2019 ኤፕሪል 25, ሐሙስ

እህት ርዕዮት ከ አላዛሯ ኢትዮጵያ ጎን መቆም ያስመሰግናል! ምርቃት!


እንኳን ደህና መጡልኝ
ከአላዛሯ ኢትዮጵያ ጎን
መቆም ያስመሰግናል።
ምርቃት


ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤
--- ምን ታደርጋለህአልኩት።

 መጽሐፈ መክብብ  ቁጥር 

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከእማ ዚዊዘርላንድ።
25.04.2019

·        መነሻ።
ቴዎድሮስ ጸጋዬ ለኢሳት የሰጠው ቃለምልልስ እንዳይሰራጭ በአፋኙ ቡድን ታግዷል
ጠያቂዋ ርዕዮት አለሙ የተፈጠረውን እንዲህ ታብራራለች፡፡
Published on Apr 24, 2019

·    ልበጉዳይ።

የኢሳት ጋዜጠኛ ወ/ት ርዕዮት ዓለሙ „ትኩረት“ ላይ አቻዋን ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ጸጋዬን የርዮት ሚዲያን ዋና አዘጋጅ ቃለ ምልልስ አድርጋ እንደነበር ትናንት አዳመጥኩኝ። ያ ቃለ ምልልስ ወደ ህዝብ ለማድረስ የድርጅቱ የኢሳት ኤዲቲንግ ክፍል ፈቃድ ስለነሳው ይህን አስመልክቶ ርዕዮት ለርዮት በድጋሚ ተገናኝተው የተደረገ ቃለ ምልልስ ግርም እያለኝ ነበር የተከታተልኩት።

ከኢትዮጵያ አልፎም ውጭ አገር ይህን መሰል መከራ ከኖረ አገር ውስጥ ያሉ ሚዲያዎች ዕድሜያቸው አጭር ስለመሆኑ ፍንጭ ይሰጣል። እርግጥ ነው ይህ አንድ አፍታን የሚመለከት አይሆንም። የማያረግዱት ግን ነገ ቀጣይ ይሆናሉ ብዬ አላስብም። ኦንግ መሰረቱ እስኪጠናከር ድረስ ነው የሚፈቅድላቸው እንጂ ከዛ የሚሆነው ይሆናል። ራሱ ክርስትና ወዮልህ ነው። ለ ኢትዮጵያዊው እስልምናም አይመጥነውም የኦነግ መንፈስ፤

ለነገሩ ለጋዜጠኛ ወ/ርት ርዕዮት አለሙ አዲስ ነገር ሆኖባታል። የዴያስፖራ ፖለቲካ መልኩን፤ ይዘቱን፤ ሆድ ዕቃውን አሁን አያዬችው ይመሰለኝል። አታውቀውም ነበር።
እሷ ለቀለጠችበት ዓላማ እውነት እና ውጭ አገር የነበረው የፖለቲካ ውስጠት ወጥ
 አድርጋ ነበር ያዬቸው። ግን አልነበረም።

ዛሬ የጠ/ሚር አብይ ካቢኔ የሚያደርገውን ስውር አፈና ውጭ አገር ግንቦት 7 ሲተረጉመው የነበረው ነበር በወገኖቹ ላይ፤ ለነጻነት ትግሉ በንጽህና በነፃ አቅማቸውን፤ ጉልበታቸውን ሁለመናቸውን በሰጡት ላይ ተከተታይ ዘመቻ ላይ ነበር። ከገቡበት እዬገባ ያፍልሳቸው ነበር። 

አገር ውስጥ ህወሃት ውጭ ደግሞ ግንቦት 7 መዋጥ፤ መጠቅለል፤ መበር ላልፈለጉ ነፍሶች ያው ካቴናው የለም እንጂ እኩል ለእኩል መሳ ለመሳ ፈተናው ነበር።  የነበረው አማራጭ ቤትን ዘግቶ መቀመጥ ብቻ።

አሁን እሱም አገር ቤት ደርሶት እያዬው ነው ሂድ ሲባል የሚሄድ፤ ቁም ሲባል የሚቆም፤ አውርድ ሲባል የሚያወርድ፤ ጋብዝ ሲባል የሚጋብዝ … ኢሳት አገር ቤት እንዲገባ የተፈቀደበት ውሉ አልገባውም ግንቦት 7፤ ሌላውም እንዲሁ …  አቅሙን ከሁለት ለመተርትር ሌላ ምርጫ አልነበረም …

የሆነ ሆኖ የነገረ ግንቦት 7 አካሄድ የሃሳብ ነፃነት፤ የመደራጀት ነፃነት ቀርቶ ሁለት ሰዎች ሆነው አንድ ፕሮጀክት ለመሥራት ፈቃዱ ከበታች አጤዎቹ መሰጠት አለበት። ያልተበተነ፤ ያልተናደ፤ ያልፈረሰ አቅም የለም። ያልከሰለ ማንነት የለም። እጣ ነፍሱን ያልቀረ የእውነት ማዕቀፍ የለም። ባለቤት አልባ ነፍሶች ብዙ ነበሩ።

ጋዜጠኛ ወ/ት ርዕዮት ዓለሙ አሁን ስታዬው፤ አሁን ስተመዝነው፤ አሁን ስትለካው መታሰሯ መሰቃየቷ እና ራዕዮዋ ምን ያህል ፈተና ውስጥ አንዳሉ የገባት ይመሰለኛል። እንኳንም በህይወት ኑራ አዬቸው። ያለፉት ሰማዕታቱማ እነሺ ብሬ እነ የኔሰው፤ እነ አወቀ ይህን አያዩም፤ አይሰሙም። መኖር ግን ሁሉንም ይሰጣል።

ምን አልባት ይህ ይፋዊ የሆነ ስለሆነ፤ በራሷ የደረሰ ስለሆነ ነው እንጂ ብዙ ረቀቅ ያሉ እገዳዎች፤ ማጠልሸቶች፤ የኖርንባቸው ናቸው። ጉግልን እንኳን ሊንክ ማድረግ የማይፈቀድልን ነፍሶች አለን። ይህን ሉላዊ ዓለም በረከት እንኳን መንፈግ ምን ምን እንደሚል ቀራንዮ ይመሰክረው … 

ድርጅት ከተባለው በላይም በቀንጣ ነፍስ ብዙ መልካም ተግባሮች ተከውነው ድጋፉ ቀርቶ ሰላም ማሳጣቱ ንጠቱ መከራ ነበር። የሚያሳዝነው አሁንም አለፈ ስንል ከዜሮ ለመጀመር መገደዳችን ነው። እግዚሩ ይይለት የአብዩ ነፍስ///

አንድ ብንሆን እኮ ማንም ከእኛ አንድነት ሙሉ አቅም ውጭ አቅም ኖሮት እንዲህ ሁለመናችን በገፍ ሰጥተን ቁምን የምንለምንበት ሁኔታ ባልተፈጠረም ወይንም እንዲህ የበይ ተመልካች ልንሆን ባልተገደድን ነበር። ለዛውም የከሰለው፤ በሰብ ደም ግፍ የሰመጠው ኢህአዴግ? እንሆ አሁን የነፃነት ትግላችን ሁሉ ኤክስፓዬርድ አድርጓል ለውራጅ እንኳን ሳንበቃ …  

·       ጊዜ፡፤

የሆነ ሆኖ ጥሩ ጊዜ ነው። የነጠረ ጊዜ ነው። ለዚህ ነበር እኔ የምንታገልለትን ዓላማ አላወቅነውም እያልኩ እጽፍ የነበረው። አቅማችን ሰብሳቢ አጥቶ ብትን ሲል ከልብ እያዘንኩኝ ነው።

ትግላችን ለሰው ልጆች እኩልነት፤ የመኖር ዋስትና፤ ለህግ የበላይነት፤ ለዜጎች የህሊና
ነፃነት፤ ለአገር ሉዕላዊነት ቢሆን እኮ ወደ ኢጎ ቁልል ግንባታ የሚወሰድ ነገር አልነበረም።

እኛ የታገልንለት ለግለሰቦች ዝና፤ ሥም፤ ክብር እና ልዕልና ብቻ እና ብቻ ነበር። ቀድሞ ነገር ፖሊሲ የሌለው የነፃነት ትግልን እኮ ዓለም አስተናግዳ አታውቅም። ለዛ ያን ያህል አቅም ማፈስስ አይገባንም ነበር። አቅሙም ይሁን እርስ በርሳችን ግን በመንፈስ መተራረድ አልነበረብንም።

አንድ የፖለቲካ ድርጅት ግልጽ አላማ ፕሮግራም እና ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል፤ የመደመሩ ፖሊሲም እኮ በድፍኑ ነው ህዝበ አዳምን እያሰገረ የሚገኘው። እሱ እራሱ አቤቱ መደመርን ማለቴ ነው ውስጡን ያውቀዋል ግን ሌላው አይጠይቅም አይመረመርም ስለምን አይልም … የፖሊሲ አልቦሹን መጪታ ... 

እኛ የምንታገልለት የእውነት መርህ ስንናገርለት የኖርነው ለግለሰቦች ሰብዕና ግንባታ እንጂ እኛ ለምንታገልለት ግልጽ ዓላማ ሙሉዑ የህሊና ነፃነት ቢሆን ኖሮ ወጀብ በመጣ ቁጥር እንዲህ አይናጥም፤ እንዲህ አይፍረከረክም ነበር። እንዲህ ባዶ እጁን ቆሞ ቅንጥብጣቢ እና ጭፍጫፊ ለማኝ አይሆንም ነበር። የተጋንለት አለማ እንዲህም ከሚሊዮን ማህል ሆኖ አይንሳፈፍም ነበር። እንዲህም አፍሰን የምንለቅምበት፤ ለቀምን እምናፈስበት ሁኔታ አይፈጠርም ነበር። ስንት አቅምተስፋ ቆራጭ ሆኖ አንጋጦ እዬዬ ስለመሆኑ ቤቱ ይቁጠረው … አይዋ መታፈን ገና ምን ታይቶ ዘውዱን ደፍቶ ነገ ይነዳል … ያስደገድጋል ...

ሃሳብ ያለው ግልጽ ሚዛናዊ አቅም ሁሉን አቃፊ አድማጭ አቅም ኖሮን ቢሆን ኖሮ እንዲህም ባዶ እጃችን አጨብጭበን ባልቀረን ነበር። ትንሽ ማናሻ እርሾ ይኖረንም ነበር። በር የለሹ አዳራሽ ምክነት ሆነ ስንበቱ።

አሁን ከቶ ምን አለን? እኮ ምን የቀረን አለ? የ27 ዓመት ተጋድሎ እኮ ለኦነግ አስረክበን እጃችን አጣጥፈን ነው የተቀመጥነው። ይህም ሆኖ ዜሮ ላይ በረዶ ላይ ተኝተን እንኳን በዛው ላይ እንድንዛገጥም ይፈለጋል። እኛ ለህሊና ነፃነት አቅም ብንታገል ኖሮ የጎደለውን ሞልቶ፤ የደከመውን አግዞ፤ የተነደለውን ደፍኖ አቅምን በቅጡ ማስተዳደር ይቻል ነበር። አቅምን እያሳደዱ ከመቅበር። የተኖረው እንዲህ ነበር።

ፈጣሪን እማመሰግነው የጠፋችብኝን ንጽህት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን ስላገኘሁ እኔ ሻማ አብርቻለሁኝ። አገር ቤት ገብታ ቢሆን ኖሮ ግን በዚህ አቅሟ ልክ አናገኛትም ነበር … ወይ ካቴና ወይ ብወዛ ይገጥማት ነበር። አሁን ግን ከንጥር መንፈሷ ጋር መገኘቷ ለእሷም ክብሯ ነው። ግን ለህይወቷ መጠንቀቅ ይኖርበታል፤ እንዲህ መረር ያለውን እውነት ለመጋፈጥ በር በሁሉም አቅጣጫ ተከፍቶ አይሆንም።

ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከሰርም። ትናንት የእኔ የምትለው ግዙፍ ሃይል ነበራት፤ ዛሬ ግን የቀነሰ ነው ያለው፤ እዬጠነከረች ስትመጣ ደግሞ በዛው ልክ አደጋው ሰፊ ስለሆነ ጥንቁቅ መሆን ይገባል፤ የታዬው ሁሉ አይገዛም፤ የተዘራው ሁሉ አይበቅልም፤ „ሁሉ ተፈቅዷል ሁሉ ግን አይጠቅምንም“ ቃለ ህይወት መቀበል ግድ ይላል።

ደግሞ ዕደለኛ ናት እህት ከአጠገብ ስደት አገር መኖር ገነት ነው። በቃ እዬር ነው። ጓደኛም፤ አማካሪም፤ ረዳትም፤ አጽናኝም እህት ስላላት በቅርበት ብዙም አንደበፊቱ መዘናጋት አያስለፈልግም።

ምንጊዜም ከእውነት ጎን መቆም መርህ ሊሆን ይገባል ለሰው ልጅ። እውነት እስካለ ድረስ መደገፍ፤ እውነት እስር ቤት ሲገባ ደግሞ ስለ እውነት መማገድ የተገባ ነው። ሁሎችም ወገኖቻችን ናቸው። ስንደግፍም ስንቃወምም ከእውነት፤ ከፋክት ሴል መነሳት ይገባል።

ይህ አጋጣሚ ስለምን እኔ ስገለል፤ ስገፋ፤ ሥሜ ሲጠፋ፤ መጸሐፍቶቼ ሲታገዱ በሁሉም ቦታ ስለምን ስሳደድ እንደነበር ዛሬ ላይ ንጽህት ወ/ት ርዕዮት አለሙ ለሷም ወጨፎው እዬደረሳት ሲሆነ ነገ በነገ ሙሉ ለሙሉ ዶፎ ሲያጥለቅልቃት እምታገልለትን፤ እምሰዋለትን ዓላም ለማን እና ለምን ስለነበር ትረዳዋለች ለዛውም ብቻዬን ከሳተናው ድህረ ገጽ በስተቀር አይዞሽ የሚል በሌለበት።

አሁንም ቢሆን አላዛሯ ኢትዮጵያ የሰው ደሃ ስለሆነች ጥቂቶች ብንሆንም እግዚአብሄር የቅኖች አምላክ ስለሆነ እውነት የምታበራበት ቀን ይመጣል። አቅም ኖሮን ቢሆን እኮ ቀድሞ ነገር ኢህአዴግን ደግፈን እምንቆምበት ምንምምክንያት አልነበረም። ኢህዴግ እኮ የተቃጠለ ካርቦን ነው የነበረው።

ከእሱ ከውስጡ የተሻሉ ነፍሶች ሲወጡ ብርቃችን የሆኑት ከዚህ ያንን በማጣችን ነበር። ግንቦት 7 ለአቅመ አዳም ያልደረስ ድርጅት ስለነበር ነው ይህ ሁሉ ገመና የመጣው። ወይ እሱ አይችል፤ ወይ ለሚችሉት ቦታ አይለቅ ማህል ላይ ተደንቅሮ ሁሉም እንዲህ ተቀበረ።

የነጻነት ተጋድሏችን እያዬን እዬሰማን ተቀብሯል። አሁን ያለው አገር ቤት ነፃነት የሚባለው ነገር ማካሄጃ እንጂ ዘላቂ አይሆንም … ኦነግ በሙሉ ቁመና እስኪደራጅ ድረስ ነው እንጂ ሁሉም ነገር ፌክ ነው።

የኦነግ ሠራዊት በሙሉ ቁመና ተገኝቶ አዲስ አበባን እወራለሁ ሲል በሦስተኛ ወገን ድርድር እስከማድረግ የሚዘልቅ መከራ አግቷል። ጠብቁት። የ80ዎቹን ታሪክ መድገም ነው የሚሻው። የኦነጉ ኦዴፓም የሚተጋው ለዚህ ነው። ተወደደም ተጠላም።

የሰሞኑን ድራማ ተመልከቱት ሰሜን ሸዋ እና ወሎ  ላይ ሁሉ በረድ ከወረደ በኋዋላ አዲስ ሹመት፤ አዲስ ኦሮማራ ፎረም፤ አዲስ ቡርቃ አዲስ የቻይና ዕዳ ስርዛ ወዘተ ወዘተበዚህ ማህል አብሪው ደግሞ ኦሮማራ እያለ ሲያደናግር ሰነባብቶ ሲሳከለት ስለቻይናው ጉዞ ደግሞከዚህ አዳናችሁ ነው ነገርዬው

https://www.satenaw.com/amharic/archives/66927
የቻይና ጅብክፍል 2 በብድር ያነክሳል! በዕዳ ጫና ይነክሳል!
በወታደር ይጨርሳል! (ስዩም ተሾመ)
April 24, 2019

እራሱ ስለ አኖሌ በአንድም በሌላም የምንሰማው መንፈስን ጠንከር አድርጎ ነፃ መሬት ተስጥቶት አንዲዘርፍ፤ እንዲገድል፤ እንዲወር የሚያደርገውን የኦነግ አጀንዳ አለባሶ ለመስራት አጀንዳ አኖሌ ሆና መጣች። ያቅድሉ እኛ በዛ 
ስንደናበር እነሱ የልባቸውን ይሰራሉ …  

የሆነ ሆኖ አዬር ላይ እንጂ ከሚዲያ በስተቀር አቅም ያለው የተደራጀ ሞጋችፕሮግራም፤ ሞጋች ደንብ፤ አጥቂ ፖሊሲ ያለው ሃይል ያ አለመኖሩን የምናውቅ፤ የተረዳን ሰዎች ነበር ቀድመን ያን የጥገናዊ ለውጥ መንፈስ ደግፈን የቆምነው እስከ የመንፈስ ኩዴታው የሀምሌው ዝምታ ድረስ። ልጅ የያዘውን ይዞ ስለሆነ የሚያለቅሰው፤  አቅም ያለው እኮ ደጅ የሚያስጠና ምንም ነገር የለም። ለአቅሙ ነው ደጅ ጥናት የሚደረግለት የነበረው። 

አሁን ኦዴፓ ለኦነግ እዬሠራ ያለው አቅም እዬመገበ ነው የመከላከል ብቻ ሳይሆን የማጥቃት አቅሙን እዬገነባ ነው ያለው፤ በተበተነ ሁኔታ የነበረውን ቄሮም መንግሥታዊ አቅም ኖሮት በእሱ ፈቃድ የኢትዮጵያ ነፍስ ተንጠልጥላ ኤሉሄ ኤሉሄ እንድትል እያስደረገ ነው። እና አቅም በእጅ ቢኖረን ይህ ይሆን ነበርን? 

ራሱ የአቶ የሺዋሱ ሰማያዊ ፓርቲ እኮ እዬለ ከእነነፍሱ ነበር ፈርሻለሁ ብሎ ያወጀው። … የሚገርም ድራማ እኮ ነው። ተፎካካሪ ነህ ስትባል ፈርሻለሁኝ?!እጅግ የሚሰቀጥጥ ነገር ነው የተፈጠረው፤ ግንቦት 7 የራሱ ላይበቃው ሌላውንም መንፈስ ነው ያስደረመሰው

አሁን እኮ ግለሰቦች እንጂ የድርጅት ህልው የሆነ የለም። ለግለሰቦችም ሹመት ተሰጥቷል። በዚያ ኒሻን ላይና ታች ይላሉ ለነገሩ የወሰን፤ የእርቅ የተባሉ ኮሚሽኖች ነፍሳቸው አለን? ፌክ የዘነበጣ ምድር ሆነች ኢትዮጵያ … 

እዛው አንደፍጥርጥሩ ቢሆን ደግሞ ምን ነበር? ስልበቱ ውጭ አገርም መሻገሩ ነው መከራው፤ ችግሩ ያን ጊዜ አውራ ሆኖ ሁሉንም ሚዲያ የተቆጣጠረው መንፈስ ግንቦት 7 አሁን ትጥቁን ስለፈታ የግድ የተቆጣጠራቸውን ሚዲያዎች፤ ነፍሶች ሁሉ ጨምሮ ማስገበር ግድ ይለዋል። ግንቦት 7 ሃሳብ ቢኖረው ለትውስት ለዛውም ለውራጅ ሃሳብ እንዲህ ቁምጥ የሚልበት ነገር ባልኖረ ነበር። ያለው አለውና።

የሚገርመው አቅም የለሹ ግንቦት 7 ገና በማቆጥቆጥ ላይ ያሉ አቅሞችን ሰብሮ እንደሱ ድራሻቸው ጠፍቶ ወይንም አንቀላፍተው እንዲገኙ አሁንም ካለፈው ሳይማር መትጋቱ ነው።

የባልደራስ ንቅናቄ ቢከስምለት ይወዳል፤ አብንም ቢናድለት ይሻል። እሱ እንዳይሳጣ፤ ከቻለም ማህል ገብቶ ተርትሮ እንደ ሰማያዊ ጣረሞትን ያስታቅፈዋል። ስንት አንበሳ  ነፍሶችን ጨምሮ ለሽ እንዳደረጋቸው እያዬን ነው …

የሆነ ሆኖ ሁሉም ለሽ ባለበት ወቅት ጧፍ ሆኖ መውጣት መታደል ነው። የታገልነው ህወሃትን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን ለተሟላ የዴሞክራሲ ሥርዓት ነው። ሥርዓት ከተዘረጋ አገር የግል ኢጎ ቁልል የመናህሪያ መርከብ አትሆንም። 

ስለዚህም ትናንትም ልብ እንዲገጠምልን ያልፈቀድን ነፍሶች እስከእልፈታችን ድረስ እውነት እውነት ሆኖ ለድል እስኪበቃ ድረስ እንታገላለን። እነሱም ወደ እውነት ይመጡ ዘንድ ነው እምንተጋው።

የህወሃቱ ኦህዴድ/ የኦነጉ ኦዴፓ እውነት ቢሆን ኖሮ ለእኛ እውነት እንጂ ሌላ መመዘኛ የለንም። አልነበረንም። ይህንንም አለም ጉድ እስኪል ድረስ አሳይተናል። በእነሱ እንጂ በእኛ ክህደት አልተፈጸመም። ተፈጥሯዊ እና ሰዋዊ ይሆናሉ በሚልም ነበር ያን ያህል እኔ እራሴ የተጋሁላቸው። ህሊና ያለው ሰው፤ ያለተደገመበት ሰው፤ ዓይነ ጥላ ያልዞረበት ሰው ገበርዲን ከረባት አይደለም ምርጫው ተፈጥሯዊ እውነትን ነበር የሻትነው።

ወደፊት መከራ በጅምላ ይጠብቃል … ከመከራም የከፋ መከራ … ቀድሞ ነገር ስለሚሆነው ነገር እኮ ባለቤትም ተጠያቂም እኮ የለም … ትበደላለህ፤ በደልህን  እንደ ጸጋ ተቀብለህ ትንፍሽ ሳትል ትቀጥላለህ ይህ የኦነጉ ባለድል ሞቶ ነው …

ስለሆነም ነፍስ ላለን ሰዎች ለኦነግ ካድሬ የምንሆንበት ግዴታ የለብንም። በዚህ አጋጣሚ ጋዜጠኛ ወ/ት ርዕዮት አለሙን ውስጧን የበለጠ በቀደመው አቅሟ ልክ እንዳዬው ላደረገኝ ለጋዜጠኛ ቴወድሮስ ጸጋዬ፤ ለአቤቱ ጊዜም፤ ለሷም ግልጽነት  ከዕድሜዋ በላይ ለሆነው ቁጥብነቷ ከልብ የሆነ ምስጋና አቀርብላቸዋለሁኝ።

እሱም ይባረክ እሷም  ትባረክ፤ እመቤቴ በዚህ ክፉ ቀን ከአላዛሯ ኢትዮጵያ ጎን በመቆምሽ አመሰግንሽአለሁኝ። አሁን ትግሎ ሰው አልገባውም እንጂ የኢትዮጵያ የህልውና ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያ ህልውናዋ አደጋ ላይ ነው። ኢትዮጵያን ቅኝ ለማድረግ ዘመናትን ሲቆጥሩ የነበሩ ጥቁር ነፍሶች የድል መባቻ ላይ ናቸው። የቤርሙዳ ትርያንግል ነገር ገና ነው ምን ተይዞ ... 

ያልተሽመደመደ ብረት መዝጊያ የለም … እጁን ያልሰጠም የለም። ነገ ጸጸቱን ከቻለው፤ 
ነገ ደግሞ ሾጉጡኝ ብሎ ምልስት ወደ ዲያስፖራው ካላደረገ፤ ለዛውም መውጫ ከተገኜ ለቃቂም ከተገኜ ነው .. ከቁም እስር መፈታት ከተቻለ … እግዜር ያሰፈታችሁ ብለናል እኛም ተዚህ ተጭመተኛዋ ዝምተኛ ሲዊዝሻ፤፡

„ለአገር ደህንነት ስጋት“ ስለተባለው ስለቃለ ምልልሱ ግን ሙሉው እስካልወጣ ድረስ የትኛው ትክክል ስለመሆኑ ስለማላውቅ ዝምታን መርጫለሁ ግን የጉለሌው መንግሥት ያላሰጋ የዲሲው ቃለ ምልልስ ብዙም እንደማያሰጋ ግን አስባለሁኝ።

አዲስ አበባ ላይ ኩዴታ ቢኖር ሠራዊታችን ልናሰልፍ ነበር የተባሉትን ቡድኖች የባልደራስ ንቅናቄ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲታገድ ሳያፍር ሳይቀፈውም የጠ/ሚር ፕሬስ ሴክረታርያት ቢሮ ስለደህንነታቸው መረጃ ደርሶን ያለበት የውርዴት ማቅ፤ ከዛም በመቀጠል ይሄው የባልደራስ ንቅናቄ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ በይፋ በአዲስ አባባ ከተማ ላይ የታገደበት፤ በስሜን ሽዋ በነበረው ወረራ በሙሉ ሎጅስቲክ በተደገፈ ሁኔታ ዜጎች አብያተ ቤተክርስትያናት ያን ሁሉ ፍዳ ሲከፍሉ እሱ አያሰጋም ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ?  

ግን የሰው ሁሉ ህሊና ከቶ የት ተሰደደ ይሆን? ምኑ አዚም መጠባን …? በዚህ ሲገርመኝ ከኢሳት በፊት የተደራጀው አባይ ሚዲያ ከባልደረስ አንድ ነፍስ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ደግሞ ቡጢ ነበር። 

ቃለ ምልልስ አድራጊው አይታይም፤ ምን አስፈራው? ስሙም አልተገለጠም፤ ልክ አንድ አፍታ ጦማሪ አቶ ስዮም ተሾመ ወይንም ኤልቲቢ የልዕልት ቤቲ ቃለ ምልልስ ይመስላል … ግን ኢትዮጵያ ፋስ ወይንስ መዶሻ አምራች ሆነች ወይ ያሰኛል … የውነት ወደዬት እዬሄድን ነው …

Ethiopia -/ አብይ አሸጋጋሪ አይደለም | አቶ ስንታየሁ ቸኮል

Published on Apr 23, 2019

·       በዚህ ማህል

ሁለቱም ጉዳይ በጣምራ መንፈሴን ሲሰንገው፤ የርዮት ቃለ ምልልስ እና የአባይ ሚዲያ ቃለ ምልልስ ነገሩ ስላስደነገጠኝ ኢትዮጵያ ከርነት አፊርስ ወጀቡ ነክቶት ከሆነ ብዬ እዛ ስገባ ግን አልነካካውም … አርኬብን ሁሉ ፈታተሽኩት፤ የአፈናው አውሎ ድርሽ አላለበትም። እናም ወንዳታ የድሮ ቤቴ አልኩኝ እና ኩራት ኩራት አለኝ … ይህም ተመስገን ነው።

ብዙ ሰው ኢሳት ከመጣ በኋዋላ ሚዲያዎች እንደተጀመሩ ይናገራሉ፤ ለኢሳት
 መፈጠርማ የቀደሙት ነበሩ እርሾው። ECDF የቀደመ ነው። የራሱ ራዲዮ ፕሮግራም ሁሉ ነበረው „አደራ“ የሚባል፤ ኢትዮጵያ ይሰማ ነበር። ራሱ ግንቦት 7 ከዚህ ሚዲያ በኋዋላ ነው የተፈጠረው የጋዜጠኛ አበበ በለው አዲስ ድምጽም ከሁሉም የቀደመ ነው፤ አባይ ሚዲያ፤ ኢትዮዛሬ፤ ኢትዮሚዲያ፤ ቋጠሮ፤ ዋርካ፤ ጸጋዬ ድህረ ገጽ እና ራዲዮ፤ ሲዊዲን
ራዲዮ የቀደሙ ናቸው ከኢሳት ከራሱ በጣም የቀደሙ። 

የሲዊድን የነበረው ከላይ ከገለጽኳቸውም በፊት በ90ዎቹ መጨረሻ ሁሉ ህልው የሆነ ነው። አዘጋጁ ጋዜጠኛ አለም ይባል ነበር፤ ዛሬ ይኑር አይኑር አላውቅም … ያው በገለጽኩት መስክ ግንቦት 7 አውራ ነኝ አለና የጠቀለለውን ጠቀለለ፤ መጠቅለል ያልቻለውን የሚከሰመውን አክስሞ አሻም ያሉትን ደግሞ አክስቶ በዘነዘናቸው አስኬዳቸው።

አሁን እሱ ሙሉ ለሙሉ ትጥቁን ሲያስረክብ ፈተናው ውረስ እና ቅርስ ያደረጋቸ ሁሉንም ሆኖ አረፈው>> ይህ ጅማሬ ነው ቀጣዩ መፋለጥ ይቀጥላል …አሁን የተደመረና ያልተደመረ በሚል ይሆናል፤ የቀደመው አሻም የሚለው ወያኔ ይባል ነበር። የአሁኑ ደግሞ ሰልጠን ባለ ሁኔታ የተደመረ ያልተደመረ …

ሳይደመሩ መደገፍ አይፈቀድም፤ ተደምሮም መተቸት አይፈቀደም። ግንቦት 7 አባል ሳይሆኑ መደገፍም መቃወምም እንደማይቻለው ማለት ነው። አጣብቅኙ የዴሞክራሲ መንፈስ እንጦርጦስ ስለመላኩ መርዶ ይልካል …

የአሁኑ ፈተና ከቀደመው በብዙ እጥፍ ይበልጣል። እንዲያውም እኔ ሳስበው 27 ዓመቱን ሙሉውን አልታገልነም ብል ይሻለኛል። የፊት ለፊቱ መራራነቱ በደህንነት ከሰለጠነ መንፈስ ጋር ስለሆነ ተጋድሎው፤ ከዛ በላይ በውስጡ አዲስ አገር የመፍጠርም መንፈስ ስላለበት መንትዮሹን በወጥ ለመግራት ካለው እሳቤ ጋር ብስጭቱም ንዴቱም ታክሎ መከራው ፍዳው በረዱ እምታ ነው።

አሁን ጎሽቶ ገና ስላልጠራ፤ የሃይል አሰላለፉ ዝንቅ ስለሆነ እጅግ ከባድ ነው። ጊዜውም ልጅ በመሆኑ የገመናዎችን ጫፍ እንጂ ገና ሆድዕቃው አልተገኘም። ልክ ህወሃት ወደ ስልጣን ሲመጣ አገር ምድሩ ሁሉ ብሥራትን አሰቦ ነበር።

ያን ጊዜ በጦብያ መጽሄት እና ጋዜጣ ብዙ ተተግቷል፤ ኢትዮጵስ፤ ሙዳይ፤ አፍሪካ ቀንድ ጀማምረውት ነበር ግን ሰሚ አልነበረም ወገብ ድረስ አተላው ሲውጥ ተነቃ አቅሙን አጠናክሮ ስለነበረ ህወሃት እንሆ 27 ዓመት ቅጥቅጥ አድርጎ ገዛ …

አሁንም ንቃቱ የሚመጣው ባነሰ ግምት ከ10 ዓመት በኋዋላ ይሆናል። የ100 ቀኑ መንፈስ መጠለፉን በለብታ እንኳን ሊሂቃኑ አልገባቸውም … ቢሆንማ እኔ እራሴ የተጋሁበት አለነበረም ወይ? ግን ሁኔታው ተገልብጦ ኦነግ ነው አሁን ያለው።

ህወሃት ሥልጣን በያዘበት ዘመን እንዳለው መንፈስ ነው አሁን ያለው። መከላከያው የኦነግ የኢትዮጵያን እስኪያክል ድረስ ሙሉ ድጋፍ ይደረግለታል። ከዛ አላዛሯ ኢትዮጵያ እና መንፈሷ ሰጥ ለጥ ብለው ይገዛል … የብአዴን ማሸብሸብ ቀኑ እስኪያልቅ ድረስ ነው … እልልታው ለሥርዓተ ቀብር መሰናዶ ነው። 

ከዛ ለፈቀደው ሎሌነት ካዝና ውስጥ ከነሥያሜው ይዶላል … አማራና ኦነግ?የበታችነቱ እኮ እዬገረሸበት ነው ወጣ ገባ እያለ ሰቅጣጭ እወጃውን የሚያስነካው፤ የጠቀለለ ዕለት ዘመነ ጉዲትን፤ ዘመነ ግራኝ ምስጋን ይነሳው ይሆናል … 

አሁን ባላሰቡት ወቅት ስለፈነዳባቸው ነው ቀዳዳ በመወታታፍ ላይ የሚገኙት … እንጂ ሩቅ ትልም ይዘው ነው የተነሱት፤ አፍሪካም እራሷ … ወዮልሽ ነው። በቃኝ የለም … ለማይበቃው እናብቃው ነው አሁን ተጋድሎው … ይህ በውነቱ የሃሳብ ሬሳነት ነው …

አይ ለፌክ! አሻም ለፌክ! እንብኝ ለፌክ ማለት ሰውነት ነው።

ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

እህት ርዕዮት ከ አላዛሯ ኢትዮጵያ ጎን መቆም ያስመሰግናል! ምርቃት!

 እንኳን ደህና መጡልኝ  ከአላዛሯ ኢትዮጵያ ጎን መቆም ያስመሰግናል። ምርቃት ። „ ሳቅን   እብድ   ነህ፤   ደስታንም፤ ---  ምን   ታደርጋለህ ?  አልኩት። “   መጽሐፈ   መክብብ...