ልጥፎች

ከሜይ 28, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ግንቦት 20 ለእኔ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ። ከጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ።

ምስል

ግንቦት 20 ለእኔ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ። ከጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ።

ምስል

ግንቦት 20 ለእኔ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ። ከጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ።

ምስል
 እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።  ግንቦት 20 ለእኔ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ። “ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳን አይሰለጥንብኝም። የ ሐ ዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፲፪” ከጸሐፊ እና ተርጓሚ ከአቶ መስፍን ማሞ ተሰማ። ሠላም ለናንተ ይሁን! ይላሉ ጸሐፊ እና ተርጓሚ አቶ መስፍን ተሰማ ከ አውስትራልያ ሲዲኒ … እኔም ሥርጉተ ሥላሴ ከእመ ዝማታ ሲወዘርላንድ ዘንጠፍ ያለ ትሁታዊ ሰላምታዬ ለታዳሚዎቻችን ይድረስ እላለሁኝ። ውዶቼ ... አሁን ወደ ጸሐፊው አቶ መስፍን ማሞ ጭብጥ አብረን ብያለሁ ጀርገድ ባለ ልስሉስ አክብሮት … እንሆ …  በድምጽ ... https://www.youtube.com/watch?v=gQ-HCCzZ_T0&feature=youtu.be "ግንቦት 20 ለእኔ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ።"  ከጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ። በአምባ ገነኑ የደርግ ዘመነ መንግሥት እስከ ግንቦት 20/1983 ዓ / ም ኢትዮጵያውያን ( ከዘር ሐረጋቸው በፊትና በላይ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና የማይደራደሩ፣ ታሪካቸውን በታሪክነት ተቀበለው የታሪክ ቂም በቀል ያልወረሱና ለዚህም ያልዘመቱ   ሁሉ )  ሀገር ነበራቸው፤ መቀመጫ። ሰሜን ብንወጣ ጎጆ ብንቀልስ፤ ደቡብ ብንወርድ ስራ ብንፈልግ፤ ምሥራቅ ብንቀመጥ ሱቅ ብንከፍት፤ ምዕራብ ብንኖር ብንነግድ/ ብናስተም ር ማንም መጤ፥ ማንም   ሠፋሪ እያለ አያፈናቅለንም፥ በገጀራና በቀስት አይፈጀንም ነበር። እንደ መንግሥት ደርግ ሁሉንም ዘር