በባዕላት ከብር ለሚገባው ክብር መስጠት ዕንቋችን።

ማለፊያ!
„አድርገህልኛል እና ለዘላላም አመሰግንሃለሁ።“
መዝሙር ምዕራፍ ፶፩ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
12.09.2018
ከጭምረቷ ሲዊዘርላንድ።
በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን!


ኑሩልን!

  • ·       መነሻዬ።

„ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ በመሆን በአንድት የአዲስ አመት በዓል ሲያሳልፉ የሚያሳይ ልዩ የበዓል ዝግጅት“


ከእንግዲህ „ሁለቱ ሲኖዶስ“ የሚለው ቃል ራሱ መታረም ያለበት ይመስለኛል። በቅደስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብጽዑን አባቶች ባዕለ ቅዱስ ዮሖንስን ሲያከበሩ ሊባል ይገባል። ቀድሞውንም ዶግማው አንድ ነው የነበረው። 

ቅድስት ቤተክርስትያነችነን ጊዜ ፈተነ፤ ዲያቢሎስ ሲረታ ደግሞ አህቲ ቤቴክርስቲያን እንደ ተፈጥሯዋ ሆነች። የሆነ ሆኖ እጅግ የሚመስጥ የበዓል ጠረን በቅደስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብፁዕን መኖሪያ ቤትም መከወኑ ዘገባው ያመልከታል። ለእኔ በቅድስት ፓትርያርክያት ደረጃ እንዲህ ባህላዊ ትውፊት ሳይጓደልበት ሲከበር የመጀመሪያዬ ነው። እንዲህ ሲከበር አይቼ አላውቅም።

ቡናው እየተቆላ እንደ አባት አዳሩ መሰናዶው ተሟልቶ፤ ቤት ያፈራው እንደዛ ኑብኝ ኑብኝ አያለ፤ መዘምራን እዬወረቡ ቅኔው እዬተዘረፈ እፁብ ድንቅ ነው።
ይህ ትውፊታችን፤ ትሩፋታችን ያከበረ አያያዝ የዛሬ 10 ዓመት ብዬ ሳስብ ዘመኑም፤ ታሪክም፤ ትውፊትም፤ ትውልድም፤ አገርም የሚካስበት አዲስ ስዕል ዲዛይን ሸልሞኛል። በሌላ በኩል ድርጊቱ የአብይ ሌጋሲ ታሪክንም እዬጻፈልን ነው። ታሪኩ ደግሞ የ አላዛሯ ኢትዮጵያ አንጡራ ሃብቷም ነው። የነገ ደግሞ ትውፊቷ። ውርስ ቅብብል እንዲህ እያለ ከትወልድ ወደ ትውልድ ይሸጋገራል።  

ውስጣችን ያለው ፍላጎታችን እንዲህ በመሰለ ክብር - ግርማ ሞገስ ቀን ሲሰጠው ማዬት፤ ሲፈቀድለት እንዴት መንፈስን ያድሳል። ተስፋን ያፋፋል። ያው እኔ በተደጋጋሚ እንደምግለጸው የብጽዑ ወቅዱስ አባታችን የ4ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ የአቡን መርቀሪዮስ ቅድስና አንድ የድርስነ ሚስጢረ መድብል ይወጣዋል። 

ዛሬ ሊከሰቱ የማይችሉ ከቶውንም ልናያቸው ያልቻሉ ርቁቅ- ጥልቅ የተደሞ ሚስጢራት፤ በብዙ የተከደኑ መንፈሳዊ ታምራቶች፤ በውስጥ ሊሂቅነት አለ ብዬ አምናለሁኝ። በውነቱ ዕድሎኞችም ነን። እኛ ብቻ ሳንሆን የኢትዮጵያ መንግሥትም ሙሴው ጠ/ ሚ/ር አብይ አህመድም ጨምር። 

የብጹዑ አባታችን ገድላቸው ስላልተፃፈ እንጂ ዘመንን የሚያናግር ምስክር አለ በብጹዑነታቸው ነፍስ ውስጥ። ዝምታቸው አገር ነው። ዝምታቸው ታሪክ ነው። ዝምታቸው ተቋም ነው። ዝምታቸው ዓዋጅ ነው።፡በዝምታቻው ልክ እዮራዊ መክሊት አለ። ቀን - ጊዜ እና ወቅትን የሚታደግ ትሩፋትም ለምልሞ እና አስብሎ ግን ተመስጥሮ አለ።

ኑሩልን!
  • ·       ቅ።


በሌላ በኩል የአማራ ቴሌቪዥን ደግሞ በዋዜም በነፃነት ተጋድሎ ሰቁ በጀግናው ኮ/ደመቀ ዘውዴ ቤት ውስጥ ተገኝቷል። የትዳርም የትግል አጋሩ ወ/ሮ ዘውድነሽ ማለደም  የኢትዮጵያ ሴቶች አካል ናቸው እና ዛሬን ዕንባ ተግ ብሎ እንዲህ ፍክት ብለው ማዬት አስችሎኛል።

የነገ ተረኛዋም ማህደር ደመቀም እንዲሁም አብዛኛውን የአገር አሳር ተሸካሚዎች ሴቶች ናቸው እና እሷንም በማዬቴ ደስ ብሎኛል። እንደ ጎንደር ተውልጄ እንደማደጌ ነገ ደግሞ እኛ በለፍንበት መከራ ወይስ የተሻለ ተስፋ ይኖርሽ ይሆን በሚል ዕድምታ ነበር ታዳጊዋን የተመለከትኳት።

የአዲስ ዓመት የባዕል ዝግጅት በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መኖሪያ ቤት


ይህን መልካምነት በማድረጉ  የአማራ ክልላዊ መንግሥት እና ሚዲያውን የ የአማራ የብዙሃን ቴሌቪዥን ሙሉ ቲም ሹፌሩንም ጭምር እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁኝ።

አንድ ቁምነገር ግን አማራን በሚመለከት በማዕከላዊ መንግሥት ደረጃ እማያቸው ያልተመጣጠኑ አንዳንድ ጊዜም የተረሱ ተባደግ ነገሮች ነገን ስላማስቀጠል ያላቸው አቅም መሳሳት በእጅጉ ያሳስበኛል። 

እኔንም ከዚህ ይፈትነኛል። … ሁሉን ነገር ነው እኔ የምከታተለው … ምክንያቱም በዚህ ውስጥ የእኔ ነፍስም አለበት። የቤተሰቦቼ ሩህ፤ ሥነ - ልቦና አለ፤ የወንድሞቼ የእህቶቼም ቀጣይ ተስፋ አለ። ሁሉም መከራ ያለው በዚህ ማህበረሰብ ኑሮ ተስፋ ላይ ነውና።

የሆነ ሆኖ እንዲህ ክብር ለሚገባው ክብር ዕውቅና መሰጠት የተገባ ነው። ታሪክም እኮ ነው። ታሪኩን የሳተ ትውልድ ራሱን እዬፈረሰ በፈረሰ ሬሳ መንፈስ ነው ሙቶ የሚኖረው። ይህ ትውልድ በተገኘበት አጋጣሚ ሁሉ ታሪኩን ቅንጣትም ብትሆን ዘግቦ ዘክሮ መያዝ አለበት። ለራሱ ለአማራ ሚዲያ ነፃነትም ተጋድሎው በትረ ሙሴው ነው። ስለሆነም ታሪኩን አሳልፎ መስጠት አይኖርበትም። 

ራስንም ማከብር ብቻ ነው ራስንም የሚያስከብረው። ዛሬ ላለው ለውጥ ሞገዱ ያለው ከዚህ ጎጆ መንፈስ ውስጥ ነው። ለወደፊቱም በመንፈሳችን ተቋማዊ ሆነን በጠነከርነው ልክ ትውልዱን ከማናቸውንም ጥቃት ለመቃቋም እንችላልን። በተዘናጋናው ልክ ደግሞ መሸነፍን፤ መክሰምን፤ መጥፋንት እናወራርዳለን።

በራስ ውስጥ መኖር አለመፍቅድ ትርፉ ለዛሬ ሳይሆን ለነገ ለነገ ተወዲያ በሃሳብ ደረጃ ላልተጸነሱትም አሳሩ ተራፊ ነው … አንድ ማህበረሰብ ከፖለቲካው መድረክ በተገለለ ቁጥር ባለቤት የለሽ ነው የሚሆነው... እዳሪ የተጣለ የማያፈራ መሃን ትውልድ ... 

27 ዓመት የተኖረው በዚሕ መሰል መዘለለ፤ መሰረዝ ሆኖ አሁንም „እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው „ ዓይነት ዕውቅና የተነፈገው ሂደት እያስተዋልኩኝ ነው። ብቻ ዕዮባዊነትም መሰነቅ መርሄ ስለሆነ በተደሞ እከታተለዋለሁኝ። 

ኑሩልን!
  • ·       ላ።


በሌላ በኩል የቸርነት አንበል አቶ ዮሴፍ ገብሬ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ የማስተዋል አባትን የነፃነት ትግሉን ባላን አቶ አንዱአለም አራጌን ጎብኝቷል። በዚህም ያለው ድባብ መልካም ነው።

ከዛ ሁሉ መከራ እና ስቃይ በኋዋላ ከሁለት የአንበሳ ግልግል ልጆቹ ጋር ባዕሉን ለማክበር እድል ያገኘው አባ ማስተዋል አቶ አንዱአለም አራጌ ውስጡ ላይ የማዬው ነገር እራሴንም የፈተነኝ ቢሆንም ለእኔ ትልቁ ቁምነገር በህይወት መኖሩ ስለሆነ ልጆቹን በዓይኑ እያዬ መዋል ማደሩም የመልካምነት ዜና ነው ብዬ አስባለሁኝ። ተመስገንም ብያለሁኝ።

አብሶ ልጆች ከሚሰሙት የሚያዩት መልካም ነገር ያስተምራቸዋል እና የተጎዳው የህሊና ማህጸናቸውን የሚጠግን እርምጃ ነው ይህ ብልህ ወጣት አቶ ዮሴፍ ገብሬ የከወነው። ይህ ብልህ ወጣት ትውልዳዊ ድርሻውን ለመወጣት ትጋቱ አብነቱ አንቱ ነው። ለመልካምነት ጉልላትም ነው። ይባረከ!

የቸርነት አንበል አቶ ዮሴፍ ገብሬም ለዚህ መልካማዊ የዓውዳዓመት ጉብኝት ወጣቱን ፓለቲካኛ ቤቱ ድረስ ሄዶ „እንሏን አደረስህ“ ማለቱ፤ ዕውቅና እና ክብር ለመስጠት የሄደበት መንገዱ በውነቱ የዚህ ወጣት አስተዋይነት ያሳያል። የኢትዮጵያ መንግሥት ያስናቀ ድርጊቱ ነው። 

እንዲህ አስታዋሽ ላጡትም ጀግኖች እና የጅግኖች ቤተሰቦች አለንላችሁ ማለት ትርፉ እዮራዊ ነው። ምርቃቱም እንዲሁ። ከሁሉ ለልጆቹ ህሊና። ለልጆቹ ሥነ - ልቦና እና ለዛች መከረኛ እናትም። ልጇ ምን ያህል ፈተናን እንደተቀበለ ታውቃለች አይታለችም - እናት። ግን ለአንዱ ከልክ በላይ የተለጠጠ ለሌላው ደግሞ ባይታዋርነት ሲነግሥ ሐዘኑ ለእናት ጥልቅ ነው ያርመጠምጣል።
  • ·       ሁለት አስተዋይ ወጣቶች የታደሙበት ቃለ ምልልሱም ይኸውና።

„Jossy In Z House የአዲስ አመት ዘመድ ጥየቃ ከፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ቤት“


የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። ሥርዓቱን መታደም የህሊና ርካታ ይሰጣል። 

መልካሞችን ያብዛልን!

ማስተዋልን ያበራክትልን። አሜን! 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።