ከቶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ባለቤቷ ማን ነበር?
ከቶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ባለቤቷ ማን ነበር 27 ዓመት ሙሉ? „እግዚአብሄርም ቃየልን ወንድምህ አቤል ወዴት ነው አለው፤ ቃዬልም እኔ የወንድሜ የ አቤል ጠባቂ እኔ ነኝን አለ።“ መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ፳፰ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 13.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=crQyRhfQXY4 ሰሞኑን በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን በተመለከተ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ መግለጫ፣የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ · መቅደመ ብልሃት። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ዶር . አብይ አህመድን እንዴት ትተረጉሜያቸዋለሽ ብባል ብሄራዊ ቀናችን ናቸው ብዬ ነው። ኪንግ ማርቲን ሉተር አሜሪካን የማዳን የመሪነት ብቃታቸው ዛሬ ነው ይበልጥ የታዬ የተገለጠው - በወጉ። አሜሪካ ለራሷ ተርፋ የብዙዎች ተስፋ መሆን መቻሏ የትናንት የኪንግ ማርቲን ሉተር የተጋድሎ ውጤት ነው ። ተስፋ ባጣንበት፤ ጥልፍልፉ ችግራችን መፍትሄ አልቦሽ ሆኖ ከጭቃ ወደ ጭቃ በዙር አዳክሮ በደቆስን ሰዓት፤ ጨንቆን ጥግ አልቦሽ በሆንበት ወቅት ብቅ ያለ የመሪነት ልዩ ድንቅ ክህሎት ነው የ ዶር . አብይ አህመድ መንገድ ። እርግጥ ዛሬ ፍሬውን ልናይ አንችል ይሆናል፤ ብንከተለው ግን ብሄራዊ ቀን የሚያስወስን ቁም ነገር በዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ህሊና ውስጥ...