ለሴቶች ታስሮ መፈታት አዲስ ምዕራፍ ነው።
ለሴቶች ታስሮ መፈታት አዲስ ምዕራፍ ነው።
ለሴት ልጅ እስር ከባዱ መርጉ የህይወት ፈተና ነው። መአዚ እንደታሠረች ሰማሁኝ። ድንግል ትርዳት። አሜን።
በእሷ ዙሪያ ያልገባሁበት ቤት አልነበረም። የእናቷ ልጅ እንኳን የእኔን ያህል ትደክማለች ብዬ አላስብም። አንድ ወዳጄ እያወያዬኝ መጸሐፋን ፃፍሽላት ያለኝን አስታውሳለሁኝ።
የሌላ አገር ዜጎችም በእሷ የተግባር ማሳ ምሰጣቸው ልዩ ነበር። ባለሥልጣኖችም ሲፈቷት አክብረው ነበር የፈቷት።
እንደ እሷ ታሥሮ እጅግ ተከብሮ ከእስር የተለቀቀ አልነበረም። ያ የብዙ ድካም ውጤት ነበር። ብዙ ያስከፋኝ ሰወች ይቅርታ ሁሉ ጠይቀውኛል። እሷ ተሸልማ ማዬት ሁሉ ምኞቴ ነበር።
በጣም በትጋት፣ በተከታታይነት 24 ሰዓት ደክሜያለሁኝ። የሚጎድልበት ማህበረሰብ። የሚጎድልበት ፕሮጀክትም ስለአለ። አንድ ብቻዋን አትታሰርም። ብዙ ተስፋወች ይታሰራሉ።
ወጣት አትሁኝ ማለት አልችልም። ወንጀል ነውና። ወጣት ሁኜ እያለሁ ነበር ጭምትነቴ፣ ቁጥብነቴ ተመዝኖ ወጣቶችን አደራጅ እንድሆን ያስደረገኝ። ስለዚህ የእኔ ብቻ የወጣትነት ዘመኔ ብቻም ሳይሆን የወጣቶችን ሥነ - ልቦና አውቀዋለሁ እና። አደራጃቸው ነበርኩ እና።
የሆነ ሆኖ ድካምን ዕውቅና፣ ድካምን አትኩሮት መስጠት ከአንድ ፕሮፌሽናል ፖለቲከኛ የሚጠበቅ ነው። ሲኖር ብዙ ይኮናል። ከታሰሩ ሁሉም ይከረቸማል።
ብዙ ነገር ይጎድልበታል። ብዙ በሮች ባለቤት ያጣሉ። ቢያንስ ያነን ማሰብ ይገባል። ድንግል ትርዳት። እግዚአብሔርም ያስፈታት። አሜን።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/05/2022
ርትህን ከእዮር።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ