የቃና ብሥራት ከአሜኑ መንፈስ ።
የቃና ብሥራት ከአሜኑ መንፈስ ። „ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቅ ትእዛዜን በ አንተ ዘንድ ሸሽግ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ ሥላሴ Sergute Selassie ከእመ ዝምታ ከሲዊዝ ጠቅላይ ሚኒሰተር አብይ አህመድ ሆይ! ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ሆይ! እናንተን የሰጠን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን! ለዚህ ስላበቃንም ልዑል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን። አምና ይህን ጊዜ ጭንቅ ላይ ነበራችሁ። ያ ሁሉ አልፎ ዛሬ እንዲህ ቃለ ምህዳን የሚሰማበት ሆነ። በ17 +27 ዓመት ውስጥ ይህ ንዑድ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ልዩ ቀን የብሥራት ቃና ዘገሊላ ማዕልቷ ነው። ፈጣሪ የእናንተን ክፉ ነገር አያሳመን። ድንግልዬ ጥላ ከለላ ሁና ትጠብቅልን። ቃለ ህይወት ያሰማንል። እንዴት ነፍስን የሚታደግ የፈውስ መልዕክት ነው። እንዴትስ „የተባረከ ትውልድ ለተባረከች አገር“ መሰረት የሚጥል ነው። ኑሩልን። ሌላም ቅን ተግባር አለ። የቅድስት የእመት ዘውዲቱ መሻሽ የመልካም ነገር ተምሳሌት ተቋምም ጎብኝተዋል። የሚገርም ነው። ቅንብሩ ራሱ የተሟላ ነው። ይህን ውስጥነት በቃና ቅኔ፤ በእድምታ መሆን እንዲህ ጠልፎ የሰጠን አማላክ የተመሰገነ ይሁን። እንኳን በህይወት ኖርኩኝ። ይህን መልካም ነገር አይ ዘንድ ይህን የሐሤት ዘመን የሸለመኝ ፈጣሪዬ የተመሰገነ ይሁን አሜን። ውዶቼ የኔዎቹ እስኪ አዳምጡት እንዴት የህሊና የመንፈስ መዳኛ እንደሆነ። አንባቢውም እራሱ ስክን ያለ ህይወትን የሚመሰጥ። ተመስገን! https://www.youtube.com/watch?v=2qV3a_IDZdk Ethiopia : [ ሰበር ዜና ] ጠሚ አብይ እና ባለቤታቸው የገና ...