የአማራ ዘመናት ጦርነት ተከፍቶባቸዋል። ፋኖ የአማራ የተፈጥሮ መከላከያ ኃይል ነው።

 No photo description available.

የአማራ ዘመናት ጦርነት ተከፍቶባቸዋል።
ፋኖ የአማራ የተፈጥሮ መከላከያ ኃይል ነው።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እንዴት ነን? እንዴት ይዞናል የጦርነት ውሎው?
የአማራ ልጅ ስለምን ተወለክክ ነው የኦነግ ጦርነት? እሱ በሰራት፣ ባበጃት፣ ባሳመራት አገር ለምን ተፈጥረህ ተገኜህ ነው።
ስለምን አገር እንዲህ በቻርተር የምንቀባረርበት ቤተ መንግሥት አደራጅተህ ጠበቅህ ነው ግብግቡ። አማራ ባይፈጠር ኢትዮጵያ ምን ትመስል ነበር? አማራ ባይኖር ዘመናቱ ምን ይሆኑ ነበር።
ከአማራ ጋር የቀደሙ ማህበረሰቦች አሉ። በአማራ ላይ ያለው ውርጅብኝ ግን መስፈሪያ የለውም። ይህ ሲሰላ የአማራ ሕዝብ ረቂቅ መንፈሳዊ ፀጋ አላኃዊ፣ እግዚአብሔራዊ መሆኑ በዝምታ በማሳልፋቸው ቀኖች ጠረጴዛዬ ላይ ቁጭ አድርጌ የማወያያቸው በትረ ጉዳዮች ናቸው።
አማራነት ንባቡ፣ ትርጉሙ፣ ሚስጢሩ ጊዜ ተሰጥቶ ሊጠና የሚገባው የዘመናችን ክስተት ነው። አማራነት ፊኖሚናል የመሆን አቅሙ ግርማ ሞገስ አግኝቷል።
የአቶ ጃዋር ቃለምልልስ ጭንቅ ጥብብ የሚለው የአማራ አቅም መጎልበት፣ መፋፋት፣ እንደ ችብኃ መለምለም ስቃዩ፣ ውጋቱ፣ ረፍት ያሳጣው ሆኗል። ጨምቶ ከርሞ የወጣበት ተልዕኮ መሳሪያውን ብታስፈቱት ህሊናውን ማስፈታት ትጥቅ ይከብዳል ይላል።
እሱ አያውቀውም። የአማራ ልጅ በሰላም ጊዜም፣ በጦርነት ጊዜም ምንጊዜም ህሊናው ትጥቅ ፈቶ እንደማያውቅ። የአማራ ልጅ ሲፈጠር ኃላፊነት ይዞ ይወለዳል። እራሱን፣ አካባቢውን ለመጠበቅ። ይህ አማራ ከተፈጠረበት ዘመን ጀምሮ ያለ፣ የነበረ ዕውነት ነው።
እኔ ግንቦት 5/ 2010 አብይ ሆይ እኔም ዜጋ ከሆንኩ ብዬ ከ20 ገፅ በላይ ስጽፍ የአማራን የመንፈስ፣ የአካል ትጥቅ ትውፊታዊ ስለሆነ እንዳይነካኩት በትህትና አስገንዝቤያለሁኝ።
ሌላም በዚህ ጭብጤ ላይ በእያንዳንዱ ቀበሌ ተከፋይ የመንግሥት ወታደር ማቆም ስለማይቻል ይህን የአማራ ትውፊት የመጠበቅ፣ የመንከባከብ ግዴታ እንዳለባቸው አስገንዝቤያለሁኝ።
ሱዳን እሳቸው ፈቅደው መሬቱን ባይሰጡት እስከዛሬ ተጠብቆ የሚኖረው በአማራ የተፈጥሮ የመከላከያ ኃይል በፋኖ ነው።
ይህ ለአቶ ጃዋር መሐመድ የፊደል ገበታው ሊሆን ይገባል። አያውቀነም እና። በተረፈ ከእስር ተፈቶ የቆዬበት የጥሞና ጊዜ እኔ ያደነቅኩለት ነው። ለኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እምመኜው በአክብሮትም ሳሳስብ የባጀሁት ጭብጥ ነው። ለማድመጥ ጊዜ መስጠት። እንኳንስ አንድ ዓመት ከሰባት ወር እኔ ትናንት አልገባሁም። ሚዲያ አልከፈትኩም። ብዙ ነገሮች አዲስ ናቸው። ረፈድ ብዬ የገባሁትም ምን እንዳለ ለማወቅ፣ ለማጥናት ነው።
ያልተና ጉዞ አደጋው የማህበረሰብ ነውና። ስለዚህ የዝምታ ጊዜውን የአቶ ጃዋር መሐመድ አክብሬዋለሁ። መለመድም ያለበት መልካም ተመክሮ ነው።
ያቀረባቸው ስልታዊ ጭብጦች ግን የአማራን ህዝብ ሰቆቃ የተጋራ አይደለም፣ እንዲያውም አፈፃፀሙ ጥበባዊ ይሆን ዘንድ፣ ተጨማሪ የብሬን ወሽ ፕሮጀክት ይከፈት ዘንድ በአጽህኖት ለኦነጋዊው መንግሥት የሚያሳስብ ነው።
የአማራ ክብር፣ ግርማ እና ሞገስ ያስደነገጠው ይመስለኛል። ጦርነቱ አማራን ሚሊተሪዝም ሲያደርግ ያን ሁሉ ማህበረ ኦነግ በሚሊዬነም አዳራሽ፣ በመስቀል አደባባይ ተሰብስቦ የሰበሩንን ሰብረን የአገሪቱን እርዕሰ መዲና ተቆጣጠርን ሲባል ምን ያህል የጆኖሳይድ ዓዋጅ እንደ ሆነ ሳይጠፋው ግን የጠፋው መስሎ ቀርቧል። "ከአማራ ጋር አትጋቡ፣ አትዋለዱ አትገበያዩም" አያስጨንቀውም።
በፈረቃ እዬመጡ ማዛል፣ አጀንዳ መሆን ዘመኑ እስካለ ሊቀጥል ይችላል። ሲደረመስ ግን ሁሉም አይሆኑ ይሆናል። ይህ ወጣት ዕውነቱን አንብቧል፣ ተርጉሟል፣ አመሳጥሯል። "እኔ የፋኖ ደጋፊ አይደለሁም። እኔ እራሴ ፋኖ ነኝ።" ለምን የደሙ ዓይነት ስለሆነ።
ይህ ማለት ግን ፋኖነት ሰላም ካለ ይኖራል ማለት አይደለም። ሰላሙን ሲያገኝ ሁሉም ስምሪቱ በመደበኛ የተመረቀበት፣ ወይ የኑሮው ዘይቤ በሆነው መንገድ ይቀጥላል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/05/2022
አማራነት ሰው ሰራሽ ማንነት አይደለም!
 
Akafawork Woubshet
"ዛሬም ሼር ሊደረግ የሚገባው ና ለሰው ሁሉ ሊዳረስ ጀሚገባው መልእክት ይመስለኛል ።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።