ኢትዮጵያ ያለችበትን የሲኦል ዘመን ያሳያል።
ጭንቅ ላይ ያለው አርቲስት ታሪኩ ኢትዮጵያ ያለችበትን የሲኦል ዘመን ያሳያል።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
መስቀል አደባባይ ተናገር ሲሉት አልገባንም። የገባን ቅኑ አማራ የሰጠውን ድጋፍ አንስቶ ከባህር የወጣ አሳ ሲሆን ነበር።
ዓለምን ያነጋገረው፣ የአለምን የጥበብ ዓውድ በአንድ መንፈስ የገራው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግሎባል ተደናቂነት ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ በምን አይነት ስልት ጭብጥ፣ ኩምትር እንዳደረጉት ዛሬ ጥዋት አዬሁት ሰይፋሻ ሾው ብድግ እና ዘጭ፣ ዘጭ እና ብድግ ትዕይንቱን።
ለጋው የጥበብ ሰው ቅባዕውን ትቶ ከቤቱ ይቀመጥ ዘንድ የታቀደው የኦነግ ግብ ተልዕኮውን ፈፅሟል።
እሳቸው ከመጡ ከቀደመው የተወጠነው ከእረኛዬ፣ የእግር እሳት በስተቀር አንድ የተሳካ የጥበብ ሁነት ኢትዮጵያ አላዬችም። ሥራወችን ስታዩ አዳዲሶችን ቅባዓ የበነነባቸው ነው። እንደ ሌላው ቦታ ተቸምችው ለዛ ቢስ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ጀምራችሁ አትጨርሱትም።
እንደ እንጨት የተገተረ ሸክም ይሆንባችኋል። ያ አልባብ ባልባብ የነበረው የጥበብ አውድ ሸሽቷል። ለነገሩ በደም ለተነከረ ዘመን።
ጥበብ የተቀበረበት ዘመን ላይ እንገኛል። ዋናው ዒላማው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰብዕና እንዳይፈጠር ነው። ሚስጢሩ ያ ነው። ሁለተኛው አናቱ ጉዳይ ዬኢትዮጵያ ክብር እና ሞገሷ በጥበብ ውስጥ ማዬት ለኦነግ #ጣሩ ስለሆነም ነው። ሚስጢረ ኢትዮጵያ፣ ዓዕማደ ኢትዮጵያ ኦነግን ያጣጥረዋል።
ሌላው የህዝብ መንፈስ ተረጋግቶ መኖሩም አይፈቀድም። ሁልጊዜ በሰበር መሰባበር አለበት እና።
ያልንኮተ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ያለ እንዳይመስላችሁ። ሰቅስቀው በአፍ ጢሙ ደፍተውታል። ለዚህ ነው አሳቻው መሪ። አሳቸው ዘመን የምለው።
በጥንቃቄ ዘመኑን ቁጭ ብሎ ማጥናት፣ ቁጭ ብሎ ማንበብ፣ ቢያንስ እራስን ካልሆነ ጉድጓድ ቀርቅሮ ከውጪ ገቢ ነፍስ ይታደጋል። ዘመኑ እራሱ ጨምታችሁ እዩኝ፣ አደብ ገዝታችሁ አስተውሉኝ እያለ ነው።
ቃለ ምልልሱ፣ አቀማመጡ፣ መሰበሩ፣ የኢትዮጵያ ዜግነት ቀራኒወነትን ያሳያል። የተናገራቸው ኃይለ ቃል፣ ያስተላለፈው መልዕክትይፈትሻል።
እኔ ከአለው፣ ከደመቀለት፣ ከሞላለት ጋር አልገኝም። እንዲህ ጭብጥ ኩምትርትር ካለ መንፈስ ጋር ግን ነኝ።
ለለጋ የጥበብ ሰው አማካሪ ያስፈልገዋል። ለዛውም በኦነግ ፖለቲካ ከእነሱ ያልተገኘ ነፍስ በፈጣሪ ታምር የሚሊዮን ሉላዊ ህዝብ መንፈስን ሲገዛ ማዬት የሚታመሙበት ገመናቸው ነው።
ተስፋ አትቁረጥ። ይህም ለበጎ ነው። ፈጣሪ ተቋም ከፍቶልኃል። ስለዚህ ፈተናው #ፍሰኃህ ሊሆን ይገባል። በሆነ ባልሆነ የማይሞቁ፣ የማይቀዘቅዙ ወገኖች እንዳሉህ እሰብ።
ከአለ አንድ ሰው አጽናኝ እና እረዳት። በርታልን ወንድም አለም። በመንፈስ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ። ሥራወችህን በሚዲዬዬ እጠቀምበታለሁ። የክፋወች ሴራ አያሸንፈኝምና። ፍቅር ምኑ ይጠላል? የምተጋበትም ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/05/2022
ኪነ ጥበብ ዳኛዋ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ኪነ ጥበብ ተስፋዋ አምላኳ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ