#ጤና
የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ
-------------------------------------
በአሁኑ ሰዓት የኩላሊት ጠጠር በጣም በብዙዎች ዘንድ የሚከሰት ችግር ሆኗል፡፡ ጠጠሩ የሚፈጠረው በሚኒራሎች እና በአሲዳማ ጨው በኩላሊት ውስጥ ሲሆን የሚከማቸው በኩላሊት ውስጥ ወይም በላይኛው የሺንት ቧንቧ አልያም በሽንት ፊኛ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡
የሚፈጠሩት ጠጠሮች በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት ግን እዚያው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ እዚያው የሚቆዩ ጠጠሮች ካልተወገዱ፣ አንድ ላይ ትልቅ ጠጠር መፍጠራቸው
አይቀርም፡፡ ምናልባት የጎልፍ ኳስ ያክል መጠን ሊደርስም ይችላል፡፡ ይህም የሽንት ቧንቧን ሊዘጋ፣ በምንሸናበት ሰዓት ከፍተኛ ህመም ሊያስከትል፣
ማቅለሽለሽ፣ እንዲሁም ማስታዎክ ያስከትላል፡፡ እነዚህ ችግሮች ጠጠሩ አስካልተወገደ ድረስ ቀጣይነት ይኖራቸዋል እንጂ አይተውንም፡፡
የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የሚሆኑ ዘዴዎች
የኩላሊት ጠጠር ከሰውነታችን በተለያዩ መንገዶች ሊወገድ ይችላል፡፡ ይህም በጠጠሩ መጠን እና አይነት ይወሰናል፡፡ የኩላሊት ጠጠር በውስጣችን እንዳለ ካወቅን ስለሁኔታው የጤና ባለሙያ ማማከር የመጀመርያ ስራችን መሆን አለበት!!!
ዋናው ነገር ግን አስቀድሞ መከላከል ነው፡፡ ይሄም በቀላሉ ከቤት በምናዘጋጃቸው ነገሮች (home remedies) የኩላሊት ጠጠርን መጠን መቀነስ እና በሽንት አማካኝነት እንዲወገዱ ማድረግ ይቻላል፡፡
ከነዚህ home remedies መካከል በጣም የምታዎቀው የሚከተሉትን ነገሮች በመቀላቀል የሚገኝ ነው። እነርሱም፦
• 1 ብርጭቆ ንጽህ ሙቅ “ውሃ”
• 2 የሾርባ ማንኪያ “የአፕል ጭማቂ”
• 1 ወይም 2 የሾርባ ማንኪያ “ማር”
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ “ቀረፋ” ናቸው፡፡
አወሳሰድ
• “ለሁለት ሳምንታት” “ማታ” ከመተኛታችን በፊት መጠጣት፡፡
• እንደ ጠጠሩ መጠን በአስር ቀን ውስጥ ጥሩ ውጤት ማግኘት እንችላለን፡፡
ለሌሎች ማጋራት ደግነት ነው!!
ጤናዎ ይብዛለዎት!!!
ምንጭ :- Ethio Tena -ኢትዮ-ጤና
LIKE OUR PAGE
@NikahPage
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ