የሚነግሩን ሳይሆን የማይነግሩንን የሚያደርጉት ጠሚ አብይ አህመድ። ዕውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሥልጣናቸውን ለማስከበር ዝግጁ ናቸውን?
የሚነግሩን ሳይሆን የማይነግሩንን የሚያደርጉት ጠሚ አብይ አህመድ። ዕውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሥልጣናቸውን ለማስከበር ዝግጁ ናቸውን? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት አደርን? እኔ ረጅም ጊዜዬ ነው በሳቸው ንግግር መነሻነት ሙግት ካቆምኩ። ዋነኛው ምክንያት ተደማሪወቻቸው በጽኑ እዬሞገቷቸው ስለሆነ እረፍት ቢጤ፤ ሁለተኛው ግን ጠሚ አብይ አህመድ አሊ የሚነግሩንን ሳይሆን #የማይነግሩንን ስለሚሠሩ አሳቻነታቸውን ስለማውቅ አዬር ላይ ለሚቀር ንግግር ጊዜም አቅም ማባከን አይገባም በሚል ነው። #ጦርነት እና አብይዝም። የሆነ ሆኖ የመተማውን ሰማዕት አጤ የኋንስን ዘለው አጤ ሚኒሊክን እና አጤ ቴወድሮስን አንስተዋል። ያ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ፍቅር ደፍተው እራሳቸው መሬት እዬደበደቡ ጦርነት አምጣልኝ "ጀግና" ተብዬ ልመስገን፤ ልሸለም፤ ልክበር ብለው በልቅ እና ባልተገራ ንግግር ከአለቆቻቸው ጋር እልህ ተጋብተው ነበር ጦርነት የጀመሩት። ከዛም በፊት ኮረና እንደመጣ ያልተመረመረ ወታደር በላስታ እና በጎንደር ልከው ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የቀደመ ጨካኝ ተግባር ፈጽመዋል። ያስቆመው የአክቲቢስት ሙሉነህ የኋንስ ፒቲሽን የማሰባሰብ የመሞገት ተግባር ነበር። የአቶ ጃዋር ከበባም ሌላው ሳይለንት ጦርነት ነበር፤ የአርቲስት ሃጫሉ ግድያም እንዲሁ፤ የአማራ ክልል ሊቃናትን #መተራም ቀውስን ከመናፈቅ የመጣ ክስተት ነው። በአባይ ግድብ የኮፒ ራይት ሽሚያ መሰናዶም ትጉሁን ኢንጂነር ስመኜውን መበቀል፤ ቀብሩበእገዳ መከወን። በ100 ቀኑ የትጋት ጉዟቸው እርገት አፋር ክልል ነበር። "ደርግ የወደቀው ሰው ስለፈጀ ነው ብለውን ነበር።" በወቅቱ በፋክትም ሞግቸወትነበር። በርስወ ዘመንስ አንዲት ቅንጣት ማዕልት ካለ ሰኔል ...