ድካሙ ሳይሆን የሰለቸኝ #ህሊናችሁን አቃቂሩ ነው።

 

 
 No photo description available.No photo description available.
 
ድካሙ ሳይሆን የሰለቸኝ #ህሊናችሁን አቃቂሩ ነው።
ዝም ማለት ይቻላል። ሳልናገር፣ ሳላሳስብ የጎደለ ነገር የለምና። እኔን ማድመጥ ለተሳነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲከኛ በልኩ መቆጠብ በእጅ ያለ ነገር ነው። የትኛው መሃያዬ፣ የትኛው የምረዳው እንዳይቀር?
እኔ ዘመኔን በሙሉ በፖለቲካ ተግባር ነው የኖርኩት። ለዛውም እራሴን ጎድቼ። ከአለ አንድ አይዞሽ ባይ፣ ካለ ብጣቂ ምስጋና። እዬታገትኩኝ። ማዕቀብ እዬተጣለብኝ። እዬተሳደድኩኝ።
ፌስቡክ በምክንያት ነው የጀመርኩት። ልሰራበትም አልነበረም። እኔ የሦስት ዓመት ታጋይ አይደለሁም።
እኔ ግርባው ኢህአዴግም መስኪን ይጥራት፣ ፈቅዳ ትሂድ እሱ አልነበረም አመክንዮ። በዚህ ወጀብ ጊዜ ምን ልትሆን ባህርዳር ሄደች ነው ሃሳቤ። ከዛ በተረፈ ሠርታለች፣ ደክማለች ልትሸለም ሲገባ ስለምን ታሠረች ነው።
ለዚህ ነው የሄደችው፣ ለዛ ነው የሄደችው የእኔ ጉዳይ አይደለም። ሁሉን ሚዲያም አላዳምጥም። ጊዜውም የለም። እሱ ብቻ ሳይሆን እኔ በምመለከትበት አቅጣጫ አይደለም ሰው ያለው።
የሆነ ሆኖ የፖለቲካ ትግል ይቅርብኝ የምትሉት ብዙ ነገሮች አሉበት። እናቴ ትቅርብኝ ከማለት በላይ #መስዋዕትነት የለም። እኔ ሁሉ በወረፋ አገር ሲገባ ተጠይቄያለሁ። አልፈቀድኩትም።
"ሁሉ ተፈቅዶልኛል፣ ሁሉ ግን አይጠቅምም"
ጊዜን ማስተዋል ይጠይቃል። እሳት እዬነደደ ልቀቀል፣ የመጣ ይምጣ አይባልም። ለዛውም ትዳር፣ ልጆች ያሉት ሰው። መስኪ ጎጃም ባህርዳር በዚህ ጦርነት ለታወጀበት ጊዜ መሄዷን አልፈልገውም። እራስን ማዳን ይገባል።
ባትሄድ አያስሯትም፣ ያስሯታል አይደለም። ወጀብን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ይገባል። ጥበብ ይጠይቃል። መቅደም ይጠይቃል። ስልት ይጠይቃል። እለፈኝ ማለት ይጠይቃል።
መስኪን እግዚአብሔር አውጥቷታል ነው የምለው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነገር ብዙ ነው። አስምራ ሹምዬ ከደንቪደሎ አምልጣ የት እንደ አደረሷት አይታወቅም። የእሷ ህይወት ያልተገላገልኩት ጽንስ ነው። ዋቢ የላትም።
መመረዝም አለ። ህሊናን መሳት አለ። የሚወዱትን ማጣት አለ። አፋኞች ከቤት ከመጡ ምን ይደረጋል።
ግን እነሱ ወደ ከፈቱበት ጦርነት አብሬ ልማገድ ብልህነት አይደለም። የሰው ልጅ ስለምን ማስክ ይለብሳል? ስለምንስ የኮረና ክትባት ወሰደ? ስለምንስ እራሱን በኳራንቲ አገደ? ሞትን ፈርቶ አይደለንም?
አንዲት ዘለላ ሃሳብ አይቀርብም፣ ዕውቅናማ ከእኔ በስተቀር ማን ለማን ይሰጣል? እማልታዘብ ይመስላችኋልን? ሰው ሁሉ ቁጥብ ነው።
በሁለት ስንኝ መግለፅና ሌት እና ቀን ባዮግራፊ ለሌላ ሰብዕና መሥራት የሚከፈልበት እኮ ነው። ተከፍሎም የማይገኝ። መፀሐፍ ሲፃፍለት።
ፎሎው ማድረግ እኮ እኔን ብርቅ ነው። አይታሰብም። ከዚህ ተመጥቶ አይሉት ቅልጣን፣ አይሉት ዘመናይነት ልቤን ያፈሱታል።
ያ ፁሁፍ ለኦነጋዊው አንስቶች፣ ለኦነጋዊው ሥርዓትም ሞጋች ነው። የሚፈሩት ጭብጥ ነው የተነሳባቸው፣ ተደናግጠው የሚፈቱትም የማይቋቋሙት ሙግት ሲገጥማቸው ነው።
እኔ ድክም ብሎኛል። ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ። ስንት አቅም ፈሶ የተገኜ ዕድል የመንገድ ላይ አሽዋ ነው። ከምንም የማይቆጠር። እስር ቤት ለሴቶች 150% ከባድ ነው። የረቀቁ ፈተናወች አሉበት።
የቀራችሁት ዘለግ ብላችሁ የወጣችሁት የአማራ ልጆች በጥንቃቄ ተራመዱ። ታገሉ ግን ትግላችሁን ስሜት እንዳይመራው ጥንቃቄ አድርጉ። ዘመኑ ፈቃዱ ለማን እንደሆነ ዕወቁ። ስልተኛ ሁኑ።
የቤተሰብ መንገላታትን እሰቡት። በልጆች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖም ዕውቅና ስጡት። እባካችሁ።
የተደከመበት ዕድል ጥሩ ማኔጅመንት አጥቶ ከፈሰሰ ተጎጂው አፍሳሹ ይሆናል። አንድ ሰው ለሌላው ሲጮህ እባክህ ፈጣሪ ሆይ ስማኝም ብሎ ነው።
የማይጮኽላቸው ሚሊዮኖች እንዳሉም ማሰብ ይገባል። በጨካኞች መዳፍ ውስጥ ሲኮን ተስፋ የሚረው ተስፋ ያደረጉ ጎስቋሎችም ይሆናሉ።
ኢትዮጵያ በገዘፈ መከራ ውስጥ ናት። ይህን ሁሉ ተሸክሞ ለሌላው ድምጽ መሆን በእያንዳንዳችን ህይወት ላይ ሪሲክ ነው። በቤተሰቦቻችንም ላይ።
በመኖር ውስጥ በነፃ የሚሰጥ መገበር እራካሹ ይህን የተከተሉ የእኔ ቢጤ ጅሎች ተሳትፎ ነው። ግን ሁልጊዜ ሞኝነት አይቀጥልም።
ልጆች የማህበረሰቡ ናቸው። ስለ እነሱ ተስፋ ስለሚያገባኝ ነው እምደክመው። እናት እና ልጅ ሲለያይ ማህፀኔ ይቀረደዳል።
እናም ቅንነቴን ይለፍ እሰጠዋለሁ። ብወቀስበትም፣ ብነቀስበትም። የአማራ ልጆች፣ የአማራ ጉልቻወች፣ የአማራ ትውልድ ተሰቃይቷል።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/05/2022
ርትህን ከእዮር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።