ደጉ አቶ ዮሴፍ ገብሬ፤ ተባረክ!
የማስተዋል አንበል። „ደግ ሰው ግን ለሞመት በደረስ ጊዜ በ ዕረፍት ይኖራል።“ መጽሐፈ ጥብብ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=9ndpRVHlBG8 „Jossy In Z House የአዲስ አመት ዘመድ ጥየቃ ከኢንጅነር ስመኘው ቤት“ ደግነት ለራስ ቢሆንም ትውልድን በማነጽ እረገድ ተቋም ነው። የደግነት ተፈጥሮ ሰላምን ይሰጣል። መጀመሪያ ሰላም የሚሰጠው ለራስ ነው። ሲቀጥል ለቤተሰብ ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ በመንፈስ ታለቅሳለች - ሲከፋት። በመንፈስ ታናባለች - ሲጨልምባት። በመንፈስ ትሰጋላች - አዬሩ ሲታወክ። በመንፈስ ሰላሟ ይታወካል ልጆቿ - ሲበተኑባት። ኢትዮጵያ ልጆቿ ሲጠነክሩ እሷም - ትጠነክራላች። ልጆቿ ሲዝሉ እሷም - ትዝላለች። ልጆቿ ተስፋ ሲኖራቸው እሷም - ተስፋ ይኖራታል። ልጆቿ ተስፋቸው ሲደርቅም እሷም - ክው ትላለች። ልጆቿ ቅስማቸው ሲሰበርም እሷም - እንኩት ትላለች። እናት እኮ ናት - አገር። አንጀት ናት የትወልድ ባዕት። ህሊና ናት የነፍስ ባድማ። ልክ እንደ ሰው ነው ጠረኗ። እንዲህ ደግሞ በክፉ ቀን፤ ሰው በጠፋ ቀን፤ ቀን ፊቱን ባዞረ ዕለት፤ አዬሩ በከፈው ማዕለት፤ ተስፋው በራቀ ዕለት፤ ስጋቱ አገር ምድሩን በረቂቅ ባከለለው ሰዓት አንድ እንደ ወልዴ የዛን የበርሃ ከልታማ ቤተሰብ ሄዶ መጠዬቅ ምን ይባል? አለሁላችሁ፤ አይዟችሁ ከአዘቦቱ ቀን ይልቅ ይህ ቀን ወሳኝ ነው። በምን መስፈርት ይህ ደግነት ይተርጎም? በምን ሜትር ይህ ቸርነት ይለካ? በምን ደረጃ ይ...