አማኑኤል አድርጎት ከሆነ እንኳን ደስ አለወት። #ይገባልም።
"የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
የማከብረወት ዶር ዳንኤል በቀለ እንዴት ሰነበቱ? አንድ #እሸት የሆነ የዕውቅና ዜና ሰማሁኝ። ዕውን ከሆነ ይገባል። የአውሮፓ ህብረት ለክብርነተወ ሰጠ የተባለው ዕውቅና ሰብዓዊነት በኢትዮጵ ያለበትን ሁኔታም ዕውቅና የሚሰጥ ስለሆነ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ብዬ አምናለሁኝ።
ከሁሉ በላይ በጽናት እርሰወን አምነን ሲከፋን እባከወት ይከታተሉት እያልን አቤት ለምንል ወገኖችም ከደስታ በላይ ሐሴት ነው ብዬ አምናለሁ። ደስታ ለምድራዊ ሲሆን ሐሤት ግን መንፈሳዊ ሁነትን ያካታል ብዬ አምናለሁ።
ኢትዮጵያ ላልከበደቻቸው ወገኖች በሚስጢሯ ልክ እስከሆኑ ድረስ እንዲህ ያለ ሞገስ፤ እንዲህ ያለ ማዕረግ እንዲህ ያለ ሽልማት ያስገኛል። ሆነም // አልሆነም #ሱናሜውን ታግሰው ከቲመወት ጋር በምታደርጉት ጥረት አለን የምንለው አኃቲ ተቋም መኖሩ በራሱ ልዩ በረከት ነው። የተቋማት ጥራት እና ቅልጥፍና ቢበራከት አያሌ ችግሮቻችን ይፈታሉ። ለትውልዱም ተስፋዊ ጉዞ ምቹ መደላድል ይገኛል።
በግዙፋ የኢትዮጵያ አሳቻ የፖለቲካ ተፈጥሮ ውስጥ ሳይታክቱ፤ ወጀቡን ታግሶ መዝለቅ በራሱ ለኃላፊነት እና ተጠያቂነት አዲስ መስመር ቀራጭ መሃንዲስ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። ለሚያደርጉት ትጋት እና ጽናታዊ ጉዞም እግዚአብሄር ይስጥልኝ እላለሁ። በእኔ በራሴ እና በ16 ዓመት በዘለቀው የፀጋዬ ራዲዮ ሥምም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
31/05/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ