ልጥፎች

ከጁላይ 12, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአማራ ቀን በጎንደር …

ምስል
የአማራ ቀን በጎንደር … https://www.zehabesha.com/amharic/archives/92836#respond የአማራ ተጋድሎ የተጀመረበትን ቀን በማስመልከት ኮል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ጎንደር ላይ ያደረገው ምርጥ ንግግር የኔዎቹ ቅኖቹ ዘሃበሻ እጅግ አድርጌ አመሰግናቸዋለሁኝ። እንኳን ደስ አለን ያን ያህል መከራ አልፎ ዛሬ ይህን ቀን ለማዬት አበቃን። በቃ የደስታ ቀን። ጧፍ በርቷል። አማራ እንኳን ደስ አለህ። እኔ ለጎጃም የተለዬ መንፈስ ስላለኝ ጎጃም እንኳን ደስ አለህ። ዕንባዬን መቆጣጠር ስላልቻልኩ ከዚህ በላይ መጻፍ አልቻልኩም። አገልጋያችሁ ሥርጉትሻ።

ሐምሌ አምስት የአማራ ተጋድሎ ቅዱሱ ቀን!

ምስል
ገናናው የአማራ ተጋድሎ የጎንደር ጎጃም አብዮት በሁለገብ ትጋቱ በአጭር ጊዜ ለድል የበቃ ክህሎቱ ስለትንግርት ነው። „ልጄ ሆይ ሕጌን አትርሳ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።“ (መፅሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ ሥላሴ 12.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        መነ ሻ። ሐምሌ አምስት አቦዬ ናቸው አነባበሮ የሚዘጋጅበት። አነባባሮ በኑግ አና በተልባ የሚዘጋጅ ነው። እንደ እሙሃይ ቂጣ ወይንም እንደ ዳቤ ያለ። አቦዬ ከጎነደር ለተማ በርቀት ስለሚገኙ ጉዞው አድካሚ ነው። ስንመለስ ግን ከትንሿ ገብያ ጉዝጓዟን ገዛዝትን ጠበላችን ይዘን ስነገባ ቤቱ ደግሞ እልባብ ባልባብ ሆነ ይጠብቅናል። ያው የሐዋርያት ፆምም መፍቻ ነው። አንድ ሐምሌ አቦ ግን ሌላ ፈተና፤ ፈተናውም ታምር ይዞ መጣ ያም እንዲህ ሆነ። ዘመናይነት።  ሰሞኑን የአቶ አባይ ወልዱ ባለቤት በአውስትራልያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አንባሳደር ወ/ሮ ትርፏ ኪዳነማርያም ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ ቃለ ምልልስ ከSBS አድርገዋል። ለውጥ ስለ አመጣው ሃይል የተለመደውን ቧልታቸውን አስደምጠውናል። ለውጡ በኦሮሞ ንቅናቄ ብቻ እንደመጣ አድርገው ነበር ያቀረቡት። እንደ መልካም መግለጫም ታይቶላቸው በዬቦታው ተለጥፎላቸው አይቸዋለሁኝ። ይሄ በአንድ እጅ ማጨብጨብ ጭቆናም ነው።  ወያኔ ሃርነት ትግራይን ለማትረፍም ሆነ ሥልጣናቸውን ሊያቆይላቸው ይችላል። በዚህ ቦታ ተቀምጦ ከእውነት ጋር ተጣልቶ ከእውነት ጋር ተፋልሶ፤ ከእውነት ጋር ተቃቅሮ ግን ከሆነ ነፍስን የመፋረዳት እዮር አለ።  ቦታው እራሱ የህሊናን ስልጡነንት ይጠይቃል። እሳቸው የኢትዮጵያ ተወካይ እንጂ የባለቤታቸውን...

የቀራንዮ መባጃ በትንሳኤ መባቻ!

ምስል
የሦስት ሺህ ዘመን አረንቋ በ100 ቀናት የተሻገረው የቀራንዮ መባጃ ሰውን ያበጀ New Era። አለዛሯ ኢትዮጵያ መድህኗን አግኝታለች። „ልጄ ሆይ ቃሌን ብትቀበል ትእዛዜን በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት ጆሮህን ጥበብን       እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፤ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።“  (ምሳሌ ምዕራፍ 2 ቁጥር  1 ) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 12.07.2018 (ከገዳማዊት ሲዊዘርላንድ)    v  „ቃል።“ የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረ ነው። ቃልን የፈጠረ እሱ ነው። ሥጋ እና ደምን አርግቶ ሰውን የፈጠረም እሱ ነው። ትወልድን የፈጠረ እሱ ነው። አገራትን፤ አህጉራትን የመሠረተ እና ያስመሰረተም እሱ ነው። ውቅያኖስን ወንዞችን፤ ተራራ ጋራ ሸንተረሮችን መስክ መሬት ምህዋርን ነፍስን በሙሉ የፈጠረ እሱ ነው። የልዑል እግዚአብሄር ቃለ ምህዳን መሬት ላይ ወርዶ የሃጢትን መርገምት ጥሶ ሰንሰለቱን በጣጥሶ ትንሳኤን ያሳወጀው እሱ ነው።   v  ውልደት። የሰው ልጅ ሲወለድ ንጹህ ህሊናን ይዞ ነው የሚወለደው። ያረጋው ደም ረግቶ ሰዋዊ ተፈጥሮ ይዞ ወደዚህች ምድር ሲመጣ ያለቅሳል፤ ያን የጸጥታ እና የአብሮነት፤ ያን የፍስሃ እና የሰናይ፤ ያን የንፅህና እና የፍቅርን ባዕቱን ትቶ ሲወጣ የሚገርፈው ወጀብ እንዳለ፤ የሚቀቅለው የክፉ ነገር ገሃነም እንደሚኖር፤ የሚያናውጠው ማዕበል እንዳለ፤ የሚቆምባት መሬት ድውያን ቋያ እንደምትሆንበት፤ የሚጠጋው እሾህ የጠናበት ስለመሆኑ፤ የቀኗ ብርሃን የሚግርዱ የሴራ ድሮች እንደሚፈትኑት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ምርር ብሎ ያለቀሳል። ይህቺ ምድር ታስለቅሳለች ከውኑ ላለ መንፈስ። ሁሉ ነገር አላት...