ልጥፎች

ከኦገስት 19, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ሰዋዊነትን ፖለቲካ ሳይሆን ሰዋዊነት #ተፈጥሯችን ይመራው ዘንድ እንፍቀድለት።

ምስል
  #ሰዋዊነትን ፖለቲካ ሳይሆን ሰዋዊነት #ተፈጥሯችን ይመራው ዘንድ እንፍቀድለት።   "የሰው ልብ መንቸድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)   #ምዕራፍ ፲፮።      የእኔ ክብሮች ቤተ - ሥርጉትሻ ታዳሜወቼ፤ በአያሌው እንዴት ሰነበታችሁልኝ። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ከእናንተ ከውዶቼ፤ ከክብሮቼ ከማህበረ ቅንነት ናፍቆት በስተቀር እጅግ ደህና ነኝ። ትናንት ምዕራፍ ፲፮ ለመጀመር ሃሳብ ኑሮኝ አልነበረም የገባሁት። የጥበብ አውራ፤ #የተሰጠው ፤ #የተቀባው ጋሼ ደቤን ዘላለማዊ እረፍት በድንገት ስሰማ ነበር ደንግጬ የገባሁት። ማአዚም ታሠረች ሲባል ጥሞና ላይ ነበርኩኝ አቋርጬ ገብቼ ነበር። እማልታገሳቸው ድንገቴወች ይገጥማሉ።    ለነገሩ የተከበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳት ዶናል ትራንፕ፤ የመላ ዓለም ሰላም ናፋቂ ቤተኞችን የውስጥ ስጋታችን ሙሉ ጤና ለማጎናጸፍ እየሄዱበት ያለው #ዊዝደማዊ ጉዞ ከድንቅ በላይ ስለሆነ እሱም ወደ ቤቴ ይመልሰኝ ነበር። በስክነት ልየው ብየ እራሴን ገትቼ እንጂ። ዊዝደም በሚል እርዕሰ ጉዳይ ስለፕሬዚዳንት ትራንፕ ጽፌ እንደ ነበር ታስታውሳላችሁ። ይህ የትውልድ ዘመን መለያየትን ሳይሆን መገናኜትን ድልድይ የመስራት ግዴታ እንዳለበት በጽኑ አምናለሁኝ። እምነቴን፤ ፍላጎቴን ስጽፍ ኑሬያለሁኝ። #ጥላቻን #ጥላቻ አያክመውም። ቋሚ ሎጎየ ነው።   ጋሼ ደበበ ለእኔ እንደ ጋሼ ወጋየሁኝ፤ ዘመኔን ሁሉ ለለገሱኩለት እንደ ጋሼ ጸጋየ ገ/ መድህን፤ እንደ ጋሼ አቤ፤ እንደ እቴጌ አለምዬ፤ እንደ ጋሼ ኪሮስ፤ እንደ ጋሼ ኩራ ነፍሱን ይማርልን ወዘተ የማየው ከውስጤ የማከብረው የጥበብ ዓውደ ምህረት አውራየ ነው። ጋሽ ደቤ ይሁን ሌሎች የጥበብ ሊ...

ፈላስፊት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር ያጽናሽ። አሜን። መራራ ስንብት።

ምስል
  ፈላስፊት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር ያጽናሽ። አሜን። መራራ ስንብት።   • የጥበብ ዓውደ ምህረት። • የጥበብ አብርሃም። • የጥበብ ምስባክ። የጥበብ አንከር። • ዋ! ጋሼ ደቤ መድረክን ለማን አደራ ሰጠኽ ይሆን። „መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ“   መራራ ስንብት። አንተ ባለ ልዩ ቅብአ የተሰጠህ፤ ደህና ሁን። እግዚአብሄር አምላክ ነፍስህን በአጸደ ገነት ያኑርልኝ። አሜን። ለክብርት አብነቷ የትዳር አጋርህ፣ ለተወዳጅ የአብራክህ እና የሙያ ልጆችህ፤ በዝምታ ውስጥ ሆነው በክብርህ ልክ ላከበሩህ ወዳጆችህ፣ አድናቂወችህም እኔን ጨምሮ መጽናናትን እመኛለሁኝ። ዘመን ቢዘረዘር አንተን የሚመስል ለማግኜት ሩቅ በጣም ሩቅ ነው ተስፋው። በሰላም እረፍልን። ለመሰጠርካት ክብርት እናትህ ኢትዮጵያም መጽናናትን እመኛለሁኝ። ዋርካዋን አጣች እምየ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 18.08.2025