መንትዮሾቹ ከቁልቋል አጫዋችነት ወደ ኦዳ አራጋቢነት የተገለበጡት ልብጣዊ ነፍሶች።


ንኳን ወደ ንበጥ ሎግ ሰላም ጡልኝ።

„ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን  ሰጡኝ፣
በመከራቸው ጊዜ ግን ተነስተህ አድነን ይላሉ።“
 ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፳፯
ንትዮሾቹ ከቁልቋል ጫዋችነት ወደ ኦዳ አራጋቢነት የተገለበጡት ልብጣዊ ፍሶች።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

·    ፍታ

የሰማዩ አሻቦ ሲጠበቅ ትውር ሳይል በደመና ተደሞ የዓውደ ዓመቱ ሥርዓቱ እዬተፈጠመ ነው። ነፍስ ተ - እንቅስቃሴ የተገደበ ይመስላል። ጸጥ - ረጭታ እንደ ቤተ መቃብር ሆኗል። የቤቴ እርግቦች እራሱ እሱ አፋቸውን  የተባሉ ይመስል ኮሽታ የላቸውም። ድምጥም የለም። ብቻ እርጋታ በ - ጫታ ሰፍኗል- ዕለቱ። ግርማ ሞገሱ ግን ያስፈራል። ጭሯቸው ብቻ የተንጫረረው ግንዶኢን ባልስ ዳንስ ላይ ይገኛሉ፤ እቴጌዋ ከመንበሯ ብቅ ብላ አፈር እንደ ማለት አሰኝቷት ከንፈሯን ነፋ አድርጋ ሽው ትላለች።
እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ቅኔዎቹ የአገሬ ውዶች? ዕለቱን ባዕላችን ብላችሁ ለምታከብሩት ሁሉ መልካም የስኬት ዓውድ ዓመት አንዲሆንላችሁ እመኛለሁኝ። ትህትና ይታከልበታል።
ወግ ገበታ።
ዛሬ ስለ ግልብጥ ሲብሊንገኖችን ትንሽ ነገር መቋጠር ፈለግሁኝ። ለነገሩ እኛንም ገልብጠው ጋልበውናል - የዛሬን አያድርገው እና።

ሁለቱም ሥም የለሾች ናቸው - ተዛሬ ላይ። ሥም የለሽነታቸው የሚያውቀው የቁልቋል አምላክ እና የኦዳ አምላክ ብቻ ናቸው። ግን ልበ - ጥፉን በሥም ይደግፉ እንዲሉ እነዛ ቅን፣ ደግ እና ቸር ወላጆች ምን የመሰለ ድንቅ ሥም አውጥተውላቸው ነበር። ልጅ ደመቀ መኮነን እና ልጅ ገዱ አንድርጋቸው ብለው።

ነገር ግን ነፍስ አውቀው ፖለቲከኛ ከሆኑ ጀምረው የወላጆቻቸውን ሥጦታ ንቀው የደመቁትም ገድ የሆኑትም ቀደመ ባለው ጊዜ ለቁልቋል ጣዖት ዛሬ ደግሞ ለኦዳ ጣዖት ሆነ። ማህከነ!
ከሰሞናቱ የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ሁለት አጤዎች እርግጫ ውድድር ላይ ስለነበሩበት ወግ አይቀር እርቀ - አባ ወራ ሆነው ነበሩ። በዛ የሁለት የኦዳውያን አጤዎች የእርግጫ ውድድር ታዳሚው በጭብጨባ እና በሽብሸባ እስኪበቃቸው አጅቧቸዋል ሥርጉትሻን ሳይጨምር።

ሥርጉትሻ አጀንዳዬ አይደሉም የእነሱ ነገር ቋቅ ብሎኛል ብላ የራሷን ጥሪ በሁለገቡ መስክ ስትከውን ነበር የሰነባበተችው - ተደጉ ፌስ ቡክ መናህሪያ ላይ። ለሥርጉትሻ ጥሪዋ ሰሚ ያጣው የድምጽ አልባዎቹ እናቶች ዕንባ ጉዳይ እንጂ የገበርዲን እና የከረባት የሻምላ የጥጋብ፤ የቁንጣን፤ የመታበይ፤ የአልጠግብ ባይ ጉጉስ ጉዳዮዋ አልነበረም እና።

ቀደም ባለው ጊዜም ቢሆን ቅንነትን በእዮባዊነት፤ በአዎንታዊነት እንደ ተፈጥሮዋ አመጣጥና የሰነቀቸው ሥርጉትሻ በጮሌው አፋቸው የገቡትን ቃል ሆነው ይገኙበታል በማለት እንጂ፤ እንዲህ ባዕድ እና ወገን በሚለይበት ተባደግ፤ ዝብርቅ፤ ዝልዝል ፖለቲካዊ ባህል መሆኑ ቢታወቅ ኑሮ ባልታደመችበት ነበር። ይድናሉ ተብሎ ተለፋላቸው። ያደክማሉ ቤተ - መራራዎች።

የሁለቱን ንጉሳንን ለማስታረቅ መንትዮሾቹ የኦዳ ተጠማቂ ተላኩ። ጎርባጣው አፈንጋጭ አጤ ለማ መገርሳ ረጭ ባለው ቤተ- መንግስታቸው አሻም ስላሉ ሳይሳካላቸው ነበር የተመለሰቱ። ለምን አልተሳካላቸውም? ስለምንስ እነሱ ተፈለጉ ጫን ያለውን ሃቅ አፍረጥርጠን እንናገራለን። እንሆ … ለቅኖች ብቻ።
·         ስለምን እነሱ ተላኩ?

ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል እና አቶ አህመድ ሸዴ አልተላኩም። ምርጦቹ የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት የህሊና ዓይን እነሱው ስለሆኑ። በነገራችን ላይ  የአጤ አብይ አህመድ ስውሩ የውጭ ጉዳይ ሚር አቶ አህመድ ሸዴ ናቸው። ይህን አገር እንዲያውቅ ጠሐይም በልባም ህሊናዋ መስጥራ የያዘቸው ቢሆንም ገለጥ ቢል አይከፋም። የውጭ ጉዳይ ሚር አማካሪም አቶ አህመድ ሸዴ ናቸው። የእኛዎቹ ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለ ባዶ ካዳ ናቸው።

ሌላው በማስተዋል ሊታይ የሚገባው ቁምነገር የአዳማው የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት መለያው ቅጥቅጥ አለመሆኑ ነው። ሁልጊዜ ድንገቴ የእንግዴ ልጅ መንታ መንታውን በመወለድ በኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ውስጥ አዲስ ሪከርድ ሰባሪ ሆኗል። ትዕይንቱ ገቪር በገቪር ሆኗል። አንዳንዱ  በአንድ ገቪር ሌላው በጣማራ ገቪር እያቅለሸለሽንም ቢሆንም አፍንጫችን ተሰንጎ ስንጋተው ባጅተናል።፡

ከቤታችሁ ቁጭ ብላችሁ በቀን ወዘተረፈ የተውኔት ሱናሜ ይላክላችኋል። የሚገርመው ተውኔቱ የሚታጀበው በበሬ መስዋዕትነት መሆኑ ነው። ደም ካላዬ አይሆንለትምና አቤቶ ጋዳወሞጋሳ። ፌስታው አገር ፈቷል። ዘወትር ፌስታ ነው። ድግሥ ነው። አስረሽ ምቺው ነው። ስለምን? የጠላት አገር ናት እና ኢትዮጵያ። ዕውነቱ ይኼው ነው። እንድፈረው እንደፈረደብን።

ጥሞናም ጥበብም ጎብኝቶት አያውቅም ቤተ - ኦዳን። ይዘርግፉታል ዝርግፍግፍግፎች። ለዚህ ምስጋና ይገባቸዋል።

ቤተ ንግሥናቸው ግን ፍርክ ፍርክ የሚለው እንዳልቦካ ጭቃ ምርጊት ነው።ይልቅ ኢትዮጵያዊው ካሜራ ዕድል ተከርችሞበት ባጅቶ የኖረውን ዘመኑን ሂሳብ እያወረራደ ነው፤ ስለትም ለዛው ለአጤ ኦዳውያን ሰጥ ለጥ ብሎ ሰግዶ እንዳስገባ ወፊቱ ሹክ ብላኛለች። ያው ስለቱ ለስታ ቅቤ ነው። የሞድ ተውኔቱ፤ የሽልማት ቅብጥርሶ ለኦዳ ልጆች በሽበሽ ሆኗል።

አጤ አብይ አህመድ፤ አጤ ለማ መገርሳ፤ ፊታውራሪ ታዬ ቦጋለ፤ ባላንባራስ ታዬ ዳንዳኣ፤ ደጃዝማች ታከለ ኡማ ሽልማት በሽልማት ሆነዋል። ቤተ - ክርስትያን እዬነደደች ሽልንግም፤ የወርቅ ካባም ትሸልማለች፤ ባህርዳር እዬተረገጠ ይሸልማል፤ ዕብዷ ዓለምም እንዲሁ ጭንቅ ለሚቀናበት የተውኔት ገቨር ለመሆን ትሸልማለች። በዚህ ውስጥ አረረ መረረ መከራቸውን ሲበሉ የባጁት ሌሎች ዜጎች በአፍ ቁልምጫ እና በፍሪንባ አይስክሬም ይሸነገላሉ።

ሁለቱ ከቁልቋል ወደ ኦዳ መጋለቢያነት የተለወጡት የብአዴን የሜዳ አራጋቢ ገመናቸው ደግሞ ቁጭ ብለው ቤት አድማቂ መሆናቸው አልበቃ ብሎ ደመቀወገዱ አደግድው ተላብሰው እንደ አባት አደሩ የአማራ ወግ ማለት ነው ኦዳ ሥር ወድቀው አጤ ለማ መገርሳን የሙጥኝ በሉ ተብለው ተልከው ነበር። አቤት ንጉሥ ሆይ! ያሉት ይፈጸም ዘንድ እንሆ መጥተናል ሲሉ ለጥ ብለው የጸጋ ስግደት ሰግደው እዬተንዘፈዘፉ ቀረቡ ከአጤ ለማ መገርሳ ፊት።
ቤቱታው … የሁለቱ አራጋቢ የተስፋ ወናዎች ደመቀወገዱ።

1.                   „እባከዎት አጤ ለማ ሆይ! በብልጽግና ይበልጽጉልን፤ ተመንድገን ተመንጥቀናል እና እርሰዎ ተነጥለው ሰርገው እንዳይቀሩብን“
2.                   „እኛ እርስዎን እንደ ጠ/ሚኒስተር ነው የምናዬዎት፤ አንዳችም ክብር እስታሁን አላጓደልንም ወደፊትም አናጓድልም።“
3.                   „እሺ! ይበሉን እንጂ ካለምንም ቅደመ ሁኔታ አንድም የአማራ ጥያቄ ላናነሳ እንምለለን። ህዝቡም አደግድጎ ይገዛላችሁ ዘንድ ህሊናውን እንሳናዳለን፤ በኦዳ ጥምቀት ይጠመቅ ዘንድ አበክረን እንተጋለን። ክብር ግርማ ሞገሥ ለኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ይሁን“
4.       „በሌላ በኩል ግን የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ሉባውያን ይገባኛል የሚለውን ሁሉ ይሆንለት ዘንድ የተለመደውን የሎሌነት ተግባር ሰጥ፤ ለጥ ብለን አደግድገን በተግባር እንፈጽማለን፤ ድልድይ ሆነንም እናስፈጽማለን። ብቻ ብቻ እርስዎ በመበልጸግ ይበልጽጉልን፤ እነሆ አዲስ ሳትላይት ስለምትመጥቅም በዛም ኦዳ አጤ ይሆን ዘንድ የፕሮፖጋንዳውን ነገር ለእኛ ይተወቱ“ ብለው ከንበል ደፋ አሉ ሁለቱ አራጋቢዎች። ቀጥለውም ቢሻም የአዲሱቱ ሳትላይት ሥም ግብር በእርስዎ ሥያሜ ለማ ሳትላይት ትሆን ዘንድ አጤ አብይን በትህትና እናሳስባለን። ታሰኝዎትምም ለክብረው 21 ጊዜ መድፍ እናስተኩሳለን። ብቻ ይሁንታዎትን ይስጡን።  
5.       አጤ ለማ ደግሞ በዱላቸው ከተደፉበት ቀና እንዲሉ ጎሳም ጎሰም አደረጉ እና „የተባለ ቢባል መደመር ብሎ ነገር አልገባኝም።  የኦሮሞ ህዝብ አንድ ሁለት ብሎ ቆጥሮ የሰጠን ስላልተገበረ አሻም አይሆንም ከመንገዴ ዞር በሉ ከፊቴ! እንቅፋት አትሆኑብኝ! ቢሆን ቢሆንም የገዳን መጠሐፍ ገላጭ ቤተ -ሌንጮን፤ ቤተ - አባ ዱላን፤ ካልመጡ አሻም“ አሉ። ተዛስ ተዛማ … ብለው አምላካችሁ አለ ድፍት ክንብል እንዳሉ አመዲቱን ላስ አድርገው እያጣጠሙ ቁልጭ ቁልጭ እያሉ አጤ ለማ ጥለዋቸው በላያቸው ላይ በሩን ከረቸሙባቸው። „ወንዳታ! ለሚ“ አሉ ሉባውያኑ።

·       ቱ የዘመን ገመናዎች ለምን ሽምግልናው አልተሳካላቸውም ?

ዋናው ብልህ ነገር አጤ አብይ አህመድ ግንቦቴዎችን ሲያባጭሉ „ለማ እንጂ እኔ አይደለሁም እሱ እንቅፋት እዬፈጠረብኝ ነው የሚለውን“ መስካሪ ሰነድ ሆነው ሁለቱ የኦዳ የጭን ረዶች እንዲሆኑ ነው የተፈለገው። እንግዲያውማ ወሳኞቹ የአጤ አብይ የልብ ሰዎች እኮ እቴጌ ሙፍርያት ካሜል እና ሊጋባ አህመድ ሸዴ ነበሩ።  

ሲመለሱ ሁለቱ የዘመን የብአዴን ጉዶች „አጤ አብይ አህመድ እውነትህን ነው አጤ ለማ መገርሳ ዋቆ እንዳስቸገርህ ተረድተናል። በችሎቱ ላይ ሰነዳችን እናቀርባለን፤ ምስክርነታችን እንሰጣለን። 

መቸገርህን፤ መጨነቀህን፤ እሱ እንደ በደለህ እንዳስቸገረህም እናውጃለን እንድች ብለን አንዲትም ቅንጣት በአገር አቅም ላይ የአማራ ተሳትፎ ላናነሳብህ ቃል ለምድር ለሰማይ“ ብለው በኦዳ ለስታ ቅቤ ማህላቸውን ጥርቅም አድርገው ማሉ። በአንድ ድምጥ። የዳቦ ሥምም አዲስ ተመሰጥሮ ነው እንጂ ወጣላቸው። ከዛ እርካታ አገኙ ሸፍጠኛው እና ሴረኛው አጤ አብይ አህመድ።

ያው የጢባ ጢቦሹ ጨዋታ ቤተ - አማራ ነውና። ስለዚህም ሬሳው ኦሮማራ አፈሪቱን ረገፍ … ረገፍ አድርጎ ተነሳ እና የፖለቲካ ሰዎች በአዳራሽ፤ የፋኖ ባለሟሎች ስብሰባ በሚሊዬንም አዳራሽ ጥቃትን እና መሰቃን እስኪበቃቸው ይጎነጩ ዘንድ ተወሰነ። ሌላ የሞት ዓዋጅ ይሉኃል ይሄ ነው።

ሁለቱ የብአዴን የገመና ጥንዝሎች „ችግር ፈጣሪው አጤ አብይ ሳይሆን አጤ ለማ መገርሳ ስለመሆኑ እኛው አረጋግጠናል፤ ሰነዱም በእጃችን ሥር ይገኛል“ ሲሉ የሞገሳ ግንባር ተጠማቂዎች ሁለቱ የኦዳ ስንክሳሮች ምስክርነቱን አሰረግጠው ተናገሩ በዬ አጋቸው።

ይህ በዚህ እንዳለ ደግሞ ሰበር መረጃ የማያጣው የአዳማው ሥርዕዎ መንግሥት አበይወለማ እርቀ ሰላም አወረዱ ብሎ በሰበር የሁለቱ ተጠማቂ እርካሽ አልባሌ ገዳውያን ኮቴ ሳይደርቅ መለከት ተነፋ፤ ነጋሪት ተጎሰመ። ዓዋጅም ተነገረ።

በዚህ ላይ ሁለተኛ ትርፍም ተገኜ ለኦሮሙማ ፖለቲካ መፍትሄ ሰጪው የኦሮሞ ፖለቲካ ባህል እንጂ ሌላ ተለጣፊ የኦዳ አሻንጉሊት አለመሆኑ በይፋ ይረጋገጥ ዘንድ ቤተ ኦዳ አሳምሮ አተመበት። እናም በቀላል ግጥምጥሞሽ ሰንጋ ቀርቦ ሁለቱ ኮርማዎች እረቀ ሰላም ፈጠሙ ተባለ። 

ለማን ሲባል? ለገዳ ሥርዓት ቤተኞች ሰናይ ወሐሴት ያግኙ ተብሎ። ተውኔቱ ይሄው ነው። የልብን በልባም በማባጨል መከወን። የ እነ አልጫ ድካምም የውርንጫ ድካም ሆኑ በከንቱነት ሰኔል እና ቹቻ ተቀብሎ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጠመ።፡

·         ግቡ ስለ ቅደመ ሁኔታው።

ውዶቼ የአገሬ ልጆች።  አቶ ዳውድ ኢብሳ ሲገቡ ምዕራፍ አንድ መደራደሪያ ይዘው ገቡ። ተፈጠም። አቶ ጃዋር አህመድ አገር ሲገባም እንዲሁ ቅደመ ሁኔታ ይዞ ገባ። ተፈጠመ። ንጉሥ አይከሰስ እንዲሉ ኦነጋውያኑ ያሉት ይፈጸማል፤ የፈለጉትን ኢሰባዕዊ ድርጊት ይፈጽማሉ ህግ በእነሱ ላይ ላይሰራ ማህላ አለበት።

አሁን ምዕራፍ ሦስት ደግሞ አጤ ለማ መገርሳ ያቀርቡት እንደ አቶ ጸጋዬ አራራስ ገለጣ ከሆነ ያሰቡትን ሁሉ በመቀበል በቀደመው አቋማቸው ላይ እንደሚገኙ ተሰሞናቱ ንግግር ቢጤ አድርገዋል። ምዕራፍ አራት ተጄኒራል ብርኃኑ ጁላ፤ ወይ ተ አዬር ኃይሉ፤ ወይ ደግሞ ተብጄ ከማል ገልቹ ይጠበቃል። ያው ሰንጋውም በተራ ተሰልፎ ይጠባበቃል።

ግቡ የአማራ የህልውና ተጋድሎ አንዳችም ጥያቄ እንዳይጠዬቅ አግር ከወርች ለማሰር ነው። ኢትዮጵያን ኦሮማያዝድ በማድርግ እና በማስደረግ እረገድ የቅድሚያ ተጠያቂው ደመቀወገዱ ስለመሆናቸው ልብ ያለው ሁሉ ህሊናው አድርጎ ይታገለው ዘንድ ጠሐፊ ሥርጉተ ሥላሴ በትህትና ታሳስባለች።

ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረጉን እነዚህ ሁለት ነፍሶች ናቸው። የሚገርመው ጠንካራ የሚባሉ የአማራ ሊሂቃን በማስመንጠር እና አሳልፎ በመስጠትም ተጠያቂዎች እነዚሁ የመንፈስ ነቀዞች ናቸው። እነ ይሁዳ። ልዝ እንጨቶች ወይ አይነዱ ወይ አያነዱ።

ሁን ሦስተኛው ምዕራፍ መደራደሪያ የለማ ቅድመ ሁኔታ ማንፌስቶ ተብሎ ይያዝ። ሌላም ተሰሞኑ ተረኛ ዓይነ እርግቡን ገላልጦ ከች ብሏል እሱን በሌላ ጡሑፍ አንገናኛለን። ኦነግ ተ18 ተተርትሯል። ሁሉም የየራሱ ማንፌስቶ ይዞ ብቅ ይላል መከረኛው ኢትዮጵያዊው ዜጋ ደግሞ እንደ ፈረደበት ተሸከም ይባላል።

·         እም! እያመጠ እንዲህ መሆኑ ይታወቅ።

1)              የአዲስ አበባ ጉዳይ እንዳይነሳ፤ እርክክቡ ተፈጥሟል።
2)              የቋንቋ ፌድራሊዝሙ እንዲቀጥል ተበይኗል፤
3)              ህገ-መንግሥት እንዳይሻሻል መደመደሚያ ላይ ተደርሷል፤
4)              አማራ ልጅ ሆኖ ብቅ ያለ ሁሉ በገዳ ጥምቀት ያልተፈጸመለት
              መወገድ ወይ ካቴና እንዲጠበቀው ተሰንዷል።
5)              በአዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ኦዳውያን ብቻ በቁልፍ መሪነት
              እንዲቀመጡ ተደንግጓል፤
6)              የወሎ ሥጦታ በተስተካከለ ሙቀት ካለምንም ኮሽታ ልክ እንደ
              አዲስ አበባው እንዲፈጸም ተረቂቅነት ወደ ፍጣሜ ተቃርቧል፤
              ለዚህ ብጄ/ ከማል ገልቹ ከመታበይ ጋር ሙሉ ኃላፊነት
              ተሰጥቷቸዋል፤
7)              የአዲስ አባባ የዴሞግራፊ ምህንድስና ተጠነክሮ እንዲፈጠም
              ስምምነቱ ደርቷል፤
8)              ኦሮምኛ ካለምንም ቅደመ ሁኔታ በአማራ ክልል ሁለተኛ ቋንቋ
              እንዲሆን ተበይኗል፤ ለአማራ ህዝብ ግን ከኦሮምኛ ትግረኛ
              ይበልጥበታል፤ ኤርትራንም ጭምር መንፈሱን መጋራት
              ስለሚቻል፤ ይቀለናልም። ብዙ አቅም አይጠይቀንም። ለግዕዝ
              ቋንቋም ቅርብ ነው። ሚስጢራችን ያለውም ከግዕዛችን ነው።   
9)              ኦዳውያን በግዛታቸው ውስጥ ስለሚፈጽሙት ማናቸውም
              በደል ድምጥ የኦዳው ተጠማቂ ግርባው ብአዴን እንዳያሰማ፤
             ይልቁንም በተለመደው መንገድ ተባባሪ እንዲሆን
             ተፈርሞበታል።
10)          የአማራ ህዝብ በሁለተኛ ዜግነት ተረግጦ እንዲቀጥል
              ታትሟል፤
11)          አማርኛ ቋንቋ የበላይነቱን ለማስቀረት በሚወሰደው እርምጃ
              ሙሉ አጋዥ ግርባው ብአዴን እንዲሆን ተወስኗል፤
12)          በክልሉ የኦዳው ዓርማ እጩ ሆኖ እንዲቀርብ ታጭቷል፤
13)          ቀጥታ አመራሩን ቲም ገዳ ንጉሱ እና እጬዋ፤ የልብ አድርስዋ
              ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሆኑ የልብ ስምምነት ተከናውኗል፤
14)          ኦዳውያኑ በፈለጉት ሰዓት እና ጊዜ ክልለሉን ጥሰው ገብተው
              የፈለጉትን፤ ያሻቸውን ያደርጉ ዘንድ ፊርማው ፍጥምጥሙ
              ተፈጠመ።

·         ነገረ ሁለቱ የኦዳ ባሕረ የጥምቀት ልጆችደመቀወገዱ።

ጭንቅላት አላቸው፤ መተንፈሻ ቧንቧቸው ግን ተገጥሞላቸዋል። ልቡ የተገጠመው በለስታ ቅቤ ተለውሶ ሲሆን የአሪስዋ አምቤት በሥርዓቱ ላይ በመንፈስ እንደተገኜች እነ ማህበረ ሹክታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ርገት ይሁን።

ይህ ይጨርስለት እንጂ አጅሬ ሰላቢው ጠ/ሚር ገብተው ካልተረተሩት የልብ አድርሱ የኢትዮ 360 ውይይት ነበር። እኔ የተንታኙ የአቶ ሃብታሙ አያሌው አቋም ነው ያለኝ በዚኽኛው ውይይት ላይ። የተንታኙ አቶ ኤርምያስ ለገሰ በጠሚር አብይን ፖለቲካ ነጥሎ የሚያቀርበው ዕድምታ ማጠቃለያ አይመቸኝም። ርህርህና አያበዛ ነው። 

አቶ ኤርምያስ ለገሰ በአንድ ጉዳይ ጸንቶ ቆሟል። የእሱ መርህ በማይናወጽ ሁኔታ ጠሚሩ ካመዘነው ጋር ይሄዳሉ የሚል አቋም አለው። ኦነጋዊነታቸው ተጋርዶበታል። እንደ ዓይነ ጥላ ነገር። ተስፈኛም ነው። እኔ ተሰፈኛ በነበርኩበት ጊዜ እሱ ሞጋች፤ እሱ ተስፈኛ ሲሆን እኔ ሞጋች። አንገረምም። 

ይህ ማለት የጠሚሩ ውስጥ በውል ያልፈተሼ አቋም ነው። ጠፍቶት ነው ብዬ አላስብም። ተጽዕኖ የሚፈጥርበት የቃል ውል እንዳለበት አሰባለሁኝ። ምክንያቱም ፖለቲካ የውስጥ አቅምን ተሰጥኦም ስለለው ይህ አቋሙ የሌላ ጫና እንደለበት ነው እኔ በግሌ እማስበው። ጠሚሩ በይፋ ኦነግ ነበርኩኝ እያሉ ይህን ያስታማዋል፤ ያባብለዋል፤ ያቆላምጠዋል። በእሳቸው ላይ በጣም የበዛ የፖለቲካ ርህርህና አለበት አቶ ኤርምያስ ለገሰ።

እሱ ብቻ ሳይሆን ሌላም መንፈስ እንዳለ አስተውላለሁኝ በሌላ ሚዲያ ላይ እንዳለው ኢትዮ 360 ላይም። ያ 86ቱ እልቂትን ገለጣ ሲያቆላምጡ ያዬኋቸው የልቦች ልባሞች እንደነበሩም ስላስተዋልኩኝ በሌላ ሚዲያ። መቼም ይሄ ዘመን ስንቱን እንደ ቀማን፤ ስንቱን እንደማረከን በተደሞ ያለን ሰዎች እናውቀዋለን። ምርኮኛው በዛ በአንድም በሌላም።

ጥድፊያ በሌለበት ህይወት ወስጥ ያለን ነፍሶች ከልብ ሆነን መንፈሶቻችን ስንነጠቅ እያስተዋልን ስለሆን። ይህን ሚሽን የሚከውኑት ደግሞ አጤ አብይ አህድ ናቸው። በግል ስልክ ይደውላሉ። በቤተሰብ ይመጣሉ። እንደ ልማና ስጦታቸው የመስለብም ልዩ ተስጥኦ አላቸው። አነሆለሉት ህዝበ አዳም ሂዋንን።

ለባው እና ስኬቱ።

·        እስልምናን በአባት፤ ( አባት አንድም ቀን ቤተ መንግሥት ሳይታዩ አለፈዋል።)
·        ክርስትናን እኔም ነኝ ባይ ናቸው፤ (በመላሾ በጉርሻ በውስጥንት ግን በትነት)
·        ጎንደሬነትን በሚስት፤ (በግፍ የታጨደው ደግሞ ጎንደሬ ሊሂቅ ነው።)
·        ሙራንን በቀለም ዕውቀት ቤተኝነት፤
·        ዲፕሎማሲውን ግራ ቀኙን የኢትዮጵያ በርን ቧ አድርጎ ከፍቶ እንዳሻችሁ ሁኑ በማለት፤
·        ተዋህዶን በእርቅ ሥም፤
·        ንጹኃን ዜጎችን በአስፓልት አስኮባ ጠረጋ  እና በእህል ማጭድ ዘመቻ፤
·        ኢትዮጵያን በማር ዘነብ የወግ ገበታ፤
·        እናቶችን በዕንባ አዋጭ የአንስት ካቢኔ፤
·        ባለቤት አልባዎችን በግብረ ሰናይ ድርጀት ብቅ በማለት በቅብ ግርዶሽ እርዳታ፤
·        ኦሮሞን በገዳ ሥርዓት ግንባር አስፈጻሚነት እና ሁሉ በደጅ እና በእጅ እንዳሻቸው እንዲሆኑ በመፍቀድ፤ በግልጥ በ አደባባይ እኔ ሃበሻ አይደለሁም በማለት። በ እናቴ የሽዋ ኦሮሞ ነኝ ሥነ ልቦናዬም ተግባሬም ኦሮሙማ ነው፤ ቅይጥ ዝንቅ የለብኝም በማለት።
·        ሞራላዊ እሳቤን በአደንዝዜ የማይንድ ሴት ዘመቻ፤
·        ጸራ አማራ ኢሊቶችን አማራን በማሳጣት በመጸዬፍ፤ በማሳደድ፤ በመቀርደድ፤ በማግለል፤ በማስወገድ በአራቱ ማዕዘን ወጥር ሰንጎ በማያዝ፤ ለዓለም በተገኜው አጋጣሚ ሁሉ በማሳጣት የልብ አድርስነት። አቅሙን እንኩትኩት አድርጎ በመሰባበር። የልባቸውን ካደረሱ በኋላ ትውር አላሉም። በዬሳምንቱ ምክንያት እዬፈለጉ ለሰለባቸው ሲዳንሱበት በባጁት የአማራ ክልል። ይህችን ጡሑፍ አድነው ካነበቡት በኋላ ግን ሊሄዱ ይችላሉ። እስታሁን ልባቸው ሳጅን ሳጥናኤል ተመስገን ጥሩነህ መድበው የልባቸውን እያደረሱላቸው ነው። ማብረ - ሲኦል።

ስማሚያ ለአብነት ሃድራ።
  
·       ቅኔቹ ዬፌስ ቡክ ልቦቼ ብለጌን ትከታተሉ ዘንድ ሊንኩ ይህ ነው። ወደ ብሎጌ ጎራ ስትሉ ብርቱካናማ ቦክስ ዲያሎግ ይመጣል፤ ያን ስትጫኑት በሩ ይከፈታል። ሊንኩ ይሄው ነው። ዘለግ ያለ ሙግት ሲኖረኝ በብሎጌ ከች እላለሁኝ።
·       ብሎጌ ህሊናዎች ደግሞ በዚህ የመግቢያ በር ካለምንም የእልፍኝ አስከልካይ መግባት ይቻላል። አጫጭር ጹሑፎች ሲኖሩኝ ፌስ ቡክ ላይ አዘውትራለሁኝ። ፌስ ቡክ እድሜውን ያርዝመው እንጂ ለአጭር ትጥቅ ልዩ ስጦታ ምቹ ማሳ ነው። ካለዘጉት እውነት ፈሪው ጠሚር አብይ አህመድ። ቢያዘጉትም በሌሎች ብቅ ይባላል። ዛሬ አለም ብዙ አማራጭ አላት።
·       በድምጥ ሲያሰኜን ደግሞ ይኸው እና ቁጥር አንድ ዩቱብ ቻናሌ  በአገርኛ በአውራው ሉላዊ ቋንቋ በእጬጌ አማርኛ።

·       ስለ ፍቅራዊነት ብናውቅስ ለምትሉ ቅኔዎቼ ደግሞ ይኸውና ቁጥር ሁለት ዩቱቤ።

ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

የኔዎቹ መሸቢያ ጊዜን ተመኜሁ።
ኑሩልኝ። እኔ ካለ እናንተ ምንም ነኝ እና - ትቢያ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።