#ሰዋዊነትን ፖለቲካ ሳይሆን ሰዋዊነት #ተፈጥሯችን ይመራው ዘንድ እንፍቀድለት።

 

#ሰዋዊነትን ፖለቲካ ሳይሆን ሰዋዊነት #ተፈጥሯችን ይመራው ዘንድ እንፍቀድለት።
 
"የሰው ልብ መንቸድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
 
#ምዕራፍ ፲፮። 
 May be an image of 1 person, smiling and jewelry
 
የእኔ ክብሮች ቤተ - ሥርጉትሻ ታዳሜወቼ፤ በአያሌው እንዴት ሰነበታችሁልኝ። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ከእናንተ ከውዶቼ፤ ከክብሮቼ ከማህበረ ቅንነት ናፍቆት በስተቀር እጅግ ደህና ነኝ። ትናንት ምዕራፍ ፲፮ ለመጀመር ሃሳብ ኑሮኝ አልነበረም የገባሁት። የጥበብ አውራ፤ #የተሰጠው#የተቀባው ጋሼ ደቤን ዘላለማዊ እረፍት በድንገት ስሰማ ነበር ደንግጬ የገባሁት። ማአዚም ታሠረች ሲባል ጥሞና ላይ ነበርኩኝ አቋርጬ ገብቼ ነበር። እማልታገሳቸው ድንገቴወች ይገጥማሉ። 
 
ለነገሩ የተከበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳት ዶናል ትራንፕ፤ የመላ ዓለም ሰላም ናፋቂ ቤተኞችን የውስጥ ስጋታችን ሙሉ ጤና ለማጎናጸፍ እየሄዱበት ያለው #ዊዝደማዊ ጉዞ ከድንቅ በላይ ስለሆነ እሱም ወደ ቤቴ ይመልሰኝ ነበር። በስክነት ልየው ብየ እራሴን ገትቼ እንጂ። ዊዝደም በሚል እርዕሰ ጉዳይ ስለፕሬዚዳንት ትራንፕ ጽፌ እንደ ነበር ታስታውሳላችሁ። ይህ የትውልድ ዘመን መለያየትን ሳይሆን መገናኜትን ድልድይ የመስራት ግዴታ እንዳለበት በጽኑ አምናለሁኝ። እምነቴን፤ ፍላጎቴን ስጽፍ ኑሬያለሁኝ። #ጥላቻን #ጥላቻ አያክመውም። ቋሚ ሎጎየ ነው።
 
ጋሼ ደበበ ለእኔ እንደ ጋሼ ወጋየሁኝ፤ ዘመኔን ሁሉ ለለገሱኩለት እንደ ጋሼ ጸጋየ ገ/ መድህን፤ እንደ ጋሼ አቤ፤ እንደ እቴጌ አለምዬ፤ እንደ ጋሼ ኪሮስ፤ እንደ ጋሼ ኩራ ነፍሱን ይማርልን ወዘተ የማየው ከውስጤ የማከብረው የጥበብ ዓውደ ምህረት አውራየ ነው። ጋሽ ደቤ ይሁን ሌሎች የጥበብ ሊቃውንት የፈለጉትን የፖለቲካ አቋም የማራመድ ሙሉ #መብት አላቸው። የሚዲያ ሆነ የፖለቲካ ፋንክሽነር ተመክሮየ ይህን ያጸደቀ ነው። ቀደምት አቨው እና እመው በላቀ ልቅና #ነፃነታችን ያስከበሩልን ለሲሶ ወይንም ለእሮቦ ነፃነት አልነበረም። ለሙሉ ነፃነት ነው። እያንዳንዱ የሰው ልጅ በእግዚአብሄር ፈቃድ ሲፈጠርም በሙሉ ነፃነት ነው። በማተር የሚያምኑትም ይህን የሚቀበሉት ይመስለኛል።
 
ጋሼ ደቤ ይሁን ጋሼ ጸጋዬ፤ ጋሼ ጸጋየ ይሁን ጋሼ ወጋየሁ፤ ጋሼ ወጋየሁ ይሁን እቴጌ #አለምየ የኖሩት ለመሰጠሯት ልዕልት፤ ፈላስፊት፤ ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ ብቻ ነው። ለቀደሙቱ ድንቅ ከያንያን አጀንዳቸው የሚስጢር ጓዳቸው ይሁን ዓውደ ምህረታቸው #ኢትዮጵያ እና #ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።
 
የኪነ- ጥበብ ሰው ከአገሩ ከወጣ የባህር ዳር አሳ ይሆናል። አሳ ከባህሩ ከወጣ አሳዊ ተፈጥሮ #ቀጥ ይላል። ትርታው ይቆማል። ኪነጥበብ ማዕረጉም ሆነ ሞገሱ #አገር ብቻ እና ብቻ ነው። አድናቂውም አክባሪውም የዛች ተናፋቂ አገር ሰው ብቻ ሳይሆን አየሩ፤ ጋራ ሸንተረሩም ጭምር ነው። ስደት ለጥበብ ሰው መኖሩ ሳይሆን #እየሞተ #ማዝገሙ ነው። አገሬ እኖራለሁ ሲል አንድ የጥበብ ሰው ደግሞ ካለው ሥርዓት ጋር በጥንቃቄ መኖርን ሊጠበብት ይገባል። 
 
ብላቴ ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን ያሳጣን ስደት ነው ብየ ነው እማስበው። ያ ዝልቅ እና ፍልቅ ነብይነት ማሳውን ስለአጣ በውስጡ ተሰቃይኖ ለዘላለም አጣነው። በድንገት አንድ የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሆነ የአማርኛ ቋንቋ ተናገሪ የጋሼ ጸጋየን አንድ ግጥም አንብብ ቢባል ተረር አድርጎ ማንበብ ፈጽሞ አይችልም። ይህን እመገልጽላችሁ አማርኛ ቋንቋ ለእኔ የሚከብድ አልነበረም። በብላቴው ቅኔ ግን ተፈትኛለው። #የአብየ ለማን የግጥም ሥርዓት ልከተል ቢል አንድ የኢትዮጵያ ገጣሚ አንድ ስንዝር አይራመድም። የቀደሜቶች ልቅናቸው #እዮራዊ ነው። እነሱን ስናጣ የኢትዮጵያ የሚስጢር ክህሎት #ሽርፍ እንደሚል በልቦናችን ልናስበው ይገባል። አዛውንት ሊቃናት መለየታቸው ሳይሆን መኖራቸው ምርቃት ነው። 
 
የአንድ አገር የጥበብ እና የጥበበኞች ጉዞ በዛ አገር ህገ - መንግሥት ስር መሆኑን ማመን፤ መቀበል ግድ ይላል። እኔ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ነኝ። በሲዊዘርላንድ ህገ መንግሥት ሥር ነኝ። ህጉን አክብሬ እኖራለሁኝ። የአገሬን ህገ - መንግሥት ድንጋጌወችንም ተሰደድኩ ብየ አንዲት ቅንጣት ለመጣስ ሃሳቡም ፍላጎቱም የለኝም። የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት መንፈሱ ሸንሻኝ ስለሆነ በሥር ነቀል እንዲቀየር የምመኝ፤ ለዛም የታገልኩ ሴት ነኝ። ግን ሥራ ላይ ያለን ህገ መንግሥት ጥሼ፤ ሌላ መመኜት የህሊናየ ሚዛን አይፈቅደውም። የእያንዳንዱ ሰው ችሎት ህሊናው ነው ብየም አምናለሁኝ። ህግ የተሠራው መኖራችን #አናሪኪ የጥማታችን ማርኪያ እንዳይሆን ነው።
 
ስለሆነም እኔ ተሰድጄ የአገሬን ህገ - መንግስት ድንጋጌወችን እንዳልጥስ እየተጠነቀቅኩኝ አገር ያሉትማ ምንኛ ሊጠነቀቁለት ይገባል ብሎ መመዘን ህሊናን ይጠይቃል። አንጎልማ #ድንቢጥም አላት እና። ከድንቢጥ እለያለሁ ስል ከድንቢጧ የተሻለ ማሰቤን እራሴን መፈተሽ ይገባኛል። ፈተናውንም ማለፍ ይኖርብኛል።
 
ትግል፤ ልፋት፤ ድካም ማዕከሉ #ሰው ሊሆን ይገባል። በሰው ህይወት ደግሞ ሳቅም - እንባም፤ ፍስሃም - ሃዘንም፤ ባለ ተስፋም - ተስፋ ማጣትም፤ ስኬትም - ኪሳራም ሁሉም ይኖራል። የሰው ልጅ መራራ ስንብቱ ከሥጋ ሲለይ ነው። ማንም ይሁን ማን የአንድ የሰው ልጅ ስንብት #አያስቅም። ወይንም #ፌስታ አይሆንም። ከአረማዊነት የምለይበት እኔ ሥርጉተ ሥላሴ እራሴን ፈትኜ በትክክል እራሴን ሳልሸነግል ሰው ሆኜ መገኜቴን ሳረጋግጥ ብቻ ይሆናል። ሰውነት ደግሞ #ሚዛናዊነት ነው።
 
ህጉ - ጨቁኖኛል፤ ህጉ - አሳዶኛል፤ ህጉ መኖሬን ነጥቆኛል የምለው ጫካም፤ እስርም ያየሁኝ፤ የተሰደድኩትም እኔ ሆንኩ ሌሎች ወገኖቼ ዱርቤቴ ያሉት ወይንም ለካቴና መኖራቸውን የሰጡ ሁሉ ህግ ማክበር ስላቃታቸው ነው ብየ አላምንም። ዘመን እና ጊዜ የሚፈጥሯቸው ረቂቅ፤ ከቁጥጥር ውጭ የሚያወጡ የማይነበቡ ወይንም የማይተረጎሙ ገጠመኞች ይኖራሉ።
 
ለዚህም ነው ግራ ቀኙን #ማዕከላዊ ሁኜ በማስተዋል እምከታተለው። በአባይ ግድብ ጉዳይ፤ በአየር መንገድ ጉዳይ ለዘመናት የዘለቀ ዝምታየም ለዚህ ነው። ወደፊትም ይኽው ይቀጥላል። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ከተሰደድኩባት ቀን አንድ ጀምሮ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ሙሉ አባል፤ ሙሉ አካል፤ የክፍለ አገራት ማህበርም የጎንደር ይሁን የዋክሽሞች የወሎ ማህበርተኛ አባልም ደጋፊ ሆኜም አላውቅም። የሰበካ ጉባኤም እንዲሁ ሆኜ አላውቅም። የእመቤቴ ትጉህ ገረድ ግን ነበርኩኝ። ግን በዕውቅና ባለው አካል ሊስት ሥሜ ግን ------ #እእ። በብልህነት ነው እምጓዘው። 
 
የሆነ ሆኖ በፖለቲካ ህይወታችን ብዙ ግድፈቶችን ፈጽመናል። !#እሰይ! እንኳንም ፈጸምን። እኛ ሰው እንጂ #ማሽን ስላልሆን። ግን ግድፈትን መደጋገም አይገባም። ተመሳሳይ ግድፈትን ገምግሞ ማረም ይገባል። ከአዳዲስ ግድፈት ግን ነፃ መሆን አይቻልም። ያም እንዲያስተምረን መፍቀድ መዳፋችን ላይ ቁምነገር ነው። #ወጣትነት ይህን ላይፈቅድ ይችላል። ወጣት ሆኜ ባላውቅም (በለጋ ዕድሜየ ከፍ ያለ ፖለቲካዊ ኃላፊነቴ ስለተሰጠኜ) የወጣቶች የህዝባዊ ድርጅቶች እና የሙያ ማህበራት #አደራጅ ስለነበርኩኝ በጥናት ቀመር አሰርቼ የደረስኩበት የወጣትነት ዕድሜ ጫናውን ይረዳኛል። ስለሆነም የወጣቶችን እርምጃ በተረጋጋ መንፈስ ነው እማስተናግደው። 
 
በሙሉ ዕድሜ፤ ከዛም ባለፈ በአዛውንትነት ደረጃ ያለ ኢትዮጵያዊ ወገን ግን ዕድሜው እራሱ የሚፈቅደው እና የማይፈቅደው ጉዳይ ስላለ በማስተዋል መራመዱ የሚበጅ ይመስለኛል። ይህ ማስተዋል በፖለቲካ ምክንያት በየዘመኑ የሚታጨደውን ስንት ሳይንቲስት፤ ስንት ፈላስፋ፤ ስንት ሊቅ፤ ስንት ዓራት ዓይናማ ገበሬ እንዳሳጣን ከውስጣችን እንሰበው። መዳን - በስክነት፤ መዳን - በእርጋታ፤ መዳን - - እራስን በመግራት እና በመገሰጽ ነው። ረጅም የጥሞና ጊዜ እምወስድም ጹሁፎቼ፤ ሚዲያወቼ ላይ የሠራቿቸውን ለመገምገም ነው። እንደገናም ቁጭ ብየ ለማድመጥ። ሁሉንም አደምጣለሁኝ። ሳደምጥ እኔ ብሆን እያልኩኝም ነው።
 
ክብሮቼ፤ ክብረቶቼ ኢትዮጵያን ታዋቂ፤ ተደናቂ፤ ተመስጋኝ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ፤ ተደማጭ አልባ በማድረግ ዘመኗ ሁሉ ምድረ በዳ ልሙጥ ነው ወደሚል ዝንባሌ መንፈሳችን እግሩን እንዳይተክል እንጠንቀቅ። ጋሼ ደቤ ተነግሮ፤ ተዘርዝሮ፤ ተብራርቶ የማያልቅ የጥበብ ምርቶችን ለእናት አገሩ ያበረከተ አውራ፤ ቀንዲል እና ቀንድ፤ የተሰጠው እና የተቀባ በጥሪው ልክ የኖረ የኪነ ጥበብ አንከር ነው። ስንብቱ ባያሳዝን እንኳን መሳለቅ በትውልዱ ላይ እኛ ምንም እንዳልሰራን የሚያመለክት ሃቅ ነው። አሁን ያለው የትግል መስመር የሚቀይር ሌላ ሥያሜ አጤ ሂደት ነገ ደግሞ ይዞ ይቀርባል። አፍንጫህን ላስ አቶ ሄደት ብየ የፃፍኩትን፤ አጤ ሂደት ብየ የፃፍኩትን ካገኛችሁት ብታነቡት ይጠቅማል። ነገ ደግሞ በማን በየትኛው አዲስ ሥያሜ? የትውልድ የሆና አንጃ ሳይፈጠርበት የዘለቀ ምን አለን? እንደ ኦፌኮ መሃን አለን ካላላችሁኝ በስተቀር።
 
እኛም ከዘመን ሰጡ ሥያሜ ጎን ተሰልፈን እናታችን መንፈስ ጋር ወይ ተቀራርበን፤ ወይ ተራርቅን ፍልሚያችን እስከ መቼ ይቀጥላ? ግን እስከመቼ? በወጣትነት፤ በጉልምስና? በስተእርጅናም በዛው በወደቅንበን፤ ባላተረፍንበት ሞናትነስ ጎዳና? ህዝባችንማ ያው ድሮም በሞፈር እና ቀንበር ዛሬም በሰው ትክሻ ሞፈር ተጎቶ፤ ድሮም በባዶ እግር ዛሬም፤ ድሮም በኩራዝ ወይ በወይራ፤ በአባሎ እንጨት ብርሃን ዛሬም። ምን አተረፍን??? ምን አሳካን? ከህሊናችን ጋር እንመክር ዘንድ ዝቅ ብየ እኔ አገልጋያችሁ እለምናችኋለሀኝ። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19/08 2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?