ደጉ አቶ ዮሴፍ ገብሬ፤ ተባረክ!
የማስተዋል አንበል።
„ደግ ሰው ግን ለሞመት በደረስ ጊዜ በ ዕረፍት ይኖራል።“
መጽሐፈ ጥብብ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፯
ከሥርጉተ©ሥላሴ
12.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
- · መነሻ።
„Jossy
In Z House የአዲስ አመት ዘመድ ጥየቃ ከኢንጅነር ስመኘው ቤት“
ደግነት
ለራስ ቢሆንም ትውልድን በማነጽ እረገድ ተቋም ነው። የደግነት ተፈጥሮ ሰላምን ይሰጣል። መጀመሪያ ሰላም የሚሰጠው ለራስ ነው። ሲቀጥል
ለቤተሰብ ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ በመንፈስ ታለቅሳለች - ሲከፋት። በመንፈስ ታናባለች - ሲጨልምባት።
በመንፈስ ትሰጋላች - አዬሩ ሲታወክ። በመንፈስ ሰላሟ ይታወካል ልጆቿ - ሲበተኑባት።
ኢትዮጵያ
ልጆቿ ሲጠነክሩ እሷም - ትጠነክራላች። ልጆቿ ሲዝሉ እሷም - ትዝላለች። ልጆቿ ተስፋ ሲኖራቸው እሷም - ተስፋ ይኖራታል። ልጆቿ ተስፋቸው
ሲደርቅም እሷም - ክው ትላለች። ልጆቿ ቅስማቸው ሲሰበርም እሷም - እንኩት ትላለች። እናት እኮ ናት - አገር። አንጀት ናት የትወልድ ባዕት።
ህሊና ናት የነፍስ ባድማ። ልክ እንደ ሰው ነው ጠረኗ።
እንዲህ
ደግሞ በክፉ ቀን፤ ሰው በጠፋ ቀን፤ ቀን ፊቱን ባዞረ ዕለት፤ አዬሩ በከፈው ማዕለት፤ ተስፋው በራቀ ዕለት፤ ስጋቱ አገር ምድሩን
በረቂቅ ባከለለው ሰዓት አንድ እንደ ወልዴ የዛን የበርሃ ከልታማ ቤተሰብ ሄዶ መጠዬቅ ምን ይባል? አለሁላችሁ፤ አይዟችሁ ከአዘቦቱ
ቀን ይልቅ ይህ ቀን ወሳኝ ነው።
በምን
መስፈርት ይህ ደግነት ይተርጎም? በምን ሜትር ይህ ቸርነት ይለካ? በምን ደረጃ ይህ ማስተዋል ይመዘን? ይገርማል እጅግም ይደንቃል።
ይህ ቅን ወጣት አቶ ዮሴፍ ገብሬ እነዚህን ወላጅ አልባ የመከራ ወጀብ እንዳሻው በተስፋ ማጣት እና በስጋት በሚንጣቸው ጎጆ ተገኝቶ
አይዟችሁን ቀለባቸው። የተባረከ። የተቀደሰ። የተመሰገነ።
ይህ
ቀን ለልጆች የተስፋ ቀን ነው። ወደ ት/ ቤት ሊገቡ የሚሰናዱበት፤ በወላጆቻቸው የተለያዬ ስጡታ የሚያገኙበት፤ እነሱም አድዮ ቆርጠው
ስዕል ስለው እንቁጣጣሽ ብለው ስትዳር // ስትዳሪ ተብለው ተስፋ ዘለግ ብሎ በርግጠኝነት የሚሸለሙበት፤ በጉጉት የሚጠብቁበት ዕለት
ቅዱስ ዮሖንስ።
በጉ
ሲታረድ፤ ፊኛ እዬነፉ የሚጫወቱበት፤ አባባዮሽ ከባልጅንራቸው ጋር የሚደልቁበት ነበር። ነገር ግን ለእነሱ ሁሉንም አልታደሉም።
አባታቸው
እንደወጣ አልተመለሰም፤ እናትም ከሄደችበት አልመጣችም። ምን ዓይነት ዕጣ ፈንታ ነው? ብቻ እኒህ ተስፋ ያጡ ህፃናትን አንድ የየኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ በማዕዳቸው ተገኝቶ እንቁጣጣሽ ብሏቸዋል። ተመስገን!
እሚበሉትማ አያጡም ግን ለተጎዳው ሥነ- ልቦናቸው ይህ
ወሳኝ እርምጃ ነው። አባታቸው አይመለሰም ነገር ግን አባታቸውን የሚተካ መንፈስ ባያገኙም ከጎናቸው የሚቆም ግን ይሻሉ። እነሱም
እኮ ዜጎች ናቸው። እነሱም የነገ ቀጣይ ትውልድ አባል ናቸው። በህይወት ከኖሩ።
ሀዘኑ
ትኩስ ነው። ውሳኔውም ትኩስ ነው። ቀኑ መራራ ነው። አዬሩ ቋያ ነው። ንፋሱ የሚያነባ ነው። ስጋቱ ታገራፊ ነው። ካለ ዕድሚያቸው
የተሸከሙት ፖለቲካዊ አመክንዮ አለ። የሆነ ሁሉ ለነዚህ ቀንበጦች ህሊና እጅግ የገዘፈ ውሃ ያዘለ ተራራ ነው።
ባልኖሩበት፤ ባልወሰኑበት፤ ባላቀደቡት ሁኔታ ጎመራው የእነሱን መንፈስ ያልርህራሄ ይንጠዋል። ከባድ ጉዳይ ነው ለህጻናት እንዲህ መሰል ውስብስብ ትብትብ ችግር። ወላጆች ተንከባክበው ለማያሳዱጉት የልጆች ህሊና ባይወልዱት ይመረጣል። ወንጀልም ነው። ቢያንስ እናት ጎን አለመኖር? ስንቱን ይቻሉት እነዚህ ፍሬዎቻችን? ማግስትን እንዴት እና በምን ሁኔታ ይቀጠልላቸው?
ሁሉም ጉማም ነው ለእነዚህ ፍሬዎች። እና በዚህ ድቅድቅ በዋጣቸው ዓውደ ዓመት ዕለት ከጎናቸው
መቆም የመሰለ የቁም ጽድቅ የለም። ይህ የተባረከ ወጣት የከወነው ተግባር የሁላችንም ሃላፊነት ነው የተወጣው። ሃላፊነትን መከፋፍል ማለት ይህ ነው። ስለሆነም ቢያንስ
በጸሎት እባካችሁ እንርዳው።
የነፍስ
ጌጥስ በመከራ ጊዜ ከወገን ጎን መቆም ነው!
የኔዎቹ
ኑሩልኝ።
ማለፊያ
ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ