት፤ አታስጠጉት፤ እያለ ነው የሚሰብክ የማከብረው ጋዜጠኛ ሽፈራው ጌታቸው። አደራ አትስሙት! አታደማጡት!
አብሶ የአማራ ወጣት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ሰላማዊ ሁኔታ የሚያተርፈው አማራ እና ቀዬው ነው። ስለምን ከፋኝ ያለው ሁሉ 43 ዓመት ሁሉ የራሱን ወገን ቀዬ ቆጥቦ ሲነደው የነበረው አማራ እና የአማራ መሬትን ነበር እና። ስለዚህ ለአማራ የአሁኑ የሰላም ሂደት ሜሮኑ ነው። እኔም የአዲሱ ቅናዊ መንፈስ ቤተኛ ነኝ! ስለትናንት ሰቀቀን አይደለም የተፈጠርኩት።
እኔ የተፈጥርኩት ስለተስፋ ነው። በጸጋዬ ድህረ ገፅም፤ በፀጋዬ ራዲዮም ሁልጊዜ ስለተስፋ መቅድም ነበር። እርእሰ አንቀፄ ተስፋ ነው። ስለዚህ ተስፋዬን ለሚቀማኝ ማናቸውም ሃይል አልተኛም። አሁን ደግሞ ሥርጉተ ሥላሴ ኢሳያሳውያን ሆነች እስቲ ምን ቁርጥ … በጎነት መልካምነት ቅንነት ባለበት ቦታ መኖር ለእኔ እዮራዊ ነው …
- · መከረኛው ቋንቋ።
ኦቦ ሌንጮ ለታ ከኢሳቱ ገዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ በእንግሊዘኛ ነበር ውይይቱ የተካሄደው። ከግንቦት 7 ጋር ትንሳኤና ህይወት መሆን ሲያማራቸው ደግሞ በአማርኛ፤ አሁን ኢትዮጵያም ሲገቡ በአማርኛ ነበር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ የሰማኋዋቸው።
ኤርትራ ብሄራዊ ቋንቋዋ ትግረኛ እንጂ አማርኛ አይደለም። ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ ፕሬዚዳንት እንጂ የኢትዮጵያ አይደሉም። በአማረኛ ምኔ ብለው እንዲናገሩ ይሆን የሚፈለገው? የጀርምን ካንሰለር እኮ አሜሪካ ሄደው በጀርመንኛ ነው ንግግር የሚያደርጉት። ኤርትራ እኮ ልዑላዊት አገር ናት። ዓለም የሚያውቃት።
ኤርትራ ዜጋ አላት ኤርትራውያን የሚባሉ። የራሷ ሁለመና አላት ኤርትራ። ኤርትራ ላይ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ የለም። ይህም ማለት አማራ ኗሪዎች የሉም፤ አማርኛ ቋንቋ የሚናገሩ የሉም ማለት አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ቻይንኛ፤ ቱርክኛ፤ አረብኛ የሚናገሩ ኗሪዎች ይኖራሉ እንደዛ ነው።
አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ፕሬዚዳንትነታቸውም ለኤርትራ ነው። እንዲያውም እሳቸው እንደ ቼጉቢራ ናቸው። ትውለድ ኢትዮጵያዊ ግን „ለኤርትራ ነፃነት“ የታገሉ። የታሪክ መሠረት አለው የኤርትራ ጉዳይ። በጣሊያን በእንግሊዝ የቆዩበት ሁኔታ ስላለ።
ከመረብ ወዲህና ወዲያም ያሉ ወቅትና ታሪክን የሚያሳድሙ እጅግ ብዙ ታሪካዊ ኩነቶች የተከወነበት ምድር ነው ኤርትራ። ቃለ ወንጌልን ጨምሮ። ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያዊው ቼጉቢራ በኤርትራ ናቸው። ከዚህ ቀደምም እንዲህ ብዬ ጽፌ ነበር።
በቀደመው ነገር ከአንተ ይልቅ እኔ መደበኛ የፖለቲካ ሠራተኛ ሆኜ አውቀዋለሁ። ያ አልፏል። ምዕራፉም ተዘግቷል። አሁን ዘመን የሰጠነን ባትለዬን እመርጣለሁኝ። መጸሐፌ ላይ ያው ካርታ የነበረው ነው። ፍቅር ስላለ። በፖለቲካ የነበረው እስጣ ገባብም ነበርኩበት። አሁን ደግሞ ታሪክ ሌላ ዕድል ሰጥቶናል። ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ መመለስ የለብንም። በፍጹም።
ከጅምሩም በቅንነት ነው እሺ ያሉት። ሴራ የለበትም። ምቅኝነት የለበትም። የበላይነት የለበትም። ቅናት የለበትም። ውጪ አገርም አይረብሹንም ኤርትራውያን እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ። እኔን በጥብጠውኝ አያውቁም። ሳድግ ደግሞ አብሬ ነው ያደግኩት።
- · ማወክ ፍቅርን ቁጣው የሰማይ ነው።
የሆነ ሆኖ አሁን በመልስ ጉዞው ኢትዮጵያ ለጉብኝት ሲመጡ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አማርኛ ቢናገሩ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሽፈራው ምን ሊል እንደሚችል ማዬት ነው። ሌላው የኤርትራ ሉዑካን በቤተ መንግሥት በነበረው የራት ግብዣ ላይ የፌድራል ምክር ቤቱ ክብርት አፈ ጉባኤ ወጣቷ ፖለቲካኛ በትግረኛ ነበር የተናገሩት፤ ታዳሚው በሙሉ አማርኛ ቋንቋ አድማጭ ነው።
አማርኛ ቋንቋ የፌድራሉ ኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ ነው። ከኤርትራ ከመጡትም ውስጥ የቅርብ አማካሪው የፕ/ እሳያስ አፈወርቂ አማርኛ ተናጋሪ ናቸው፤ ሁለት የልዑካን ቡድን ብቻ ነበሩ አማርኛ የማይናገሩት። በፆታቸውም የመላ ኢትዮጵያን ሴቶችን አንደበት የወከሉት የፌድራል ምክር ቤቷ ክብርት አፈ ጉኩባኤዋ ግን በትግረኛ ነው። ስለምን እንዴት? ለታሪክ መተው ነው።
እኔ እንዳዬሁት ኤርትራ ላይም የቀረበ አያያዝ እንደነበረ ተመልክቻለሁኝ። እኔ ሁሉን ሥራዬ ብዬ ስለማስተውል። መቀራረብ መልካም ነገር ቢሆንም ቡድኑን በእኩል መንፈስ ማስተናገድ ግን ይገባል። ከልዑኩ ጋር ሁለቱም አንስት ናቸው። ለሁሉቱ እኩል ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ለወደፊት።
ይህን ሁሉ ታግሰን ማለፍ የሚገባው ፍቅር ከጠማን ብቻ ነው። ፍቅር እኮ ጥማትም እራህብ ነው። እዚህ ያሉ ኤርትራውያን ጦርነት ብትገጥሙን ሄድን አቶ ኢሳያስን እናግዛለን ሁሉ ብለውኛል። ፍቅራቸው ግን ልዩ ነው። አንድ ጊዜ ጽፌያለሁኝ ኤርትራውያን ለማህበራዊ ኑሮ እና ለጉርብትና ያላቸውን ክብር። ዘመን፤ ታሪክ ነው የበደለን። አሁን ደግሞ መለያዬታችን በወጉ መሆኑ የስለት ልጅ ያህል ልንከባከበው ይገባል። አይዞህ ልንለው ይገባል።
- · ማቁሰል።
ብዙ ነገሮችን ቁስል እንዲነፈርቅ መፈለግ መግል መልሶ መቁሰል ነው። ልክ የነፈስ በላው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ደብዳቢዎች እንደሚያደርጉት አቁስለው በቁስሉ ደግሞ እዬጠሩ፤ እዬረጋገጡ እስረኞችን እንደሚያሰቃዩት፤ እንደሚሳለቁት። እኔ እኮ ወንድሜን አፋቤት ላይ አጥቻለሁኝ። ሌላውም እንዲሁ። ታሪክን እዬቆፈሩ መሰነጣጠቅ ሰይጣናዊነት ነው። ደግሞም አልጠቀመንም። ወደፊትም አይጠቅምም። መለያዬት ምኑ ያምራል? ጨገጎት የሆነ ጉድ …
በወቅቱ አማራር፤ ጥብብ፤ ብልህነት፤ ስልት አጣ ያ ሁሉ ነገር ወደመ። ፍቅር አብሮ ወደመ። አሁን ደግሞ ያ የወደመው ፍቅር እንደ ወደመ ይቀር ነው የሚለን ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሽፈራው። ውስጡን እራሱ ስለሙን እንደ ተፈጠረ የሚያውቀው አይመስለኝም።
ሰው የተፈጠረው ስለፍቅር ነው። ቃል የተፈጠረው ስለፈቅር ነው። ፈጣሪ ወደ ምድር የመጣበት ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ነው። ትውልድን የሚፈጥረው ፍቅር ነው። ለፍቅር የተፈጠሩ አካሎች ሁሉ አሉን። ለዚህ ነው እኔ ፍቅር እንደ ሙያ በት/ ቤት ደረጃ መሰጠት አለበት የምለው።
የባህርዳሩን ሰልፍ ብክል እንዲኖርበት አለወቅቱ የሚነሳ ተባይ ሃሳብ ታዝሎ አርበኝነትን ከሳ። አንዲት ሴት ወደ ፖለቲካ መድረክ ስትመጣ በራሱ ፈተና ነው። ያን ሁሉ አልፋ እጅግ ለላቀ ደረጃ እራሷን አሳለፋ ስተማገድ ደግሞ የሰማይ ታምር ነበር። ያን ጸጋዋን ሳያውኩ በተገባው መድረክ፤ በተገባ አቀራረብ ዕውቅናውን ማስጠበቅ ማዝለቅ ሲጋባ ቁልቁል ወረደ። እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ነው አሜሪካ የሚኖሩ ወገኖቼ የደወሉልኝ። እውነትም ነው። መጠንቀቅ ያስለፈልጋል።
አሁን የሚፈለገው የአማራ ወጣቶችን መንፈስ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ያለውን ግንኙነት ነቅፈው እንዲወጡ ለማድረግ ነው። በአብይ አልተሳካም አሁን የመጨረሻው ዕድል ደግሞ ይሄው ነው። „ኢሳያስን አትቀበሉ“ ነው።
ስለነበረው ነገር ይወሳ ከተባለ ከወንጀል ነፃ የሆነ ሰው ማግኘት አይቻለም። ይህ የአንድ የሁለት ሰው ችግር አይደለም።
የ66ቱ ዘመን „አማራ ጨቁኗሃል፤ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እስር ቤት ናት፤ የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል“ ከእኛ የቀደሙት ያነሱት መፈከር ነው። ኢህአፓም፤ መኢሶንም፤ ኦንግም፤ አሆዴድም፤ ወያኔም፤ ሻብያም፤ ጀብሃም በኋዋላም የመጡት ቢሆኑ ሁሉም አማራን በጠላትነት፤ አማርኛ ቋንቋን በጠላትነት የፈረጁ ናቸው።
ስለዚህም አማራ ተጋድሎ ባለቤት አልባ ሆኖ ያን ያህል እንግልት አስካሁን እዬደረሰበት ያለው። ስለዚህ ሁሉ ስልጣኑን ስላላገኜ እንጂ ቢያገኘው ከዚህ ውጪ አይታሰብም። ችግሩ እናንተም ወጣቶች ከዛ የተለዬ ንድፍ ማቅረብ አለመቻላችሁ ነው። ሁሉን ነገር በአሉታዊ ነው እምትቃኙት። የተፋቀ ዘመን።
ሰው ጥሩ ሲሳራ ጥሩ ማለት ካልተቻለ እኮ መጥፎነትህን ቀጥልበት ነው። እና ጦርነትን ጠማኝ የሚል መሬት የመደብደብ ጉዳይ ነው። አሁን ቀጣይ ስበሳባ ሲኖር ደግሞ አንድ ከእስር የተፈታ አርበኛን እንዲናገረው ይደረጋል። ለዚህ ነው „አኖሌ“ አልነበረችም የአማራ የማንነት ተጋድሎ አስኳል ጉዳይ። ነገር ግን „አኖሌ“ በዬሁኔታው እንድትነሳ የሚደረገውም ለዚህም ነው።
መሰባሰብን መተማማን ማንምም አይፈልግም። የኦንግን መሥራቾች አሽኮኮ አድርጎ የኖረ ድህረ ገጽ „አኖሌ“ ስትነሳ በአብይ መንፈስ ዘመን ደስታው ነበር። ለስንት ዘመን ነው አማራ ማገዶ እንዲሆን የሚፈለገው?
አሁን አንድ የኦንግ ክንፍ ኢትዮጵያ አቀባበል ሲደረግለት ዓርማውን ይዞ ነበር የገባው። የትም ቦታ የነፃነት ታጋይ አቀባባል ሲደረግለት በዚህ መልክ ሥልጣኔ የት ነህ ያሰኛል? በዛ ላይ የበታችነትም ነው። ይህን ለማረቅ ነው እነ ለማ አብይ ገዱ አንባቸው ሌት ተቀን እዬሠሩ ያሉት። ሚሊዮኖችም ደግፈውታል። ነገ ደግሞ በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ ያደመ ሌላ መፈክር አስይዛችሁ ሰው ታሰውጣለችሁ። እንደ ሰሞኑ ከዶር አብይ አህመድ ጋር የዲያስፖራ ፖለቲከኞችን እንዳስለጠፋችሁ ማለት ነው። ከዚህ ተረተረት ውጡ።
ዓለም እራሱ የተጠማችበት መሠረታዊ ጉዳይ አለ። ፍቅር ሰላም። በአንድ ወቅት ስለ ዶር አብይ አህመድ ሙግት ላይ በነበርኩበት ጊዜ አምንሲት ኢነተርናሽናል ራሳቸው ናቸው ብዬ ነበር። የሆነው ያነ ነው። ወደፊትም ታያላችሁ። አሁን እዛ ተገኙ እና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ቅርበት ተጀመረ ነው። በስንቱ ቀንታችሁ ትዘልቁታላችሁ?
በበደል ያልበደለ የለም። ይቅርታ መድረግ ነው ክብር። ሌላው ይቅር በዛ ዕድሚያቸው እነዛ የኤርትራ እናቶች ያን ያህል ሲደስቱ እንደ ዓለም ዜጋ አያስደስትም? ህፃናቱ፤ ወጣቶች፤ ስለነገ እንሰብ። የጦርነት መንፈስን ለልጅ ልጅ ለማውረስ አንትጋ። እኔ እንዲያውም እራሴ የኤርትራ ልዑክ አዲስ አበባ ሲጋባ እንዳዛ አይነት የማላውቀው ስሜት ይሰማኛል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ለካንስ ጉዳቱ ውስጤኔ አክስሎት ነበር። አዲስተ ስሜት ነው የተፈጠረብኝ።
እባካችሁ ደስታችን አትቀሙን! ተረባባርባችሁብናል። የዶር አብይ አህመድ ወደ ፊት ሲመጡ፤ „ከዝንጀሮ ቆንጆ እያላችሁ፤ ፈንጠዝያው ጣሪያ ነክቷል በልክ አድርገት፤ ለማ አብይ ገዱ አጀንዳችን አይደለም፤ የተንሳፈፈ ስልጣን ነው ያለው ህዝብ የሚመራው በጋንታ በኮሜቴ ነው …. ቃል ብቻ ዋጋ የለውም፤ ዋስታና ቢስ ቃል አንፈልግም፤ እክሌ ካልተፈታ እንዲህ ካልሆነ እንዲያ ካልሆነ“ እያላችሁ ስታምሱን ከረማችሁ። አሁን ደግሞ ፍቅር ሰላም ሲመጣ አይምጣባችሁ ትሉናላችሁ። መላ ቢሶች። መላም ሥራም አጣችሁ። አጀንዳም አጣችሁ። ችግራችሁ ይሄ ነው።
- · ዴሚክራሲ በህግ ለህግ የሚገዛ ነው።
ዴሚክራሲ እኮ ህግ የሚገዛው ነው። እናንተ ናችሁ ሥርዓተ አልበኛ የሆናችሁት። ሲቂዝ ብትመጡ የሚተነፈሰው አዬር በህግ ነው የሚተዳደረው። ቆሻሻ መጠያ በተገዛ ፕላስቲክ ነው። የሚገዛው ፕላስቲክ ደግሞ ዬዬከተማው በተለዬ ማርክ ነው።
ወረቀት ዝም ብሎ አይጣልም ገመድ ተገዝቶ በሁለት ሳምንት አንድ ቀን በስርዓት ታስሮ ነው የሚቀመጠው ከማንሻው ቦታ ወስዶ ማስቀመጥ ግድ ነው፤ ልብስም እንዲሁ አይጣልም፤ በሚላከው ፕላስቲክ በማንሸው እለት ተዘጋጅቶ ነው የሚጠብቀው። ክፍያ በመጀመሪያው ደብዳቤ ካልተከፈለ በዳብል ነው የሚመጣው ሁለተኛው ደብዳቤ … ያ ካልሆነ ቀጥታ ወደ ፖሊስ እሰከ ቅጣቱ ይመጣል።
ቤት - ሥራ - ፓስ ለማግኘት ማነቆ ነው የሚሆነው። ወዘተ ወዘተ …. ለእያንዳንዱ ህዝበ ነክ ሞጋች ጥያቄዎች በዬሦስት ወሩ ህዝብ ውሳኔ አለ … ከዛች ፈቅ የለም … ሲዊዝ የዴሞክራሲ አገር ብትሆንም ዴሞክራሲው ግን በህግ መገዛት መተዳደር አለበት። የሲዊዝ ዴሞክራሲው ከሲዊዝ ህገ መንግሥት በታች እንጂ በላይ አይደለም። „መተቸት እችላላሁ የመደገፍ ግዴታ የለብኝም¡“ … ልኩን ያለወቀ አገላለልጽ ነበር።
አሁን አይደለም ኢትዮጵያ የታዬውን ታይቷል። ሁሉም አበቃ ለማም ገዱም አብይም ተከተከቱ አሁን ደግሞ ወደ አዲሱ ጉዞ ሆኗል። ኤርትራ አትቀበልም ጥሪውን ስትባል እልል ብላ ተቀበለች … አሁን ደግሞ እልልታው ዋይታ ይሁን ነው ሙግቱ …. ሰነፎች!
እኔ እውነት ለመናገር የትናንት የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ መንፈሱ የለም ባይ ነኝ። ጥርጣሬዬ እና ምልክታዬ የተለወጠው ከቦሌው ትዕይነት ቅጽበት ነበር። አሁን በቅኗ ሥርጊትሸ ልቦና ውስጥ አዲስ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ነው ያሉት። ይህም በውስጤ ነው።
ካለምንም ጥርጣሬ ፍቅርን - ቅንነትንት - ሰላምን የተቀበለ ፍጹም የተለወጠ አዲስ አቶ ኢሳያስ ነው አሁን ያዬሁት። እኔ እንዲያውም በዝቶብኛል። ህዝቡ እና መሪውንም ስታዩት በጣም የተቀራረበ ነው።
ቤት ውስጥ ያለው የአኗኗር ዘይቤም በቃ እንደ እኔ እንደ ተርታዋ እንደ ደሃዋ ዜጋ ነው። አፍሪካ በሙስና በተዘፈቀችበት አህጉር እንዲህ ዓይነት አቅም ማግኘት ድንቅ ነው። አንድ ጊዜ እቀናለሁኝ ብዬ ሁሉ ጽፌ ነበር። የቤተሰቡ አለባበስ፤ የቤቱ አደረጃጃት፤ የቤተሰቡ ትህትና፤ የቤተሰቡ ፈርሃ እግዚአብሄር።
ሌላው ቀርቶ የእኛ ውጣቶች ሲዳሩ ጡት ማሰሪያ እንኳን ለማድረግ አለመፍቀዳቸውን አይተናል፤ ፊልም ላይም ከወገብ በላይ በሉ አካሎች ያለው መከደን እዬጠፋ ነው። ተራቁቷል ትውፊቱ።
የኤርትራን ወጣቶች ተመልከቱ ከነተፈጥሯቸው ነው ያሉት። ሥልጣኔ ማለት ከትውፊት ማፈንገጥ መለት አለመሆኑ ተቋም ከፍተዋል። ተመስጦዬ ብዙ ነው። የገጠር ጉዞ መንገዱ ሁሉ ሰው ነበር … ግብዣው ቁልቋል ነበር። ቁልቋል ጎንደርም አለ። አስተናጋጇ አለባበሷ እንዴት እዬላጠች ስታስተናገድ እንደ ነበር … ጥንቃቄዋ … የነፈቁኝ ብዙ ነገሮች ናቸው። የአብይ መንፈስ ምክንያት ነው ልዑል እግዚአብሄር ሁላችንም ወደ ልቦናችን ተመልሰን እንድናስተውል ጊዜ ሰጥቶናል።
- · የጉራጌ ዞን ጉዳይ።
ኤርትራን ወደ ሰላም ያመጣል ተብሎ የታሰበው ግንቦት 7 ነበር። አሁን የሆነውን በማስተዋል እንመርምረው። 27 ዓመት የኖረ ጉራጌ ከድል ማግስት ያለፋታ የክልል ጥያቄ ያነሳው ለምክንያት ነበር። እዛው ሆነው ነበር ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ የኤርትራ መንግሥትን የይሁንታ የምሥራቹን ዜና የሰሙት።
እዛው ላይም ሆነው ነው ወንድሜ ብሎው የደስታቸውንም መልዕከት ያስተላለፉት … እኛ የምናስበው ወዲህ ነው። ፈጣሪ ማህተሙን ከነምክንያቱ ያሳረገበት ደግሞ ይሄው ነው። ይህ መክሊት ለግንቦት 7 መሪ የተሰጠ አልነበረም። በመንፈሳዊ ትርጉሙ ይሄው ነው …
ፈጣሪ ስለማናቸውም ስለምናያቸው ነገር ሁሉ ምክንያተዊ አምክንዮ ላይ እንድናተኩር እያስተማረን ነው። አንዳንድ ጊዜ ፈጣሪ መሬት ወርዶ እዬሠራ እስኪመስለኝ ድረስ ነው በነገሮች ሁሉ እምመሰጠው።
የዚህ ሁሉ መሠረት „የኦሮሞ ደም ደሜ ነው“ የጎንደር የአማራ ተጋድሎ አብዮት ከዚህ በኋዋላ ነው „ጣና ኬኛ አባይ ኬኛ“ የኦሮሞ ንቅናቄ አብዮት የተፈጠሩት። ይህን መተርጎም ተስኗቸው ነው ከዛ ከወደቁበት ከፍ ያደረጋቸውን ለውጥ መነሻ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ መተቸት ያሰኛቸውም።
ለዛውም አማኝ ናቸው እኮ።
ይህቺን ኢትዮጵያ ያቆያት የእነሱን ህገ መንሥት ለመቀረጽ አገር የምትባል አገር ስለቆዬች ነው። ለዛ መሠረቱ ደግሞ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ልሙጡ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ነው። ዛሬ ለላው ለውጥም መነሻው የአማራ ተጋድሎ ነው። ሁሉንም አገሩ እንዲገባ ያስቻለ። የአማራ ድምጽ ባይኖርበት ኦህዴድ ምንም መሻገር አያቻለውም ነበር። ባለቅኔው የአብይም መንፈስም አይገኝም ነበር። የዚህ ሁሉ ትዕይንት የጀርባ አጥንት ያ ተጋድሎ ነው። ይዞት የወጣውም ይሄውን ሰንደቁን ነው። ለወደፊቱም እስከ ደም ጠብታ ትግሉ ይቀጥላል።
አንግልብ! … እናስተውል! እንሰከን! መክሊታችን ለማጥፋትም አንደፈር። በስተቀር የተሰጠን መክሊት ከላያችን ላይ ይወሰዳል።
„በነገር እዬተራቀቀ ራሱን የሚያስጠላ ሰው አለ። እግዚአብሄር የዕንቁውን መወደድ አይሰጠውም እና፤ ከጥበቡም ሁሉ ወጥቷል እና፤“
- · ቀጣይ አፍ ሞልቶ የሚገኘው ውጤት!
በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ለማስነሳት ግንቦት 7 ብዙ ደክሟል። መክሊቱ ስላልነበር፤ ስላልተሰጠውም፤ ፈጣሪ ስላልፈቀደለትም አልተሳካለትም። አሁን ግን መክሊት በተሰጠው በፈጣሪ በተቀባው በአሮን በትር አማክኝነት በዘመነ አብይ መንፈስ በቅርብ ቀን ይነሳል። ይህም ያልምንም ቅድመ ሁኔታ ነውየሚነሳው።
ሃይማኖት አለን ግን የፈጣሪን ጥበብ ማንበብ መረዳት ቀርቶ ምልክቶችን ተከትሎ ከማወክ መቆጠብ እንኳን አልተቻለም። ይህም ያማረብን ስለሚመስለን በዬተገኘው አጋጣሚ እንጠፈጥፋዋልን። ሸለሸል!
- · በሚስጥር የህሊና ስንቅነት ተዘወተረ! ተመስገን!
ሚስጢሩ ብዙ ነው ይህ ክንዋኔ። አብነቱ የላቀ ነው። የኤርትራ የካቢኔ አባላት ሁሉ ቁመው ሲያስተናገዱ ተመልክቻለሁኝ። ይህን ያደረገው ፍቅር ነው። ለአብይ መንፈስ ደግሞ ቅኖችም፤ ደጎችም፤ ግልፆችም፤ ሰላም ወዳዶችም ሁሉም ከመንፈሱ ጋር ቀድመው ነው የተጋቡት።
እትጌ ኤርትራም እያጣጣማችው ነው። ሰነብት ኤርትራ ላይ ትንሳኤ ነበር። ሰንበት ሁሉም ፍቅርን ቋጥሮ ሰንቆ ነበር ወደ ቤቱ የተመለሰው። አብሶ ህፃናት እና እናቶች ስቀውልኛል። ለእኔ ይሄ ከሁሉም በላይ ነው።
ጠ/ሚ አብይ የኢሳያስን ባለቤትና ልጆች ሲተዋወቅ PM Abiy Ahmed meets Eritrea's First Family.
በዚህ ውስጥ ብዙ ሚስጥራት አሉ አቅም ያላቸው ከእግዲህ እኔ ስለቀደመው አንዳችም ክፉ ነገር አላነሳም ብቻ ሳይሆን ዶር አብይ አህመድ ደርስ እስኪመለሱ ቅንጣት ታክል ስጋት አልነበረኝም። ስለምን? ጥበቡ የፈጣሪ ስለሆነ …
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
ፈጣሪዬ ሆይ የዚህ ዘመን ታዳሚ ስላደረከኝ አመስግንሃለሁኝ!
ተመስገን!
የኔወቹ ቅኖቹ የምትችሉ ፌስ ቡካችሁ ላይ ለጥፉልኝ።
ትውልዱን ማዳን አለብን። ኑሩልኝ!
መሸቢያ ጊዜ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ