#ለመክሰስ ያልበቃን፤ ይህ ተይዞ ነው #ስንካሰስ ውለን የምናድረው። ቤታቸውን እስኪ #ከውስጡ ሆነን እንየው። ሰውኛነት ከእኛ ጋር ከሆነ።
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ምዕራፍ ፲፰።

"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ምዕራፍ ፲፰።
ቀና ብሎ ለመሄድስ ያስችለን ይሆን??
አደጋው ብቻ አይደለም። #መኖራቸው ብዙ ይናገራል። የለበሱት፤ የቤታቸው ሁኔታ ይናገራል።
ይህ #የጋሞ ብቻ አይደለም። የአገሬ ገበሬ፤ በትናንሽ የገጠር ከተማ የሚኖረው ወገናችን ዕለታዊ፤ ዓመታዊው ኑሮው ይኽው እያዬነው ነው። በየሰልፋ፤ በየስብሰባው የማየው የመኖሩን ደረጃ የሚያመሳጥርው ይህንኑ ነው። ካነሳሁት ላይ የአደጉበትን ባህል እና ወግ በመፍራት ያልፋልን እየጠበቁ ሊለምኑ ያፈሩ ወገኖች አሉን። ባሊህ ባይ የሌላቸው።
#ምን መደረግ አለበት?
#ውስጣቸውን በአትኩሮት እንይ። ኑሯቸው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ? ሊቅነቱ የዚህን ማህበረሰብ ህይወት በተጨባጭ ካለወጠ፤ መማሩ ለማን? መማሩስ ለምን??? ነገ ሲመጣስ እንዴት ይሆን ይሆን? የሚለውን ከመለሰ ይሆናል። እኛ እና እኛ ተሸዋውደን እስከ መቼ???
ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት አደጋው ብቻ አይደለም እኛን የሚያሳይ ራዲዮሎጂው ከናዳው በፊት የተረፋት የሚኖርበት ህይወት ነው። እሱ ብዙ፤ በጣም ብዙ ያመሳጥራል። እኛን ማየት #የእኔ ብሎ ሊሆን ይገባል። ለነገሩ "እኛ" የሚባል ቃል መስማት የማይፈልግ ተቋም እንዳለም አንድ የወጣቶች ቃለ - ምልልስ ላይ አዳምጫለሁኝ። የእርግማናችን ልክንም አይቸበታለሁኝ። "እኛ" ተፈርቶ አገር፤ ሉዓላዊነት፤ ሰዋዊነት ተፈጥሯዊነት እንዴት ይታሰብ? "ሀ" ሳይባል መቼስ "አቡጊዳ" አይባል ነገር።
እህ። ለምን?
የትኛው ---------#ይቀድማል?
የቅደም ተከተል ችግር አለብን። አጀንዳ #ከመምረጥ ጀምሮ።
አንዱ ይህን አለ፤ ሌላው ይህን አለ፤ የመልስ መልስ ጊዜን ያስቸግረዋል።
ተማርክ - አልተማርክ፤ አወክ - አላወቅህ ይህን ዕንባ የእኔ ካላልክ ማን ነኝ? ምንስ ነኝ ባትል መከራውን ብታገል፤ እኮ የላይኛው ይፈትሻል። ይህን ሰቆቃ ቸል ብሎ፤ በዕንባ ውስጥ ተመስጥሮ ያለው #የድህነት ልክ፤ ይህ አደጋ ከመድረሱ በፊት #እራት ሳይበሉ፤ ምሳ ሳያገኙ፤ ቁርስም ሳይቀምሱ፤ ይህ መደበኛ ኑሮ ቀርቶባቸው ለለት የጉሮሮ ማርጠቢያ ሳያገኙ ሰማዕት የሆኑ፤ እስካሁንም በጭቃ ውስጥ ያልተገኙ ስንት እኛወች ይኖሩን ይሆን???? እስከ መጨረሻው የትንፋሽ ስንብትስ በምን ሁኔታ መራራ ስንብቱ ተከወነ ይሆን? ይህ ጭንቅ እራሳችን እኛኑይሞግተን ዘንድ እንፍቀድለት። መዳኛችን በዚህ ዕውነት ውስጥ ተጋርዶ አለና።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/03/026
ጌታ ሆይ! ቋሚ ምህረትህን ላክ። አሜን
አማኑኤል አባቴ ሆይ! ለእኛም ፖለቲካዊ ልብ ሳይሆን #ሰውኛ ልብ ስጠን። አሜን።
የሃዘን ዳርቻ ይሁን። አሜን።
ለንጹኃን ሁሉ መጽናናትን ይስጥ ፈጣሪ። አሜን።

የከረባት፤ የገበርዲን፤ የሽብሽቦ፤ የሚኒ፤ የኩላኩል፤ የልብስ ፋሽን፤ የስታይሊንግ ዓይነታችን እና #ዕውነቱ #ገብያ ላይ ሲሆን እኛ ይህን ኑሮ እንመስላለን። ቢቀድም የውስጣችን መጎሳቆል፤ እኛን እና እኛን የሚያፎካክር፤ የሚያቧክሰን፤ ፊት የሚያዞር፤ ከመቃብርህ፤ ከመቃብሬ የሚያስብለን ምንም ፋክት፤ ምንም ዕውነት ባልኖረ ነበር። ከዚህ በላይ የእኛነት ገላጭ ራዲዮሎጂ የለምና።
ልብ እያለን በልባችን ላይ #ሸፍተን፤ ማስተዋል ተሰጥቶን በቅጽበታዊነት ስንካሰስ ዘመኑ እንሆ የተደከመበት፤ የተለፋበት በግልም በጋራም የተለፋበት፤ ሳያፈራ፤ ወቅታት #ዕንቡጣቸው ጠውልጎ፤ ወራት ቡቃያውን #ማስቻል አቅቷቸው፤ በሳምንታት ዘሩ #ለችግኝ ሳይደርስ እዛው መክኖ ይቀራል። ያፈሰስነው - ጉልበት፤ የምንጋጭበት ወዘተረፈ ገመና፤ በከንቱ የባከነው አቅም፤ ወጣትነታችን ተምሎበት መኖ የቀረበት ዕውነቱ ይህ ነው፤ በምስሉ የምታዩት።
ይህ #የጋሞ ብቻ አይደለም። የአገሬ ገበሬ፤ በትናንሽ የገጠር ከተማ የሚኖረው ወገናችን ዕለታዊ፤ ዓመታዊው ኑሮው ይኽው እያዬነው ነው። በየሰልፋ፤ በየስብሰባው የማየው የመኖሩን ደረጃ የሚያመሳጥርው ይህንኑ ነው። ካነሳሁት ላይ የአደጉበትን ባህል እና ወግ በመፍራት ያልፋልን እየጠበቁ ሊለምኑ ያፈሩ ወገኖች አሉን። ባሊህ ባይ የሌላቸው።
#ምን መደረግ አለበት?
ሽሽቱን ትተን ዕውነቱን #መጋፈጥ። መካሰሱ ቆሞ ይህን አሳዛኝ የህዝባችን ህይወትን ለመለወጥ ርህርህና፤ አዝኝነት፤ አጽናኝነት ጥቁር ለብሶ፤ ጥቁር ቀኑ አልፎ ብርሃን ለሚወጣበት ዕለት ቅንነትን ለመመገብ፤ መወሰን። #መሆንም።
#ውስጣቸውን በአትኩሮት እንይ። ኑሯቸው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ? ሊቅነቱ የዚህን ማህበረሰብ ህይወት በተጨባጭ ካለወጠ፤ መማሩ ለማን? መማሩስ ለምን??? ነገ ሲመጣስ እንዴት ይሆን ይሆን? የሚለውን ከመለሰ ይሆናል። እኛ እና እኛ ተሸዋውደን እስከ መቼ???
ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት አደጋው ብቻ አይደለም እኛን የሚያሳይ ራዲዮሎጂው ከናዳው በፊት የተረፋት የሚኖርበት ህይወት ነው። እሱ ብዙ፤ በጣም ብዙ ያመሳጥራል። እኛን ማየት #የእኔ ብሎ ሊሆን ይገባል። ለነገሩ "እኛ" የሚባል ቃል መስማት የማይፈልግ ተቋም እንዳለም አንድ የወጣቶች ቃለ - ምልልስ ላይ አዳምጫለሁኝ። የእርግማናችን ልክንም አይቸበታለሁኝ። "እኛ" ተፈርቶ አገር፤ ሉዓላዊነት፤ ሰዋዊነት ተፈጥሯዊነት እንዴት ይታሰብ? "ሀ" ሳይባል መቼስ "አቡጊዳ" አይባል ነገር።
ተራርቆም #በቅርበት መተሳሰብ ይቻላል። ተቀራርቦም እንዲህ #መራራቅም አለ። ይህን እንቆቅልሽ በብልህነት የመፍታት ቁርጠኝነት ይጠይቃል፤ የፈላስፊት ኢትዮጵያ በኽረ አጀንዳ ውስጥ በቤተኝነት በቤታችን እያንዳንዳችን በግል፤ ሁላችንም በጋራ ለመገኘት። ይህ ልካችን ያጋለጠ ገመና እያለ እኛ ሌላ የማዶ ለማዶ ነገር ያሰኜናል። ለምን?
እህ። ለምን?
የትኛው ---------#ይቀድማል?
የቅደም ተከተል ችግር አለብን። አጀንዳ #ከመምረጥ ጀምሮ።
አንዱ ይህን አለ፤ ሌላው ይህን አለ፤ የመልስ መልስ ጊዜን ያስቸግረዋል።
ተማርክ - አልተማርክ፤ አወክ - አላወቅህ ይህን ዕንባ የእኔ ካላልክ ማን ነኝ? ምንስ ነኝ ባትል መከራውን ብታገል፤ እኮ የላይኛው ይፈትሻል። ይህን ሰቆቃ ቸል ብሎ፤ በዕንባ ውስጥ ተመስጥሮ ያለው #የድህነት ልክ፤ ይህ አደጋ ከመድረሱ በፊት #እራት ሳይበሉ፤ ምሳ ሳያገኙ፤ ቁርስም ሳይቀምሱ፤ ይህ መደበኛ ኑሮ ቀርቶባቸው ለለት የጉሮሮ ማርጠቢያ ሳያገኙ ሰማዕት የሆኑ፤ እስካሁንም በጭቃ ውስጥ ያልተገኙ ስንት እኛወች ይኖሩን ይሆን???? እስከ መጨረሻው የትንፋሽ ስንብትስ በምን ሁኔታ መራራ ስንብቱ ተከወነ ይሆን? ይህ ጭንቅ እራሳችን እኛኑይሞግተን ዘንድ እንፍቀድለት። መዳኛችን በዚህ ዕውነት ውስጥ ተጋርዶ አለና።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/03/026
ጌታ ሆይ! ቋሚ ምህረትህን ላክ። አሜን
አማኑኤል አባቴ ሆይ! ለእኛም ፖለቲካዊ ልብ ሳይሆን #ሰውኛ ልብ ስጠን። አሜን።
የሃዘን ዳርቻ ይሁን። አሜን።
ለንጹኃን ሁሉ መጽናናትን ይስጥ ፈጣሪ። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ