ዕውቅና የሌው ችግር ከመፍትሄ ማን አስደርሶት?!
እንዴት? መቼ? በምን ሁኔታ? ስለምንስ? ዕውቅና የሌለው ችግር ከመፍትሄ ማን አስድርሶት? "ንጉሥ በፍርድ አገሩን ያጸናል፤ መማለጃ የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል።" መጸሐፈ ምሳሌ ፳፱ ቁጥር ፬ · መ ራራ መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=v1-4DqsofQw የራያ አማሮች በትግራይ ቅኝ ገዢ ወራሪዎች የሚደርስባቸው እንግልት ግድያና የማንንት ነጠቃ። https://www.youtube.com/watch?v=cUE6uDsTPW4 Ethiopia Special News የወልቃይ ስቃይ እየበረታ መቶዋል October/5/2018 https://www.youtube.com/watch?v=szp63jqOiXs ራያ አላማጣ ከትግራይ ጨፍጫፊ ሰራዊት ጋር ፍጥጫ 7 አማሮች ተገድለዋል · እ ምታን በዕድምታ፤ ኡኡታን ለሰርክ … አሁንም ጩኸት ሆነ። አሁንም እሪታ አለ። አሁንም ስጋት አለ። አሁንም መከራ አለ። ህፃናት ያለቅሳሉ፤ እናቶች ያነባሉ፤ አዛውንቶች ኡኡ ይላሉ። ማን አላቸው እና ያልቅሱ ... ፈጣሪ ከሰማቸው። አሁንም የታቀደ ጥቃት አለ። አሁንም ለቅሶ አለ። አሁንም መሰደድ አለ። አሁንም ተስፋ ማጣት አለ ለአማራ። አሁንም መኖር ተከልክሏል። አሁንም መተንፈስ አያቻልም - አማራ። አሁንም ችግሮች በአይነት ተደርድረዋል በተለይ ለአማራ። አሁንም አሳሩ ውጧታል አማራን። እንዴት ይፈታ? መቼስ ይፈታ? በምን ሁኔታስ ይፈታ? ስለምንስ ችግሩ አዬለ? መቼ ይፈታ ቢባል ችግሮችን ለመፍታት ለችግሩ ዕውቅና መስጠትን ይጠይ...