ነገረ ጋዜጠኛ መሳይ ...

በመሆን ውስጥ ብዙ ፈተና አለ።
„መተለላፉ የቀረችለት፤ ኃጢያቱም 
የተከደነችለት ምስጉን ነው።“
መዝሙር ምዕራፍ ፴፩ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 12.09.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።


  • ·       መነሻ

„የከንቲባው ነገርመሳይ መኮነን“

·       ወግ ቢጤ …


መርጋዊ ፈተና ያለው በመሆን ውስጥ ነው። በመሆን ውስጥ ያለው ፈተና ደግሞ መጀመሪያ የሚያጠቃው የራስን ሰብዕና እና ሞራላዊ አቅም ነው። በራስ ሰብዕና ውስጥ መሆን እንዲገኝ ከተፈለገ ዕውነትን መድፈር ይጠይቃል። ዕውነት ተፈጥሮ አለው። ዕውነት የኖረው ሆነ ወደፊትም የሚኖረው በተፈጥሮው ውስጥ ነው። ዕውነት አምላኪነቱ ለተፈጠረበት ዕውነት ብቻ ነው።

ዕውነት ዳኛ የሚሆነው በተፈጥሮ ውስጥ ለመኖር ለፈቀዱት ብቻ ነው። አሁን እኔ በጸሐፍት ውስጥ የማዬው ዕውነት እንደ ፍልጎታችን፤ እንደ ዝንባሌያችን፤ እንደ ስሜታችን ሆኖ ነው በአብዛኛው ጊዜ። ከዚህ የወጡ ጸሐፍት ደግሞ አሉ ለምሳሌ የኢኮኖሚ ሊቀ ሊቃውነቱ እና ጸሐፊ ዶር ፈቃዱ በቀለ።

እሳቸው ጹሁፋቸውን ሲያዋቅሩት መሰረታቸው፤ መደወሪያቸው፤ ባላ እና ወጋግራው ሆነ ሰቁ ሁሉመናው የሚዋቀረው በፋክት ላይ ነው። ስለሆነም ሁኔታዎች እውሃ ቅዳ አውሃ መልስ ቢል፤ ወጀብ ቢናጥ፤ አውሎ ቢጋልብ፤ ማዕበል ቢጎርፍ ንቅንቅ አይልም የጹሁፋቸው መንፈስ። 

መቼም አንድ እና አንድ ሲደመር ሦስት ሆኖ አያውቅም ወይንም ራሱን መልሶ አንድ ሆኖ አያውቅም። ያው ሁለት በቋሚነት ነው የሚሆነው። ቁጥሮቹ በተለያዬ ቀለማት፤ በተለያዬ ዲዛይን፤ በተለያዬ ስፋትና እርዝመት ይጻፉ አንድ እና አንድ ሲደመሩ ሁለት ብቻ ነው የሚሆኑት። ድምሩ ቋሚ ነው። የዶር ፈቃዱ በቀለም የጹሁፍ መንፈስ እንዲህ ነው።

ፋክቱ ነው የክስተቱ ደጋፊም ተቃዋሚም የሚሆነው እንጂ ስሜቱ ወይንም ፍላጎቱ አይደለም። የሳቸውን ጹሁፍ ለረጅም ጊዜ ለተከታተለ ሰው የፈለገ ሥርዓት ቢቀዬር ወይንም ቢለወጥ የፈለገ አመለካክት ቢመጣ ወይንም ቢሄድ ያው ነው የዛሬ 10 ዓመት የጻፉት ዛሬ ላይ ቢነበብ ያው ፋክት ነው። የሚወድቅ ነገር የለውም። አብሶ ለኢትዮጵያ ሚዲያ ሞራላዊ ሂደት ይህ በእጅጉ ያስፈልገዋል። 

ዕውነት እንደ ዘመኑ ሳይሆን ዕውነት እንደ ተፈጥሮው እንዲሆን ሊፈቀድለት ይገባል። ዛሬ የጋዜጠኛ መሳይ መኮንነን ጹሑፍ አነበብኩት። በአዎንታዊነት የምክትል ከንቲባን አቶ ታከለ ኡማን ብቃታቸውን ይዘረዝራል። ይህን ቀድሞ ማዬት መቼም የአንድ ጋዜጠኛ ሥነ - ምግባሩ ነው። 

ፊት ለፊት ብዙ ቀናት ወራት እያሉ አስቀድሞ አብጠልጥሎ ሥልጣኑን ለእከሌ ስጡ አትስጡ፤ ልምድ የለውም፤ አዲስ አበባን አያውቀውም፤ ያው ከተለመደው የወል መንፈስ ያልወጣ ውጊያ ነበር። ያን ጊዜ ያን መክቶ ባልደረባን መሞገት አንድ ነገር ነው።

አሁን „አያጅቦ ሳታማህኝ ብላኝ አይነት ነው።“ ለኢሳት ሆነ ለፕሮ ግንቦት 7 ሰው አይደለም መለኪያው፤ ብቃት አይደለም መስፈርቱ፤ ሞራል አይደለም ዕውቅና የሚያሰጠው። የግንቦት 7 ክብር እና ልዕና በመስጠት እና ባለመሥጠት ነው አንድ ሰው ሰውም ነው አይደለም ተብሎ የሚለካው የሚፈረጀው።

 ጀግንነትም እንዲሁ ነው። ታታሪነትም እንዲሁ። ዜግነትም የሚሰጠው እንዲሁ፤ በግንቦት 7 እኮ እኛ ዜጎች አይደለንም። ዘግነታችን ተንበርክከን ብንለምነውም አይሰጠንም። በጣም የሚናፍቀኝ የግንቦት 7 ንቅናቄ ሆነ ተከታዮች መጨረሻ ነው። መቼ በዬትኛው ዘመን በፋክት ላይ ድጋፍ እና ተቃውሞ እንደሚያደርጉ ይናፍቀኛል። 

አሁን አዲሱን ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ላይ ስንት ማዕት ወረደ። የአሁኑ ድጋፍ ሰንበት ላይ የፖለቲካ ድርጅቱን ግንቦት 7 በስቲዲዬም ምክንትል ከንቲባው አቶ ታከለ ኡማ አቀባበል አድርገዋል በቃ ይህ መስፈርቱን አሟልተዋል። ስለዚህ አሁን ቅዱሰ ቅዱሳን ናቸው ባለ 6 ክንፍ።

ዛሬ አይደለም ቲም ለማ መሆናቸው የሚታወቀው። ከቲም ለማ ፈቃድ ውጪ መቼም አንድም ሰው ወደ ፊት እንደማይመጣ ቀድሞውንም ይታወቃል። ነገር ግን ራሱ ቲም ለማ በምን ሁኔታ ሲብጠለጠል እንደባጀ አገር ያውቀዋል፤ እንኳንስ አሁን የመጡት አቶ ታከለ ኡማ ቀርቶ።

ማጥናት የለም፤ መመርመር የለም፤ በቃ! በአሉታዊነት መውቃት ነው። የሚገርመው አቶ ታከለ ኡማ የቅኔው ልዑል የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንም የሥጋ እና የደም ቤተስብ ናቸው። አዎና! 

እግዚአብሄር ረድቶን የሎሬቱ መንፈስ አቅም ኖሮት፤ ችሎታ ኖሮት ቦታ ቢሰጠው፤ ቢያንስ ሳናውቀው ፍልስፍናው ሳይገባን አፍሰነው አባክነነው፤ የሎሬትዝም ተቋማዊ ፍልስፍና አንድም ውለታ ሳንከፍለው ለኖርንበት ዘመን ካሳም፤ እግዚአብሄር ይስጥልንም በሆነ ነበር ልብ ላለው። ማስተዋሉን ለሰጠው። አቅሙ ከኖረ፤ ከዚህ ደረጃ የመድረስ ክህሎቱ ያለው ቤተሰብ ከኖረ ዕድለኝነትም ነው።  

ሎሬትዝም አፍሪካኒዝም ነው። ሎሪትዝም ሉላዊ ጥበቢዝም ነው። ሎሬቲዝም መሆኒዝም ነው። መንፈሱ በራሱ፤ ቅኝቱ በራሱ፤ ጠረኑ በራሱ የሙሉ ሰብዕና ልዩ መለያ ነው። ግን በጀምላ ማጨድ፤ በደቦ ማራካስ፤ ማብጠልጠል፤ ማቃለል ነው ትጋቱ። ተው! የሚል ሽማግሌ የለም። ፓርቲ የሚባለውም ከመርህ ውጪ ለሆኑ ወታደሮቹ ሲያርም፤ ሲገስጽ፤ ሥርዓት ሲያስዝ ታይቶም ተስምቶም አይታወቅም።

እንዲያውም ጀብዱ ነው። አቅም በተሰበረ ቁጥር አቅም የሚፈጥር ይመስላል።
ቀድሞ ነገረ ቲም ለማ ባይሳካለት ኖሮ እኮ የዛሬ ምንትሶ ዓመትም ቅስቅስ አይባልም ነበር። የኩሬ ውሃ። 

ዕውነት እጅ ላይ ሆኖ እየመሰከረ፤ እዬተናገረ ፤እየመዘነ ተመልካች አልነበረውም። በሽታሽቶሽ ተሰልቆ፤ ዕውነት አከርካሪው ተሰብሮ፤ ተስፋ ክው ብሎ እንዲደርቅ ነበር ዘመቻው። ጹሁፎቹ፤ ውይይቶቹ ሁሉ ቢለቀሙ ዛሬን ለማግኘት በመሆን ውስጥ ያተባጀውን ፈተና መመዘን ይቻላል።

እንደ እኔ ሊንኮችን ሁሉ ለማምሳከሪያነት ለሚይዝ ሰው ዕውነት በመሆን ውስጥ ያለፈበትን መከራ ሳይሆን ወደፊትም የሚገጥመው ፈተና ቁልጭ ብሎ ያሳዬኛል። በስህተት ውስጥ ሆነ እንኳን ስህተተኛ አይደለም የጋዜጠኛ መሳይ መንፈስ አምልኳዊ ታቦት። በመሸነፍ ውስጥ የማሸነፍ ሥነ  -ልቦናን በቅብ ለማስረገድ ከመጣር ይልቅ በመሸነፍ ውስጥ በነበሩ ግድፈቶች እና እርማቶች ላይ ማተኮር ያስፈልግ ነበር። 

አንድ ነገር ልበል ትንሳኤ ራዲዮን የቅንጅት መንፈስ ነን ለማለት የ አማራ ተጋድሎ ሲመጣ ብቅ አለ። ይህ መሆን በራሱ በወቅታዊ መንፈስ ውስጥ ራስን አለመሆን ነበር። በቀጣዩ ደግሞ ማን ያውቃል ሁለት ጣት ተመልሶ ይመጣ ይሆናል … ወቅት ለነሳህ ነገር ያሳጣህን ዕውነት ፈልጎ፤ ቆፍሮ ጥሮ ግሮ ማግኘት እና በአዲስ ሃሳብ አዲሱን መንፈስ ማስተናገድ የተገባ ነበር።

የግንቦት 7 አዲስ አባባን በሚመለከት ያለው አቋምን ስናዳምጥ ኖረናል። በብሄራዊ ሰንድቅዓላማ ይሁን፤ በልዑላዊነት፤ ኢትዮጵዊነት ማለት ከዬት በመለስ ስለመሆኑም እናውቃለን። የአማራ ታገድሎውንም በምን መልክ እንደተወራደደ አስተውለናል። ተወቃሽም ሆኖ ነበር። 

በሁሉም መስክ የሚሰጡ የትንሳኤነት ማብራሪያውንም መግለጫውንም በመደበኝ ተጥንቷል። ሁሉንም ዝበቱንም፤ ዝብጠቱንም፤ ቀጥ ያለውን መስምርም። በዚህ ውስጥ የሚታዬው  በአመዛኙ  ህዝብን ያለማወቅ ችግር ነው። አብሶ የብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ፍቅርን በሚመለከት፤ ኢትዮጵያዊነትን በሚመለከት ያው አማራም ኢትዮጵያዊ ነውና ለግንቦት 7 ሊሂቃን የሳጅን በረከት ስምዖን አማራነት መሸከም ያልቻለው አመክንዮ መሰል ፈተና እና ችግር ፊት ለፊቱ ይገጥመዋል ብዬ አስባለሁኝ። በልክህ የሆነ ነገር ነው ሳያሸልክ ራስን ማዝለቅ የሚችለው። ቅብ ከግድግዳ ቀለምነት ውጪ ምንም ነው።  

ምክንያቱም ዜጋ በሲሶ እና  በእርቦ ለሚሸነሸንበት ሚዲያ እና ንቅናቄ በፈለገው ዓይነት ቢወጣ ቢወረድ ዕውነቱን የሚያፍልቁ፤ ዕብለቱን የሚያበልዙ መረጃዎች ጊዜያቸውን እዬጠበቁ ብቅ ይላሉ። በመሆን ውስጥ ያለው ፈተና አገር ውስጥ ከገቡት ከዬትኛውም አገር ውስጥ ሆኖ እታገላለሁ ከሚለው የፖለቲካ ድርጅት በላይ ለግንቦት 7 ፈተና ነው።

የህዝቡ መንፈስ እና የግንቦት 7 መንፈስ ሃዲዱ የተቋረጠ ነው። በሚባለው ውስጥ እና በሚጠበቀው ውስጥ ቢኖር እንኮን አውራው ፓርቲ እሱ ነበር። የተሰገደለት የተደገደገለት። ነገር ግን በፈለገው ዓይነት የሙገሳ ቅንብር የጠቀለለውን ቢጠቀልል፤ ያስወገዘውን ቢያስወግዝ፤ የገፋውን ቢጋፋ፤ ያዘባረቀውን ቢያዘባርቅ ዕውነት ገሃዱን ማውጣቷ አይቀሬ ነው። 

ይልቅ ዕድሜ ለአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ እና ለቄሮ ተጋድሎ ቢባል ይሻላል። ከጉድ አውጥተዋል፤ አድነዋልም። ይህን ላደመጡ ሊሂቃንም ምስጋና ይገባቸዋል። … ምክንያቱም ከዚህ በላይ ትግሎ ቆይቶ ቢሆን ኖሮ የመጨረሻውን ጽዋ መጎንጨት አይቀሬ ነበር። መራራው ነገር ይህ ነበር። 

ወደፊትም እንደ ጋዜጠኛ በህሊና መኖር ነው የሚበጀው። ልክ እንደ ወሎው መከራን በመጋራት ቀዳሚ ሐዋርያ እንደ ተሆነው። እርግጥ ነው ከእውነት ጋር በተከተመ ቁጥር አጨብጫቢው፤ አጀቡ ላይኖር ይቻላል፤ በአላቆችም ተግሳጽም እንዲሁ ይገጥማል። ግን ለህሊና መኖር ይቻላል። 

አገር ባይመች ይለቀቃል፤ ጎረቤት ባይመች መለያዬት ይቸላል። ትዳር ባይመች ይፈታል። ሥራ ባይመች ይተዋል። ህሊና ባይመች ግን ከዬት ይደረሳል?

ጋዜጠኛ ከመሆን ፈተና መዳን የሚችለው በውነት ውስጥ ለመኖር ከተቆረጠ ብቻ ነው። ቀድሞ ነገር ጋዜጠኛ ዕውነት እንጂ ወረቀት አምላኪ ከሆነ ከሙያው ማዕቀፍ ወጥቷል የመክሊት ነፍሱም የ አደጋ ጥሪ አለበት። … ይህ ጹሁፍ መውጣት የነበረበት ይህን አቶ ኤርምያስ ለገሰ ሲጽፍ ነበር ...  

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ለከንቲባነት  ኢንጂነር ታከለ ኡማን ለማዘጋጃ ቤት ሓላፊነት (ኤርሚያስ ለገሰ)”

  • መውጫ።

መሆን ፈታና ላይ አስቀምጦ ይደውራል ዘንድሮን … ነገስ? በተለመደው ቁና ይሆን መስፈሪያው?

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ። 




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።