"ለእግዜር አይቀርበት ለሰው አይቀርበት ሰሌ ከሰራው ቤት እኛ ገባንበት"
„ለእግዜር አይቀርበት ለሰው አይቀርበት
ሰሌ ከሰራው
ቤት እኛ ገባንበት።“
„ከእኔ ጋር ማን ነበር?
ትንቢተ ኢሳያስ ፵፬ ቁጥር ፳፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ
13.11.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።
- · መነሻ ከኑሮ በዘዴ ዩቱብ።
Teddy Afro - ቴዲ አፍሮ ታሪካዊውን የኢትዮ-ኤርትራ የፍቅር ሩጫ ሲያስጀምር |
The First Ethio - Eritrea Great Run
ቴዲ አፍሮ ኢትዮ-ኤርትራ የፍቅር ሩጫን ላሸነፉ ሽልማታቸውን ሲሰጥ
- · እንዲህ እስቲ እንበልለት …
እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ቅኖቹ ደህና ናችሁ ወይ? አንድ ቀን ከአይቲ ጋር ሲለዩ ብዙ አዳዲስ ነገሮች
ይኖራሉ። ትናንት የጥሞና ቀኔ ነበር። የሃሳብ ቀኔ። ማሰብ ማሰብ ማሰብ እስከ ህልፈት ድረስ። ስለ ሃሳብ አንድ ጹሑፍ ጽፌ የሥነ
-ጹሑፍ ኮርስ ስጨርስ በምርቃታችን ዕለት እንዲቀርብ አልፎልኝ ግን ያን ቀን በጤና ጉደለት ምክንያት ሳይሳካ ቀረ። ሃሳብ የማይለቅ
የህይወት ጓደኛ። በእኔ ህይወትም የሃሳብ የተለዬ ቀን አለኝ። ሃሳብ ለማሰብ የምወሰንለት ዕለት ልብሴም ቤቴም የዓውደ ዓመት ያህል
ልዩ ክብር አለው።
ውዶቼ፤ እርእሱ የጎንደር ሰው የሚለው ነው። እንግዲህ ጣሊያን በሽንፈት በኢትዮጵውያን አርበኞች ሲሰናበት በጎንደር ከተማ ባደኩበት ጨዋ ሰፈር
ካሉ የጣውላ እና ጣሪያቸው የሸክላ ቤቶች ውስጥ አርበኛው ሲገባ ያለው ይመስለኛል። ወተባርኮም አደባባይ እዬሱስ አካባቢም
ያለ ይመስለኛል።
ግን ጨዋ ሰፈር ራሱ እግሩ ያው የጣሊያን የሠራው የኢትዮጵያ አርበኞች
የደም ዋጋ ነው።
ነገር እሲከ ነገር ያንሳውና ይፈቀድለት ለዛ የአርበኞች ተጋድሎ ውለታ ተብሎ የተሰራ የመብራት ጄኔሬተር
ወተባርኮ ላይ ነበር። አይዋ ወያኔ አገር እዬመራ አጋፎ አልጠቅም ብሎት ነቅሎ ወስዶ ትግራይ ላይ የተከለው። አሁን አሁን
ስሰማ ወሎም ጅማም ተመሳሳዩ
እንደ ተፈጸመ አድምጫለሁኝ / አንብቤያለሁም። ለነገሩ አፈር የሚጭን እንኳንስ የሃይል ማመንጫ፤ ለነገሩ ብረት ነገር የደም ሥሩ ነፍሱ
እንደ ነበር ነው … አይታፈርፍም ሌብነትም እንደ ጀግንነት ተቆጥሮ ሰማዕትነት ያሰጣል በእነሱ መንደር? ህም።
ወደ ቀደመው ምልሰት ስናደርግ ሰንበት ላይ የኢትዮ ኤርትራ የፍቅር ሩጫ በኢትዮ አፍሪካ ዋና ከተማ አዲስ አባባ ላይ
ነበር። ሩጫውን ያስጀመረው ለአሸናፊዎቹ ሽልማቱን የሰጠው ደግሞ የቅኔው ዕንቡጥ ገጣሚ እና አርቲስት ቴወድሮስ ካሳሁን ነው። ለዚህ
ነው የጎንደርን ይትባሃል ከች አድርጌ እጬጌ ያደረኩት። „ለእግዜር አይቀርበት“ በምልሰት ተውፊትም ስለሆነ ያነሳሁት።
ያ ክፉ ዘመን አልፎ እንሆ መንፈሱ ግዞት የተፈረደበት መከረኛ የቅኔው ዕንቡጥ ጠሐዮዋ ቦግ ብላለት
በክብር የልቡን ጽላት ኢትዮጵያዊነትን አሸንፎ
አዬ።
በዛ እንደ ትርፍ ዜጋ በሚታይበት፤ ሥራዎቹ ሁሉ በሚከለከልበት አደባባይ ላይ መሪ ተዋናይ ሆኖ
የፍቅርን ህይወቶች በአህትዮሽ መንፈስ እንሆ መራ። ራዕዩን አዬ። ትንቢቱንም ተመለከተ። ኢትዮጵያዊነትም አሸነፈ። ተመስገን።
የሚገርመው የኤርትራው ፕሬዚዳንት እና የሱማሌው ፕሬዚዳንት በወል ለፍቅር ሊተጉ አማራ ክልል
በቆዩበት ማግሥት ነው የሆነው። ፍቅር ሩጫውን አዘጋጆቹ የመንግሥት እቅድ አያውቁም ነበር። ነገር ግን የእነሱ መሰናዶ እና የመንግሥት
የአፍሪካ ቀንድ የፍቅር ጉዞ በእዮራዊ ታምር
ሰመረ። ዋዜማ እና ትንሳኤ ግጥምጥም።
ቅንነት ከኖረ፤ የህሊና ድንግልና ከኖረ፤ እንዲህ ነው በመንፈስ የበጉነት ማሳ የቅኖች ጋለሪ
በራሱ ጊዜ የሚሠራው። አሁን አምና ይህ ቀን ይመጣል ብሎ ማን አስበ? ማንስ ያልም ነበር? ለዚህ ነው አስቀድሜ የዛሬ ዓመት „መባቻ“
የሚል ጹሑፍ የጻፍኩት። ቀደም ብሎም መቋሚያንም ጽፌ ነበር።
ለዚህም ነበር ያን ንጹህ አዬር በሴራ የሽታ ሽቶሽ እንደ ተለመደው አከርካሪው ተሰብሮ ተልፈስፍሶ
ሊቀር በግራ በቀኝ ሲፈታተኑት፤ እኔ እህታችሁ ደግሞ መዥለጥ አድርጌ የብዕር ሰይፌን ስነሳ ይባረክ እንጂ ሳተናው ፈቅዶ ስሞግት
የባጀሁት። አዲስ ቡቃያን በመንቀል የሚታወቀው የግራው የሴራ፤ የኢጎ፤ የምቀኝነት ፖለቲካ ያን ያህል ዙሪያ ገባውን በአሉታ ተደራጅቶ
ድንግሉን መንፈስ ሲያዋክብ ተሳክቶለት ቢሆን ኖሮ ዛሬን አናገኘውም ነበር።
ዛሬ የተገኘው በትናንት የታጋሽነት፤ የአዬባዊነት እና ከብረት ቁርጥራጭ በተሰራ ድንቅ የጽናት ጥንካሬ
ነው። ይኸው አሁን ሁሉም ተነፈሰ፤ ሁሉም ተጠቃሚ ሆነ። ሁሉም ጀግና ተባለ፤ ሁሉም ጉሮ ወሸባዬ ተባለለት። እዮባዊነት ያንሰናል
ብዬ የጻፍኩትም ለዚህ ነበር። እጬጌው ሂደትም እንዲሁ።
የሆነ ሆኖ ያ ጥቁር ዘመን አልፎ እንሆ ህዳርም አልፎለት ጸሐይ ወጣለት። ህዳር ከእኔ ቤት ጠሐይ የወጣላት አምና ነበር። ለሌላው ደግሞ
መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም።
ነፃ የወጡት መከረኞቹ የኢትዮጵያ ቀናቶች፤ ወራት፤ ዓመታት፤ ዘመኑ ጭምር። ነፃ የወጡት የኢትዮጵያ
ጋራ ሸንተረሮችም ጭምር ነው። ነፃ የወጡት እንሰሳትም ናቸው። ነፃ የወጣው እራሱ ፍቅርና ተስፋም ናቸው። አዬሩ እራሱ እስረኛ ነበር።
አሁን ተመስገን ነው። እንኳን ደስ አለሽ አላዛሯ ኢትዮጵያ።
መባቻን የጻፍኩት የዛሬ ዓመት ህዳር 9 ቀን 2017 እ.አ.አ ነበር። ያ መባቻ መሰንበቻ ስለመሆኑ ብዙ
ተግችበታለሁም። ቀንበጥን ብሎግንም አስወስኖ ግንቦት ላይ ያሰጀመረኝ ይኸው ጉዳይ ነው። ቀንበጥ ብሎግ የዛሬ ሁለት ዓመት ጀመሬው ግን በድንግልና ብዕሬን ሲጠበቅ ለ እሱም ቀን ወጣለት።
መባቻ ጹሑፌን 150 ሰው ነበር ሸር ያደረገው።
ምክንያቱም ያ ጹሑፍ በዛን ጊዜ ወቅቱን ያልጠበቀ
ስለነበር። ሌላው አዬር ላይ በሠረገላ በቦሌ ብቅ የሚል ትንሳኤና ህይወት መሪ ይጠብቅ ስለነበር።
የሆነ ሆኖ ጊዜ መልካሙ እንዲህ አሳዬን ቀናቶችን በተደሞ እንቃኝ ዘንድ ደግሞ ልዑሉ ፈቀደልን
እናም ያልነው አለን፤ ያልነውም ሆነ። ተመስገን! ይኸው ዛሬ የቅኔው ዕንቡጥ በአገሩ መሬት በግዞት በቁም እስር እንዲሆን የተደረገበት ድቅድቅ ጨለማ አልፎ እንዲያውም የክብር እንግዳ ሆኖ ተገኜ።
ተመስገን።
- · ጥቂት ምርኩዞች።
https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/archives/40997
መባቻ – ሥርጉተ – ሥላሴ
November 9, 2017
አብይ ጥሪው ከዕንባ ነው፤
መልካም ዕድል ለኦህዴድ፤
አብይ የመልካምነት ባለቅኔ ነው፤
የበረከት ሸር ግብዕቱ አይቀሬ ነው፤
https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_38.html
ኢትዮጵያዊነትን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ፤
ዶር አብይ አህመድ ዛሬ የበቀሉ አይደሉም። Fact፤
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ
ሚስጢር።
የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
እናንተን አያሳጣኝ አምላኬ።
ካለ
እናንተ እኔ ትቢያ ነኝ እና።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ