ልጥፎች

ከኦክቶበር 15, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የፋክት #ፍልሰት #በፍድሰት።

  የፋክት #ፍልሰት #በፍድሰት ።    "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   መጥኒ ላንች ማህፀንሽ ማገዶነቱ አባርቶ ለማያውቀው ገራገሯ የአማራ እናት። ከዬት እንደምጀምር አላውቅም። ሰሞኑን ዶር ዳኛቸው አሰፋ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ በሚመለከት የራሳቸውን ዕይታ አቅርበዋል። በህዝቡ መንፈስ ውስጥ እራፊ መሬት ካገኙ ጊዜ ይዳኜው። እንደ እኔ ግን ኮነሬል ደመቀ ዘውዱ የተመሰጡበት ዴሞክራሲያዊ አቋም የፋክት ፍልሰት እና ፍድሰት ሆኖ ነው ያገኜሁት። ይህን ያህል ከገዢው ድርጅት " ከብልጽግና" መንግሥት ጋር መተማመኑ ካለ ስለምን ባጀት አይለቀቅላችሁም????   ዶር ዳኛቸው አሰፋ በንግግራቸው ውስጥ ብዙ የማያውቁትን ማብራሪያ ሲሰጡ ሰምቻለሁኝ። ከዚህ ቀደምም። እሳቸው ያልፈፁምትን፤ ወይንም ያላስፈፀሙትን ጉዳይ እንደ ፍልስፍና ሙሁርነታቸው እንደዛ ደፍረው ሲናገሩ ገረመኝ። "አወዛጋቢ ቦታወች" የደቡብ አፍሪካ ስምምነት ያመነጨው ነው።    " ምዕራብ ትግራይ" የሚለው ግን ጥቅምት 2022 ስምምነቱ ተከናውኖ፤ እስከ ሰኔ 2023 ድረስ ከተከበሩ አንባሳደር ማይ ሃመር ኤክስ ገፃቸው ላይ ሄደው ይፈትሹ። ይህም ብቻ አይደለም የኤርትራ መንግሥት እንደ መንግሥት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ መንግሥት፤ ህወሃት እንደ ክልል ባልተጠዬቁበት ሦስት ወንጀል የአማራ ልዩ፤ ኃይል፤ ፋኖ፤ እና የአማራ ሚሊሻ በሦስት ጣምራ ወንጀል ነበር ሲከሰስ እማዳምጠው። ከቦታው ስላልነበርኩ ዕውነቱን ማወቅ አልችልም።   በሰው ልጅ ላይ ግፍ የፈፀመ መጠዬቅ ግድ ነው። ማንም ይሁን ማን። ተጣርቶ ብዬን ከተሰጠበት። ግን ሁለቱም መንግሥታት እና ህወሃት በጦር ወንጀል ብቻ ሲከሰሱ ዬአማራ ፀጥታ ኃይል ግን #በሦስት ወንጀል ተከሳሽ ነበር። ...