የቀራንዮ መባጃ በትንሳኤ መባቻ!

የሦስት ሺህ ዘመን አረንቋ በ100 ቀናት የተሻገረው የቀራንዮ መባጃ ሰውን ያበጀ New Era። አለዛሯ ኢትዮጵያ መድህኗን አግኝታለች።
„ልጄ ሆይ ቃሌን ብትቀበል ትእዛዜን በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት ጆሮህን ጥበብን
      እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፤ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።“
 (ምሳሌ ምዕራፍ 2 ቁጥር  1 )
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 12.07.2018
(ከገዳማዊት ሲዊዘርላንድ)





   v  „ቃል።“
የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረ ነው። ቃልን የፈጠረ እሱ ነው። ሥጋ እና ደምን አርግቶ ሰውን የፈጠረም እሱ ነው። ትወልድን የፈጠረ እሱ ነው። አገራትን፤ አህጉራትን የመሠረተ እና ያስመሰረተም እሱ ነው። ውቅያኖስን ወንዞችን፤ ተራራ ጋራ ሸንተረሮችን መስክ መሬት ምህዋርን ነፍስን በሙሉ የፈጠረ እሱ ነው። የልዑል እግዚአብሄር ቃለ ምህዳን መሬት ላይ ወርዶ የሃጢትን መርገምት ጥሶ ሰንሰለቱን በጣጥሶ ትንሳኤን ያሳወጀው እሱ ነው።

  v  ውልደት።
የሰው ልጅ ሲወለድ ንጹህ ህሊናን ይዞ ነው የሚወለደው። ያረጋው ደም ረግቶ ሰዋዊ ተፈጥሮ ይዞ ወደዚህች ምድር ሲመጣ ያለቅሳል፤ ያን የጸጥታ እና የአብሮነት፤ ያን የፍስሃ እና የሰናይ፤ ያን የንፅህና እና የፍቅርን ባዕቱን ትቶ ሲወጣ የሚገርፈው ወጀብ እንዳለ፤ የሚቀቅለው የክፉ ነገር ገሃነም እንደሚኖር፤ የሚያናውጠው ማዕበል እንዳለ፤ የሚቆምባት መሬት ድውያን ቋያ እንደምትሆንበት፤ የሚጠጋው እሾህ የጠናበት ስለመሆኑ፤ የቀኗ ብርሃን የሚግርዱ የሴራ ድሮች እንደሚፈትኑት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ምርር ብሎ ያለቀሳል። ይህቺ ምድር ታስለቅሳለች ከውኑ ላለ መንፈስ። ሁሉ ነገር አላት ግን ላላት ነገር ብቁ አይደለችም።

ይህቺ ዓለም ሲመጡባትም - ሲኖሩባትም ሲሄዱባትም ታስፈራለች። የተፈጥሮው ቁጣ የሰው ልጅ ሊከላከለው፤ ሊቋቋመው ሊያሰቀረው አይችልም። የሰው ልጅ ግን አቅም አለው ይህን የተፈጥሮን አደጋ ማስቀረት ባይችልም እራሱ የሚሠራቸውን ሰው ሰራሽ ፈተናዎች፤ በሰው ልጅ የሚደርሱ ሰቆቃዎችን፤ ስቃዮችን ለማስቀረት ቢጥር ቢፈቅድ ቢያንስ የሰው ልጅ ወደ ምድር ከመጣበት ጀምሮ የሚገጥሙት ድርብ ፈተናዎችን አንዱን ማስቀረት ቢችል መልካም ነበር።

በመንግሥታት መውደቅ እና መነሳት፤ በመንግሥትት አንዱን በመውረር እና እንዱን በማስገበር የነበሩ ፈናዎች ሁሉ ሰው ሰራሽ ፈተናዎች ናቸው። ያ ሁሉ ዓለም ያስተናገዳችው የሃይማኖት፤ የርዕዮተ ዓለም፤ የቅኝ ግዛት ምኞት፤ የመደብ ጦርነቶች ሁሉ የሰው ልጅ ራሱ የሰራው መከራ ነው። የሰው ልጅ የራሱን መከራ ራሱን አበጅቶ ባባጀው መከራ ሲማቅቅ ነው የባጀው። ውልደቱን ያጣበትም በዚሕው ነው።

   v   እንደገና መወለድ።
ዓለም በተወሰነ ደረጃ እጅግም ዘግይቶ ከእንቅልፉ ሲነቃ ከሁተኛው ዓለም ጦርነት በኋዋላ ሰው መሆንን ዋና እንብርታዊ ጉዳይ አድርጎ ወስዶ ስለሰባዕዊነት መቆርቆር ጀመረ። ተፈጥሮም ለስው ልጅ መፈጠር ውስጥ ሰለመሆኑም እንክብካቤ ይኖረው ዘንድ ተጋ በተወሰነ ሁኔታ። ሉላዊ ድርጅቶችን መሰረተ። ህግ አረቀቀ። አጸደቀ። የሰዎች ማህበር መሥርቶ፤ መሪ መርጦ ሰውን አክብሮ ስለመነሳት ሰበከ። ይህ እንግዲህ አንዱ እርምጃ ነው። ይህም ሆኖ ግን ክፉ ነገሮችን የሚያበረታቱ ሌሎች ተግባሮችን በተከፈለ የሃይል አሰላለፍ በጎንዮሽ መሥራቱን ግን አላቋረጥም። ለዚህም ከፍተኛ መዋለ ንዋይ መድቦ ተግባሩን አንቱ ብሎ ይከውናል። መከራው እስከዋጠው እስከ 21ኛው ምዕተ ዓመት ድረስ።

  v   ንቅለት።
እርግጥ ነው መልካሙ ነገር ተመጣጣኝ ለማድረግ የተሄደበት ነገር ጥሩ ነው። ግን በቂ አይደለም። ለምን? እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ተቋማዊ ተግባር መፈጸም ስላለበት። ለምሳሌ „አልሸባብን፤ አይሲስ“ በሚመለከት በጀት የሚሰጧቸው አገሮች ወቅቱ ሲጫናቸው፤ ወይንም ከሃያላን መንግሥታት ሹም ሽር ጋር የፖለሲ ለውጥ ሲገጥም ተግ ሊል ይችላል፤ ነገር ግን ከሥሩ የሚነቅል ተግባር ካልተከወነ በአንድ ወቅት ደግሞ ሊፈነዳ ይችላል፤ አግርሽቶ ይነሳል። በአዲስ ሥም እና ሁኔታ።  እኔ የዚህ ዶግማ „የሽብሩ“ ማለቴ ነው ጉድለቱ የግለሰቦች ወይንም የድርጅቶች ነው ብዬ አላምንም። በፍጹም። ነገም በ አዲስ ሥም እና ይዘት አዲስ ኢ- በስዕዊነት፤ ኢ- ተፈጥሯዊነት ይከሰታል። ስለሆነም መፍትሄው ችግሩን በጥሞና አጥንቶ የችግሩን ሥር ከመሠረቱ መንቀል ነው የመጨረሻ መፍትሄ አስገኝ እርምጃው።

  v   ሰውና ሰውኛ።  
ስለምን? ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ጉድፍ ሃሳብ ይዞ አይወለድም። ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ጨካኝ ሆኖ አይወለድም፤ ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ዘረኛ ሆኖ አይወለድም፤ ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ጨቋኝ ሆኖ አይወለድም፤ ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ፋሺስት ሆኖ አይወለድም፤ ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ትዕቢተኛ ሆኖ አይወለድም፤ ማንኛውም ልጅ ሲወለድ አክራሪ ሆነ አይወለድም፤ ማንኛውም ልጅ ዘረኛ ሆኖ አይወለድም። ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ሰው የሚጠላ ሆኖ አይወለድም፤ ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ዘራፊ ሆኖ አይወለድም፤ 

ማንኛውም ልጅ ሲወለድ አስገድዶ መድፈርን እንደ የተለመደ አድርጎ መወስደን ይዞት አይደለም የሚፈጠረው፤ ማንኛው ሰው ሲወለድ ሌላውን መጨቆንን፣ መግደልን፣ ማሰቃዬትን ይዞት አይወለድም፤ ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ተፈጥሮን ተጻራሪ ሆኖ አይወለድም።

ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ኢጎኢስት ሆኖ አይወለድም ይህን ክፉ ነገር ልጆች የሚማሩት፣ የሚያጠኑት የሚከተሉት ከቤተሰብ፤ ከማህበረሰብ፤ ከት/ ቤት፤ አንዲት አገር ከምትተዳደርብት ዝበታዊ አይዲዮሎጂ፤ ተዛናፋዊ ህገ መንግሥት፤ በማህበራዊ ኑሮም ልጆች አብረዋቸው ከሚውሉት ጓደኞቻቸው ነው …

በስታሊን ዘመን የተወለደ፤ በአዶልፍ ሂትለር ዘመን፤ በናዚ ዘመን የተወለዱ ልጆች ይህን ጠጥተው ጠብተው ነው የሚያድጉት። እንደንዚህ ዓይነት ሰዎች ሲፈጠሩ መርዛቸውን የሚጀምሩት መሠረት ይሆነኛል ካሉበት እትብታቸው ከተቀበረበት ቦታ ነው። የአላዛሯ ኢትዮጵያም ፈተና ይሄው ነው። ያ እትብታቸው የተቀበረበት ቦታ የናሙና የሠርቶ ማሳያ ማዕከላቸው ነው። ከዛ ነው አዲሱ እኩይ ስብዕና የሚቀረጸው። ከዛ ነው አዲሱ አሉታዊ ሰው የሚፈጠረው፤ ከዛ ነው የክፉ ነገር ማምረቻ የምድር እንቦይ የሚፈጠረው …

ስለዚህ ዓለም ይህን ነገር ከሥሩ ነቅላ ለመጣል የወሰደቻቸው እርምጃ በቂ ባለመሆኑ ነው ዛሬ ናዚዝም እጅግ ጠንክሮ ባለፉት ዓመታት ታይቶ የነበረው። በዬአካባቢው ያለው ሰው አይምጣብን ጥላቻም ትልቁ የፖለቲካ ትኩሳት የሆነው። እርግጥ ነው ለወቅቱ ችግር ትናንት በጦርነት በማሸነፍ እና በመሸነፍ፤ አንዱ አደራዳሪ ሌላው ተደራዳሪ በመሆን በሽምግልና ፈተውታል፤ ግን ተቋም አልፈጠሩለትም።

ተቋም የተባባሩት መንግሥታት፤ የአማንስቲ ኢንተርናሽናል፤ ቀይ መስቀል ወዘተ እንሱን ለናሙና ማንሳት ይቻላል። እነሱ ችግሩ ከደረሰ በኋዋላ መፍትሄ አፈላላጊ ድርጅቶች ናቸው። እኔ ዓለም ስታዋላች፤ ጭራሽም ረስተዋላች የምለው የዕምሮ አጣባውን Brainwashing ፕሮጀክት ነው ብዬ ከ2015 ጀምሮ እዬሞገትኩት ያለሁት መሠረታዊ አምክንዮ ልጆች ሲወለዱ፤ አዬሩ ሊቀበላቸው የሚገባ የፍቅር ተፈጥሯዊ መርህ የሰፈነበት ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ። 

ምክንያቱም ችግርን ከተፈጠረ በኋዋላ መፍትሄ ለመስጠት ከመድክም ይልቅ፤ ችግሩ እንዳይፈጠር የችግሩ ማድረቂያ የህሊና እጠባ Brainwashing ፕሪጀክት ተግባርን በቋሚነት በትምህርት ደረጃ ማህበረሰቡ ሊማረው ይገባል ነው መሰረታዊ ጉዳይ መሆን የሚገባው። ይህ ብቻ ነው ሰውና ሰውኛን ሊያገናኝ የሚችለው ድልድይ።

  v   ፍዳው።
ቤተሰብ መልካም አድርጎ ቢያሳድግም፤ ሃይማኖታዊ ተቋማትም የበኩላቸውን ቢጥሩም፤ ከንፍሮ ጥሬ ያወጣቸው ደግና መልካም ሰዎችም የቱን ያህል ቢደክሙም፤ ውጪ ልጁ የሚወልባቸው መንገዶች፤ ት/ ቤቶች፤ ሲያድጉም የሚኖርባቸው አካባቢዎች፤ ኑሮውን የሚመሠርትባቸው ቦታዎች የጠሩ ካልሆኑ ታጥቦ ጭቃ ነው። እንዲያውም የልጁ አዕምሮ በግጭት የታወካ እና በውስጥ ሰላሙ የታመሰ ነው የሚሆነው። ስለምን ወደ ቤቱ ሲሄድ ሰላም ይጠበቀዋል ግን ውጪ ሲወጣ በሌብነት የበለጸጉ ቤተሰቦች የኑሮ ጣሪያ ከፍ ማለት ያውከዋል፤ ጋባዥ ካገኘ እሱም ይቀለቀላል ያን የተበከለ አዬር።  

የአንድ አካባቢ ጤንነት፤ የአንድ አካባቢ ንጹህነት ማህበረሰብን ለመቀዬር ውጤቱ አድሮ ጥጃ ነው። እዚህ ታጥበዋለህ ሰው ተንቀሳቃሽ ፍጡር ነው፤ በቅንቅስቃሴው ልክ የሚቀበለው አዬር ወጥ ካለሆነ ቅይጥን መንፈሶችን እንዲያስተናግድ ይገደዳል። „ሰው ለማዳ እንሰሳ“ ስለሆነ። ለዚህ ነው እኔ የፍቅር ተፈጥሮ መርህ ዓለም አቀፍ ዕውቅን አግኝቶ በት/ ቤት ደረጃ በቋሚነት መሰጠት አለበት የምለው።
የቀድሞው የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ደጉ ሰው ለጻፍኩላቸው ጥያቄ መልሳቸው እስኪ ለአገርሽ መንግሥት አማካሪው ነበር ያሉት። 

ያ የእኛ አገር ብቻ ችግር አይደለም። የሁሉም አገር ችግር ነው። እኔ እዚህ ሲዊዝ ስመጣ ክፍት ከሆነው ወንበር ላይ ተቀምጬ ወደ ፈለግኩት ቦታ እንቀሳቀስ ነበር። ያ እዬከበደ ነው ከ15 ዓመት በኋዋላ … ሰው ፊቱ ያስፈራል። ቀለሙ አይደለም ከተመሳሳይ ቀለሜ ጋር ሄዶ ለመቀመጥ ገጹ ያስፈራል። ስለዚህ ባዶ ቦታ ካልኖረ ቆሜ መሄድን እመርጣለሁኝ። ሰውን ሰው ማስጠጋት አይፈቅደውም። ይሄን በተለያዩ የሲዊዝ ከተሞች ለናሙና ተዘዋውሬ ጥናት ሰርቼበታለሁኝ። ምንድነው ይሄ የሚያሳዬን ሰው ሰውን የአለማቅረብ ዝንባሌው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ነው …

  v   ሥልጣኔን ቅጥ ስለማስያዝ።
ሌላው የዲጅታል ዘመን ወረራ ነው። ስለጣኔው መልካም ነው ግን ከ50 ዓመት በኋዋላ ሰው ቴሌፎን፤ ኢንተርኔት አግብቶ ብረት ወዶ እና ወልዶ እንደሚኖር ሁሉ አስባለሁኝ። አምላኬ ቴሌፎን ኢንተርኔት ነው የማለት ሁሉ አደገኛ ዝንባሌ ይታያል። ይህንም ተንቀሳቅሼ ባዬሁት ከ10 ሰው እንኳን አንድ ሰው ከቴሌፎኑ ጋር የማይጫወት ለማግኘት ይቸግራል፤  ስለዚህ አፍቅሮተ ማሽን ግሎባል ዜጋ እዬተፈጠረ ነው ማለት ነው።

በዚህ ውስጥ የቤተሰብ፤ የባህል፤ የሃይማኖት ዕሴቶች ድርቀት ለመጪው ዘመን እጅግ ያሳጋል … ብሎጌ ላይ ፖስት ማድረግ አልችልም፤ በተለያዩ ሁኔታ አገጣጥሜ በ2015 የሰራሁትን ንድፍ ስለሆነ ቪዲዮ ግን እሰራበታለሁኝ እኔ ለወደፊት የሚታዬኝን  የዓለም መከራን የነደፍኩበትን ሁኔታ …  እጅግ አስፈሪ ነው። ጸሐይ ትወጣለች ግን እምታሞቀው ግማሹን ነው። 

እምታሰብለውም ግማሹን ነው ንድፉ ተደሞው እንዲህ ነው የሚለው መጨረሻ በ100 ዓመት ጸሐይ መስበል አቅቷት ጭራሮ ብቻ ነው የሚታይበት ለዛውም በደመና የተዋጠ። እንዲህ ዓይነት ምስል ባይመጣብኝ፤ ባለስበው ደስ ባለኝ ግን ሰውን ሰው እዬፈራው ነው፤ ሰው ከሰው ተነጥሎ የመኖርን ሁኔታ የሚያበረታቱ ተጫኝ ሁኔታዎች የሰው ልጅ ሥልጣኔ በራሱ ግማድ ሆኗል።

ተፈጥሮም እራሱ አድነቂ የሚያጣብት ዘመን ይመጣል ብዬ እሰጋለሁኝ። ለተፈጥሮ ጥንቃቄም አይደረገም፤ ተፈጥሮ ደኖች፤ የዱር አራዊታት ደስታን ፈጣሪ ናቸው። ደስታ የሚገኘው ደግሞ የምታዬውን ስታፈቅረው ነው።

ስለዚህ ዓለም ማድረግ ያለበት የመጀመሪያው ጉዳይ የፍቅርን ተፈጥሮ  ዕውቅና መስጠት ነው። ፍቅር ሲባል በሥርጉተ ፍልሥፍና የሁለት ተቃራኒ ጾታዎችን ብቻ አይደለም፤ የ አገር፤ የሙያ፤ የሆቢ፤ የመክሊት፤ የ ዕውቀት፤ የቀለም፤ የሰንደቅ ዓላማ፤ የሃይማኖት፤ የፍልስፍና፤ የፖለቲካ፤ የምህዋር፤ የሃሳብ፤ የ እንሰሳት፤ የተፈጥሮ ውጤቶች፤ የ እሳተ ጎመራ፤ የውቅያኖስ፤ የምግብ፤ የስፐርት፤ የጥበብ ወዘተ ወዘተ … ፍቅር ዲካ የለሽ ነው …

በሞራላዊ ዕሴትም ስንመጣ፤ ጽናት፤ ምስጋና፤ አክብሮት፤ ዕውቅና፤ ተቀባይነት፤ አድናቆት፤ ለውጥ፤ መቻቻል፤ መቀበል፤ መስጠት፤ ትህትና፤ ጽናት ትዕግስት፤ መታመን፤ ማመን፤ ድምጽ፤ ቃና፤ ቅላጼ፤ ዕንባ፤ ሳቅ፤ ፈገግታ፤ እርህርህና፤ ማዬት፤ ማድመጥ፤ መናገር፤ መቻል፤ አይ፤ አዎን፤ ይሁን፤ አይሆንም፤  ዕውነት ፤ ቅንነት፤ ማስተዋል፤ መመራመር … ድንጋጌ፤ ዶግማ፤ ቅኖና  ወዘተ ….

ስለዚህ ለዘርፈ ብዙ ሁልአቀፍ የመፍትሄ አዛውንት ለሆነው የፍቅር ተፈጥሮ መርሁዎች  የትምህርት ሥርዓት መንደፍ፤ ለመምህራኑ ሥልጣና መስጠት፤ የትምህርት መሣሪያዎችን ማዘጋጀት፤ የትምህርት ተቋማትን መክፈት፤ ወርክሾፖችን ማደረጃት፤ ሰሚናሮችን ውይይቶችን ማቀናበር፤ መምራት። 

ዓለም ዐቀፍ የፍቅር ቀን፤ የፍቅር የመንገድ ላይ ትሪኢት፤ የፍቅር ሙዚዬም፤ የፍቅር ተፈጥሮ መርሆችን ላይ ያተኮሩ ቋሚ የቴሌቪዥን፤ የራዲዮ፤ የበራሪ ጹሑፍ፤ የመጋዚን፤ የፊልም፤ የቲያትር፤ የሥነ - ሥዕል፤ የሥነ - ጥበብ ሥራዎች ላይ መትጋት አለበት።

እራሱ የት/ ቤቶች ሥያሜዎች „መከባባር፤ መቻቻል፤ መታመን፤ ትዕግስት፤ መቻል ….“  ይህን እንግዲህ እኔ በ2015 ሠርቼ የላኩት ነው ለተባባሩት መንግሥታት ጽ/ ቤት እና ለሌሎችም … ሌሎችም ዝርዝር ጉዳዮች አሉ … ምንም ምላሽ ሳጣ ነው ደግሞ ሃሳቤን በዩቱብ የቃላት ፖስተር ቻናል የጀመርኩት …

የፍቅር ተፈጥሮ ፍልስፋና ነው። የፍቅር ተፈጥሮ ሳይንስም ነው። ፍቅር ግን ቁጥር አይደለም። ነገር ግን የፍቅር ተፈጥሮ አንድም ሳይንቲስት፤ አንድም ተማራማሪ፤ አንድም ኤክስፐርት፤ አንድም የምርምር ማዕከል፤ አንድም ተቋም የለውም።
ፍቅር ህሊናዊ ዕሴት ነው። ህሊናዊ ዕሴት ደግሞ በጥረት፤ በድካም፤ በልፋት፤ በንግግር ጥበብ፤ በመሆን ጥበብ፤ የሚመጣ ነው  … 

ለዚህ ደግሞ ዓለም በጀት መድባ፤ ትምህርት ቤት ከፍታ፤ ኮሌጅ ከፍታ፤ ዩንቨርስቲ ከፍታ የፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎችን ሳይንቲስቶችን፤ የፍቅር ተፈጥሮ መርህ ፈላስፋዎችን፤ የፍቅር ተፈጥሮ ኤክስፐርቶችን፤ የፍቅር ተፈጥሮ መርህ የምርምር ማዕከል ማቀድ እና መከወን ይጠበቅባታል። ይህን ካላደረገች ከ50 ዓመት በዋኋላ ዓለምን በሰውኛ፣ በተፈጥሮኛ ሳይሆን በማሽነኛ፣ በግለኛ መርሆዎች ተውጣ ነው እኔ የምትታዬኝ። ግራጫማ ዓለም ነው ለወደፊት የምተታዬኝ። 

አሁንም ግራጫማ ሰብዕና ያለቸው ጥቂት የዓለም ዜጎች ቢኖሩም በመጪው 50 ዓመት ግን እነዚህ ግራጫማ ሰብዕናዎች ተጫኝ ወሳኝ የመሆን ዕድል ይኖራቸዋል፤ ምክንያቱም ልጓም አልቦሽ ስለሆነች ዓለም።

  v   ሉላዊ የባጀት ፍሰት እና ቅይጥነቱ።
ዓለም ቁጥር የለሽ ባጀት ለአውዳሚ ኬሚካሎች፤ ቦንቦች፤ ሚሳዬሎች፤ ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ታወጣለች። ሰውን ሳታበጅ ለሰው ቅንጦት ለሚውሉም ሰፊ በጀት ትመድባለች፤ ግን የሰው ህሊና ከመዳፏ እዬወጣ ነው …

አውሮፓ ህብረትም የሚለው የህብረቱን አገሮች ዜጎችን በባህል ማስተሳስር የጀመርነው መልካም ነገር ነው እሱን ብናጠናክረው ትውልዱን ይቀርጽልናል የሚል መልስ ነው የሰጠኝ። ችግሩ አልገባቸውም። በፍጹም በርቀት በምናብ አላዩትም። የፍቅር ተፈጥሮ መርሁ በተለምዶ እኮ ነው የሚኖረው። ለዚህ ነው ከሚጸኑት ጋብቻዎች የሚፈርሱት የሚልቁት። 

አውነተኛው አለ ቢባል ኢሚንት ነው፤ ከዚህ ከኢሚኒቱ የሚወጡት ልጆች ደግሞ ቤት ውስጥ ያዬትን፤ የሚወርሱትን በጓዊ አውንታዊ አምክንዮ የሚፈርስ ውጪ ይጠበቃቸዋል፤ ስለዚህ ውጤቱ ግራጫማ  ይሆናል … ምክንያቱም ነጭ ልብስ ለብሰህ ውጪ ስትወጣ በጭቃ የተበጠበጠ ውሃ የሚረጭ መንፈስ ከኖረ ነጭነቱን ውጦ ነግሥ የሚወጣው ያው ብልሹው ኮትና ሱሪ ነው … ዓለምም እንዲህ ናት።
ለዚህም ነው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ገና ለእጩነት ሲቀርቡ „አስመሳይ ነው፤ ዕውነተኛ“ አይደለም የሚል ሰይጣናዊ መንፈስ ጎልብቶ እኔን ሳይቀር ሰውን ወደ ተሳሳተ መንገድ እዬመራሸው ነው አቁሚ የሚል መልክት ዱላውን አዝሎ በ ኢሜል ሲያጣድፈኝ የነበረው። ምክንያቱም ሰዉ አቅሉ ያለ ከቁሳዊ ጋር ነው ተጣብቆ የሚገኘው።

  v   የፍቅር ተፈጥሮ መርህ የመራቸው 100 ቀናት።
ይህ የፍቅር ተፈጥሮ መርህ በራሱ ውስጥ የበቀለ እንጂ ድንገቴ አይደለም። ድንገቴሜ አይቀጥልም። ተቋራጭ ነው። ተለጠፊ ስብዕናም አይቀጥልም አቋራጭ መንገድ ላይ ተጎርዶ ነው የሚቀረው።

አሁን ኢትዮጵያ ያሉት የ100 ቀናት ትንግርት እንግዲህ ለእኔ የፍቅርን ተፈጥሯዊ መርህ በመቀበል፣ እውቅና በመስጠት፤ ዕውቅና በሰጡት መስመር ሰው መሆንን ማስጀመር አህዱ ስለተባለ ነው። ሠው ተፈጥሯል ግን ሰዋዊ ባህሪ እንዲኑረው ህሊናውን መሥራት ነው  የአብይ መንፈስ ከሰማይ የተመረቀው መልዕክቱ። አዝማቹም ዘማቹም የፍቅር ተፈጥሮ መርህ ነው። ይህ  የጀመረበት ዘመን በመሆኑ ነው ለውጤት የተበቃው። ፍጥነቱም እንደ ብርሃን የሆነው የፍቅር ተፈጥሮ የማያሸንፈው እንዳችም ፈተና ስለሌ ነው።

ይህን ቀደም ብዬ በጠቅሰኳቸው ሲናርዮዎች አማካኝነት ወደ ተግባር ለመወለወጥ ኢትዮጵያ ሥራ መጀመር አለባት። ሰው እና እንጨት ተሰባሪ ስለሆነ። ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ፍቅር ተፈጥሮ ህግጋትን የምታሥተምርበትን ካሪክለም፤ የትምህረት መሳሪያ ማዘጋጀት ይኖርባታል። ይህን የአሜኑን መንፈስ ማስቀጥል፤ ማጽናት፤ ማደራጀት፤ ማዝለቅ ትችል ዘንድ። ተቋም መፍጠር አለበት።

ይህም ብቻ አይደለም ቤት ውስጥ ሚኒ የመወያያ መድረክ፤ ቀበሌ ላይ፤ ሥር ቦታ፤ ወረዳ ላይ በብሄራዊ ደረጃ የፍቅር ተፈጥሮ በአጀንዳ ውይይት የሚደረግበት መንፈስ መፍጠር ግድ ይላታል። Mindset እንደ አስኳል ወስዶ የፍቅርን ተፈጥሯዊ መርሆዎች ማዕከል አድርጎ እነኝህን ተግባራት የሚከውናባቸው ብሄራዊ መሥመሮች ቢዘራጋ መልካም ነው። ስለ ፍቅር ተፈጥሮ ጥልቅነት ውቅያኖስ፤ ሰማይ እና መሬት ቢደመሩ አይዘለቀውም። ምክንያቱም በጥልቀት ስትይዙት እና አንዱን ቃል ነጥላችሁ ተያያዥ፤ ተወራራሽ፤ ተሳቢ እና ሳቢ፤ ስበቃ ፈጣራነቱን እና በስበቃው ውስጥ ያለው ፍጭት እና ሂደቱን ልመርምርህ ስትሉት የወራት ጉዞ ነው። አንዱ ቃል። ለምሳሌ „ምስጋን፤ ምህረት፤ ይቅርታ፤ እርቅ፤ መቻቻል“ ወዘተ …

  v   ሉላዊነት።
አንዲት አገር ብቻዋን ለፍቅር ተፈጥሮ ዕውቅና ብትሰጥ ይቻላታል። ፍቅር ሙያ ነው፤ ፍልስፍና ነው ብላ ብትቀበል፤ ፍቅር ሳይንስ ነው ብላ በትወሰን ሌላም ፈተና ደግሞ ይኖርባታል። ሉላዊ ያልሆኑ ነገሮች ፈተናቸው ግዙፍ ነው። ስለምን? ኑሮ ጉዞ ስለሆነ በመምጣት እና በመሄድ የሚናዱ እና የሚገነቡ ጉዳዮች ይኖራሉ፤ ይሄም ማለት ከሌላ አገር ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡት ይህን መሰል የለማ ተግባር ሊጠብቃቸው ይችላል፤ ኢትዮጵያ ተግታ ከሰራችበት፤ ከኢትዮጵያ ወደ ሌላ አገር የሚሂዱ ሰዎችም በዬሄዱበት መሰል ተቋማት ካልተፈጠረ አሁንም ታጥቦ ጭቃ ነው የሚሆነው።

ወጥ የሆነ የዕውቅና እና የመተግበር ተነሳሽነት ግድ ይላል። ከውጪ የሚገባወም ከእነ ጓዙ ነው የሚገባው። ለዚህ ነው በሴራ ፖለቲካ የባጀው ሊሂቅ ወደ አገሩ ሲገባ በወል በዚህ መንፈስ ውስጥ  በአብይ መንፈስ እንደገና መጥመቅ ያስፈልገዋልም የምለው። ንድፈ ሃሳቡ ብክል ነው።

መሪ መሪነቱ ውስጥ አልነበረም። ስለምን? ሰውን የማበጀት ትልቁን ሥራ ስላልጀመረው እሱም ስላልተበጀ። ስለዚህም ተከታዮቹም እንዲሁ ነው … በዬአካባቢው ትልቁ ሥራቸው የሰውን ሰላም ማወክ ነው … ያ ነው የአንድ የፖለቲካ ድርጀት ትልቁ ፖሊሲ ነዳፊነቱ የሚረጋገጠው። የሚገርመው ፈርሰው እንኳን በመፍረሳቸው መንፈስ ውስጥ ያሉትን እኩይ ነፍሶችን ለመግራት አቅም የለም። … ይህን ባይረስ ተሸክሞ ቅልቅሉ ከተኖረው በላይ ግዙፍ ነው …

አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ክስተት ከተፈጥሮ እና ከሰው የተነሳ ነው። ለዚህም ነው እኔ ከዴሞክራሲም በላይ ነው የምለው። ስለዚህም ነው „የሽግግር መንግሥት ብሄራዊ እርቅ“ የሚባሉት ከአሁኑ አብይ መንፈስ ጋር ማጠጋጋት የማልችለው። እነኝህ ሃሳቦች ቁሳዊ ናቸው። ማተርያላዊ ናቸው፤ ሥነ - ልባናዊ አቅምን መገንባት ነው ዋናው ተግባር መሆን ያለበት። ሰውን ሆኖ እንዲቆም ሰው አድርጎ እንደገና መፍጠር። ሰው እኮ ለክፋት፤ ለሸር፤ ለሴራ፤ የሰውን ሰላም ለማወክ አልተፈጠረም።
ስለዚህም የፖለቲካ መሪዎች መሪ ያልነበሩ መሆናቸውን አውቀው ሰው ሆኖ ለመጀመርም ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው። 

የሰው ልጅ ሁሉንም የችግር ዓይነት መፍታት አይቻለውም ፍቅር ግን ይቻለዋል። ስለምን ስለተሰጠው? የተሰጠው መሆኑን ደግሞ እያዬን ነው። ፍቅር ብቻ ነው ጎባጣን፤ ጠማማን፤ ወልጋዳን፤ ሸካራን፤ ኮረኮንችን ልጎ ማሰተካካል የሚችለው። እስከ አሁን በተኖረው የፖለቲካ መስመር መልካም ነገሮች ተቀብረው ተፃራሪው የጸላዬ ሰናይ መንፈስ ነግሶ እና ተበራክቶ ነው የተኖረው። ሰውን ለመምራት ሰውን በማጣፈት እያጣፉ ለመምራት ማለም። እፉኝታዊ ዘመን …

  v   ምዕታዊ ታምራት።   
የ100 ቀን ውስጥ ዛሬ ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ዓለመነህ ዋሴ ከሪፖርትር ያገኘውን የራሱንም እድምታ እያከለ አስደምጦናል። ሪፖርትር የዘገበው ውስጣዊ ነው ማለት አልችልም፤ ንጥረ ነገሩ ድርቀት አለበት፤ የቃላት ግጥምጥሞሽ ነው እኔ ያዬሁት። ማለት በለመደው የዘገባ አቀራረብ ሞድ። የ100 ቀኑን መንፈሱን ማግኘት አላስቻለውም፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሠራውንም እንዲሁ እኔ አዳምጨዋለሁኝ። ከተኖረበት ምልከታ እና ዕይታ የወጣ አይደለም። ፖለቲከኞችም፤ ተንታኞችም በዚኸው ስሌት ነው መጪ የሚሉት።

በነገራችን ላይ እጅግ በጣም ብዙ ጉዳዮችንም ዘሎ እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው ዓይነት ነበር ዘጋበው። በዛ ላይ የለውጡን መንፈስ የተረጎመው በጋህዳዊ ምህፃር ነው። ጎርዶ ወይንም ገምዶ ወይንም ጎምዶ። ይልቅ በማህል ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ የሰጠው ማብራሪያ ጥልቅነቱ መስጦኛል።

በቀን እኮ ሦስት አራት መንፈሳዊ ታምራቶች የተከወኑበት ወቅት ነበር። ሥራ አይደለም እኔ ያልኩት ታምራት ነው ያልኩት። ምን ለማለት የሁለቱም የማጠቃለያ ትንተና መንፈሳዊ ሃብት ላይ ለመነሳት አቅም አንሷቸዋል። ለዚህ ድል የበቃው የፍቅርን ተፈጥሯዊ መርህ በጥበብ - በረጋ እና በሰከነ፤ በዕውቀት እና በተመክሮ መስተጋብራዊ ሁኔታ፤ በነቃው የህሊና ክፍል የተማራ ስለሆነ ነው። ሉላዊነትን ባዳመጠ እና ምዕቱን በጥልቀት ባስተዋለ፤ በታቀደ - በታለመ - በወጉ በተደራጀ አኳኋን የተከወነ ነው።

  v   100 ቀናቱ የቀራኒው ተጎለጎታ ጥልቅቱ በጥሞና በመጠኑ …
አደራጅነት፤ መሃንዲስነት፤ አቅጅ እና ፈጻሚነት፤ የማስተባባር እና የማቀናጀት አቅም ከንግግር ጥበብ እና ክህሎት ጋር በውል በተክሊል የተዋዋሉበት፤ ከዲፖሎማሲያው ልዩ መክሊታዊ አቅም ጋር የተዋደደ፤ ከማሰውስን ከመወስን ቁርጠኛ እና ደፋር የእርምጃ አቅም ጋር የተስማማ፤ ከማሳምን ከማምን አቅም ጋር በብልጹግ ብቃት የተካነ፤ ችግርን ከመሠረቱ ከማጥናት እና መፍትሄ ከማፍለቅ ጋር የተዋደደ፤ ሃሳብን ከመፍጠር እና ከመተንተን ጋር የተገናኘ፤ እሩቅ ከማዬት እና ምናባዊ ዕይታን በዘለቄታ ከመሳተዋል ጋር የታመነ፤ ሰው ከማበጀት እና ከመሥራት ጋር መንፈሳዊ ልምድን ከማከፈል ቅናዊ ጥገትን ከመቀለብ ጋር የሆነበት።

ሰው ከማብቀል እና ከማብቃት ጋር የተቃኜ፤ ሰውን ለማዬት ከመፍቀድ እና ሰውና ሰውን ከማወራረስ ጋር በውስጥነት ጋር የተነባበ፤ ሰው ከማገናኘት እና ከማስታረቅ ጋር የመሪነት ክህሎት ከመንፈሳዋ አባትነት ጋር እዬርን ያስከበረ፤ ሰው ስለመፈጠሩ እራሱን አውቆ ደስታውን፤ ፈገግታውን፤ ሳቁን ላለመጣት የራሱ አክቲቢስት እንዲሆን የነቃውን ህሊና የመራ፤ ልዑል እግዚአብሄር የወስጡን ሰላም ሰጥቶን የሄደውን በራስ ላይ ከመፈጸም ጋር ለሌለውም ከማስብ ጋር ያሰተማረ ነበር።

ስልቹ ካለመሆን፤ ከመጽናት እና ከማጽናት ጋር በፍጹም ታማኝነት እና ቅንነት ከማገለገል ጋር ክህሎትን በአዲስ ንጹህ መንፈስ ያጸደዬ፤ በትህትና መሪነት፤ በአክብሮት አጋፋሪነት፤ በመቻቻል ችሎት ሁለገብ ንጥር ተፈጥሮዊ ዕሴቶች ጋር ያስተዋወቀ የሰበከ የዳኜ፤ ልዑል እግዚአብሄር ከፈጠራቸው መልካም ነገሮችን ሐዋርያዊ በመሆነ መልኩ ጋር በጽኑ፤ በጥሞና፤ በተደሞ በዕድምታ በቅኔ የታቃኘ ወቅት ነበር ያሰለፍናቸው 100 ቀናት።

100ሚሊዮን ህዝብ የአገሬ ጉዳይ የፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ነው፤ እኔም የድርሻዬን ብሎ የተነሳበት፤ የተለያዬ መንፈሶች ሁሉ በእርቅ ሰንሰለት ለማያያዝ የተሄደበት አጭር ጉዞ ግን የሺህ ዘመናትን የድንጋይ ሸክም ንዶ እፎይታን የለገሰ፤ ተስፋን ዘርቶ ተስፋን አብቅሎ ተስፋን ያሰበለ ሌላ አዲስ ተስፋን ያሳጨ New Era.


ስለሆነም በዘመናት መካካል የነበረውን የጥል ግድግዳ ንዶ አዲስ የፍቅር ድልድይ የዘረጋ ንጹህ ቅዱስ ብጹዕ መንፈሳዊ ወቅት ነበር አሳለፍናቸው 100 ቀናት። ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን መንፈሱ በተገኘበት አህጉራዊ ባዕቶች ሁሉ ፍቅርን ያሰነቀ፤ ምህረትን ያገባ፤ ርግጠኝነትን ያዋለድ፤ በራስ መተማማን የበራ ነው። አፍሪካ ይችላል ችግሩን ለመፍታት፤ ከድህነት ለመውጣት፤ ተፎካካሪ ተደራዳሪ ድምጽን በድምጸ የመሻር መብትን አምጦ በሉላዊነት የማስከበር ብቃት አለን፤ እንችላለን የመለውን የፓን አፍረካኒዘም ምንፈስ እንደገና ያዋለደ ዕጹብ ድንቅ ወቅት ነበር።

እርግጥ ነው መከራዎች ነበሩበት፤ ዕንባዎች ነበሩበት፤ መስዋዕትነት ተከፍሎበታል፤ የጠሩ የሃሳብ ጉግሶች ተካሄደውበታል፤ በመበተን እና በመሰብሰብም ብዙ ተደክሞበታል ግን፤ ተስፋን ለሰነቀ የአሜኑ ዘመን ፈተናውን ተሻግሮ ሉላዊ ምስጋና፤ ሉላዊ አውቅና፤ ሉላዊ የድጋፍ መልክቶች ሁሉ አግኝቷል። ራሱ የተባባሩት መንግሥታት የሰብዕዊ መብት ቢሮ በሰብ ረገጣ እና ጭካኔዊ መከራ ውስጥ የነበረችው ኢትዮጵያ በአዲሱ ጉዞ ላይ መሆኗ በድንቅ አገላላጽ አብስረዋል ማዕከላዊ ቢሮም አብነቱን ነገ በዓለም አደባባይ መድረክ አግኝቶ የ አብይ መንፈስ ልምዱን እንዲያካፍል የሰብዊነት አንባሳዳር እንዲሆን መሥመሩን ይዘረጋል።

የመጪው 8 ዓመት ለዚህ መንበር ለተባበሩት መንግስታት ጸሐፊነት የማትበቃበት ምክንያት የላትም። እሳር ቅጠሉ የሚመሰክረው ዕውነት ላይ አላዛሯ ኢትዮጵያ ስለምትገኝ። ዳግማዊ ማርቲን ሉተር ኢትዮጵያ ፈጠረች አሜኑን። ተመስገን!
በዚህ ሂደት የታዬኝ ዋናው መሠረታዊ ነገር የሰው ልጅ መገኛ የሆነች አገር ለሰው ልጅ ጤናማ ኑሮ አብነታዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ከወደቀችበት ትቢያ ላይ ተነስታ አዲስ የቀደምትነት ጃኖ የለበሰችበት New Era። 

ስለሆነም ሥነ ልቦናዊ መንፈሳዊ ማራላዊ ትርጉም የጸደቀ እና የበቃ ነበር። እራሱ የተፎካካሪ ፖለቲካ መሪዎች መሪ አልነበራቸውም። ምክንያቱም እራሳቸው መሪ ነን ብለው ያስቡ ስለነበረ፤ ስለዚህም ነው የኦሮሞ ንቅናቄ እና የአማራ ተጋድሎ የተነሳው መሪ ሙሴ በማጣቱ። አሁን ግን ሁሉም መሪ ሙሴ አለው። ሙሴው ደግሞ ከሁሉም በሁሉም ብቁ እና የበቃ የጸደቀም ነው። ለዛውም አንጀቱ ስስ እና እናት ሆዱ ነው።  


  v ሉላዊነትን ሰለማሳረፉ።
ይህ አላዛሯ ኢትዮጵያ የጀረችው ጉዞ ለ ዓለምም እፎይታን አበርክቷል። ዓለም የምትሰገባት የስደተኝነትን የመከራ ጉምም ከበላዮዋ ገፎላታል። አገሮች በቀውስ ውስጥ ሲሆኑ ዓለምን ከሚያስጨንቋት መከራዎች አንዱ ስደት እና ከስደት ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ቀውሶች ናቸው።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የ አፍሪካም፤ የመከከለኛው ምስራቅ አፍሪካም፤  ዓለምም መንፈስ መናህሪያም ናት፤ ልናገራቸው እማልፈቅድቸውን ስጋቶች አክሎ ሰፊ ተስፋ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ እንዲኖራት አድርጓል።

ሌላው ቀርቶ በኤርትራ ጋር የተፈጠረው ተስፋ ብቻ ሳይሆን አውሮፓን ምርር ያደረገው የስደተኛ መበራከትም ሌላው የጉም መከራ በአጭር ጊዜ ባይሆንም ረጅሙ ጊዜ ሲታሰብ የተሻለ የተስፋ ብርሃን በዚህ የስምምነት ሂደት ይኖራል ብላ ዓለም ታስባላች።

በኢትዮጵያ የሰብዕዊነት መከራም ላይ የተጉት ታላቅ ሸክም ወርዶላቸዋል። ይህን ስል ይህ የሽግግር ጊዜ ስለሆነ በዚህ ወቅት ያሉት፤ ወደፊትም ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮች እንደ ተጠበቁ ሆነው። ለዛም ኢትዮጵውያን ወገኖቼ እዬባዊነትን መሰነቅ ግድ ይላቸዋል። የተስፋ አገራቸውን ለማዬት የሚጓጉ ከሆነ። የትውልዱ ብክነት መንፈሳቸውን ካጎሳቀለው።    
  • ·       የኔዎቹ ቅኖቹ ግዜው ካላችሁ ታደሙበት …

Compact 23, Love Nature’s Relationship (Chapter Three) 7/11/2018
  • ·       ማነጻጻሪያ ምርኩዝ።

awaze news
  • ·       ክውና።

አውሬ የትም አለ። አውሬ አጀንዳችን ሊሆን አይገባም። አውሬው የትም ቦታ ሽንፈት ስለተጋተ። ምርጫው ወይ ይደመራል፤ ወይ ደግሞ ይጠፋል። መሸነፍን መቀበል አዋቂነት ቢሆነም መሸነፍን አለመቀበል ደግሞ ሰዋዊነትነት መቀበር ነው። ተቀብረን እንኖራለን ለሚሉም መብታቸው ነው በስልክ ረብሻቸውን ይቀጥሉ፤
ከፈረሰ ናዳ እና ከተነፋ ባሎን የሚጠበቅ ብጣቂ ሞራላዊ ትፍስህት ስለሌ። ባዶ ቆርቆሮ ነው እንደ ማይክ ላይ እንደ ጮኽ የሚኖረው …
ብትን የመንፈስ ፍርፋሪ መለቃቀም የተለመደ ነው … መሪዎችማ አዬን እኮ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በሉላዊነት በ100 ቀን ገድል፤ ትንግርት፤ ታምራትን ሲፈጥሩት፤ ሲሰሩት ሲያባጁት …
የፍቅር ተፈጥሮ ቁጥር አይደለም !
የፍቅር ተፈጥሮ ሳይንስም ፍልስፍናም ነው !
የፍቅር ተፈጥሮን ላልተቀበል የነቃው ህሊና አልተፈጠረለትም !
ሰነፎች በዬፌርማታው የሚገጥማቸው ውድቀታቸው ይመራቸዋል !
ሊቀ ትጉሃን በዬሰከንዱ የመንፈስ ሰብልን በዝቀሽ አምርተው ከጎን ያሰልፋሉ !
የሊቀ ትጉሃን ዘመን ይለምልም !
ቅኖቹ የኔዎቹ ደጎቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።