ልጥፎች

መንትዮሾቹ ከቁልቋል አጫዋችነት ወደ ኦዳ አራጋቢነት የተገለበጡት ልብጣዊ ነፍሶች።

ምስል
እ ንኳን ወደ ቀ ንበጥ ብ ሎግ በ ሰላም መ ጡልኝ። „ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን   ሰጡኝ፣ በመከራቸው ጊዜ ግን ተነስተህ አድነን ይላሉ።“   ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፳፯ መ ንትዮሾቹ ከቁልቋል አ ጫዋችነት ወደ ኦዳ አራጋቢነት የተገለበጡት ልብጣዊ ነ ፍሶች። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·     እ ፍታ የሰማዩ አሻቦ ሲጠበቅ ትውር ሳይል በደመና ተደሞ የዓውደ ዓመቱ ሥርዓቱ እዬተፈጠመ ነው። ነፍስ ተ - እንቅስቃሴ የተገደበ ይመስላል። ጸጥ - ረጭታ እንደ ቤተ መቃብር ሆኗል። የቤቴ እርግቦች እራሱ እሱ አፋቸውን   የተባሉ ይመስል ኮሽታ የላቸውም። ድምጥም የለም። ብቻ እርጋታ በ - ጫታ ሰፍኗል- ዕለቱ። ግርማ ሞገሱ ግን ያስፈራል። ጭሯቸው ብቻ የተንጫረረው ግንዶኢን ባልስ ዳንስ ላይ ይገኛሉ፤ እቴጌዋ ከመንበሯ ብቅ ብላ አፈር እንደ ማለት አሰኝቷት ከንፈሯን ነፋ አድርጋ ሽው ትላለች። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ቅኔዎቹ የአገሬ ውዶች? ዕለቱን ባዕላችን ብላችሁ ለምታከብሩት ሁሉ መልካም የስኬት ዓውድ ዓመት አንዲሆንላችሁ እመኛለሁኝ። ትህትና ይታከልበታል። የ ወግ ገበታ። ዛሬ ስለ ግልብጥ ሲብሊንገኖችን ትንሽ ነገር መቋጠር ፈለግሁኝ። ለነገሩ እኛንም ገልብጠው ጋልበውናል - የዛሬን አያድርገው እና። ሁለቱም ሥም የለሾች ናቸው - ተዛሬ ላይ። ሥም የለሽነታቸው የሚያውቀው የቁልቋል አምላክ እና የኦዳ አምላክ ብቻ ናቸው። ግን ልበ - ጥፉን በሥም ይደግፉ እንዲሉ እነዛ ቅን፣ ደግ እና ቸር ወላጆች ምን የመሰለ ድንቅ ሥም አውጥተውላቸው ነበር። ልጅ ደመቀ መኮነን እና ልጅ ገዱ አንድርጋቸው ብለው። ነገር ግን ነፍስ አውቀው ፖለቲከኛ ከሆኑ ጀምረው የወላጆቻቸውን ሥጦታ

ከኦሮሙማ ፖለቲካ ስንተኛውን ሰንጋ እንጠብቅ

ምስል

ከኦሮሙማ ፖለቲካ ስንተኛውን ሰንጋ እንጠብቅ

ምስል

Ethiopian- አስደንጋጭ መረጃ ጃዋር በ75 ሚሊዮን ፕ/ር መራራን በከላቸው ? መረጃው ከኦዲፒ መንደር እነሆ

ምስል

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

ምስል
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“  (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·          እፍታ። ጤናይስጥልኝ የአገሬ ቅኖች እና ቅኔዎች። እንደምን አላችሁ? ለረጅም ጊዜ ጠፋሁኝ - በምክንያት። እርግጥ ነው እሰከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ በቀንበጥ ብሎጌ እጽፍ ነበር። ከዛ ደግሞ ቀንበጥ ብሎጌ ለተወሰነ ጊዜ መሰተጓጎል ቢገጥመውም ፌስ ቡክ ላይ ብዙ አድካሚ ያልሆኑ ግን በውስጤ እማምንበት አጫጭር ጹሁፎችን ስጽፍ ቆይቻለሁኝ። ዕይታዬ ያመለጣችሁ ይኽውና ሊንኩ። https://www.facebook.com/pages/category/Personal-Website/Httpfbmecg-1591546727802213/ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ግን የድምጽ አልባዎችን የኢትዮጵያ ዕናቶች ዕንባ በፈቃድ ውክልና ለሚያደምጡኝ ደጋጎች መላኬን አላቆምኩኝ። አሁን ታስህሳስ ወር ነው በዚህ ወር ላይ ሰሚ የለም ክርስሚያስ ጥድፊያ ላይ ስለሆኑ ነጮቹ። ስለዚህ ታህሳስ እና ጥር አጋማሽ ረፍት ይሆናል ማለት ነው። አዲሱ ጉዳይ የማይድኑ ሃሳቦች ላይ ጊዜ ማጥፋት ትቼያለሁ። አቁሜያለሁኝ። የማይድኑ ሚዲያዎችንም አላዳምጥም። ስለዚህ ሙግቱ ቀንሷል ማለት ነው። ሌላ በልቤ ሙዳይ የነበሩ ወገኖቼ ሲያዛልጣቸው ባይም ልወቅሳቸው ግን አልደፈርኩኝም። ስለምን? መብታቸው ስለሆነ። እርግጥ ነው በልቤ ያላቸውን ቦታ እንዳያጡ ባላዳምጣቸው ስለሚሻል አቅሜን ቆጥበውልኛል። እንዳከበርኳቸው ቢቀመጡ ይሻላል አድምጬ ከምቀንሳቸው። በሌላ በኩል ደግሞ ስሞግታቸው የነበ