የፕሮፌስር መራራ መራር ማንፌስቶ።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „እንሆም ሁሉም እሾኽ ሞልቶበታል። ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፤ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“ (መጽሐፈ ምሳሌ (ተግሳጽ) ምዕራፍ 24 ቁጥር 31) የፕሮፌስር መራራ መ ራ ር ማንፌስቶ። ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 27.12.2019 · እፍታ። እንዴት ናችሁ የእኔ ቅኖች የኢትዮጵያ ቅኖችም ዛሬ የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ ላይ እና ተያያዥ ጉዳያዎችን እንደ አንድ የአገር መሪ ያላቸውን ሰብዕና አክሎ እምለው ይኖረኛል። ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል እና። በቅድሚያ ግን የእኔ ውዶች ይህን ፎቶ ልጋብዛችሁ። ትኩር ብላችሁ በማስተዋል በፈርጅ በፈርጁ ታስተውሉት ዘንድ በትሁት አክብሮት እለምናችሁ አለሁኝ። እዩት እስቲ። ፈትሹት እስቲ። የአንድ የአገር መሪ ቢሮ ነው። በመንፈሳችን መሪ ቢሆኑልን ብለን ስናስባቸው ስንናፍቃቸው፤ ስንመኝም ኑረናል። የሰው ልጅ እራሱን የሚያደራጀው በራሱ ልክ ነው። እራሱን የሚመራውም በራሱ አቅም ልክ ነው። ከቶ ኢትዮጵያዊ መሪነት እና የዚህ ቢሮ አደረጃጀት እና አያያዝ ተመጣጠኑ ይሆን። የፈረደባት ኢትዮጵያ ስንቱን ገመና ተሸከሚ ብለን አሳሯን እንዳበላናት ዛሬ ላይ ሳስበው ይሰቀጥጠኛል። በዚህ ዘመን ያላዬነው መከራ፤ ያልሰማነው መስቃ የለምና። ደበደቡን። ሰለቁን። ሾከሾኩን እግዚአብሄር ይይላቸው። የምንፅናናበት የፖለቲካ ሊሂቅ የለንም። ተስፋ የምናደርግበት የፖለቲካ መሪም የለንም። · ዝርክርክነት ለአገር መሪነት ያበቃ ይሆን? ...