ድሮን ታቀደለት።

 

ይህ መኖር ተቀንቶበት ዲሽቃ ታዘዘበት፣ ድሮን ታቀደለት።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ዕንባቆም ፲፯ ቁጥር ፫)
 
 No photo description available.
ከ12 ዓመት በላይ የታገልኩበት መርህ ዓለም ዓቀፍ ይሁኑ ታላላቅ መንግሥታት ሥሜን የሚያውቁት ለድምጽ አልባ የኢትዮጵያ እናቶች ስጮህ ነው። ዛሬ ኦነግ እንዲህ ለሚንፈራሰስበት ሥልጣን በጣም የከበረ ተጋድሎ አድርጌበታለሁኝ። ተደማጭም ነበርኩኝ።
የማዝነው የአማራ እናቶች እኔም ሆንኩኝ ሌሎች እኔን መሰል በተለያዬ ትግል እና ስልት መስዋዕት የከፈሉ ወገኖቼ ጥረት ፈሶ መቅረቱ ነው።
ፈሶ መቅረቱ ብቻ አይደለም እኔን የሚያሳዝነኝ የአማራ እናት መከራ መቀጠሉ። ተገለውም፣ ተፈናቅለውም፣ በጎጃቸው ጥሬ ቆርጥመው ለማደር የልጆቻቸውም፣ የእነሱም ሰላም ከመሳሪያም ከባድ መሳሪያ ተደግኖ በባዕታቸው አሳራቸውን ያያሉ። ፍዳቸውን ይከፍላሉ።
የአማራ ሊሂቃን የተደመሩም ይሁን ያልተደመሩ ቢያንስ የአማራ እናቶችን ስቃይ ባያበራክቱ ጥሩ ነው።
ይህ ሁሉ መከራ የምትሸከም የአማራ እናት ናት። የአማራ እናት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ እናት የማትታይ፣ ዕውቅና የማይሰጣት፣ ሞት የታወጀባት፣ ሃዘንተኛ ትሆን ዘንድ በፖሊሲ የሚሰራበት ጉዳይ ነው።
እና ልጆቿን የዜግነት ፖለቲካ እያላችሁ 30 ዓመት ሙሉ አስፈጃችሁ። ቢያንስ አሁን ተዋት። እባካችሁ ተዋት። የአውሬው ጭካኔ ብቻ ሳይሆን ተስፋዋን የምትነጥቁት እናንተ መሆናችሁንም ዕወቁት።
የማን ልጅ ተገደለ?
የማን ልጅ ታሠረ?
የማን ልጅ ታገተ?
የማን ልጅ ተጨፈጨፈ?
የማን ልጅ ከትምህርት ውጪ ሆነ?
የማን ልጅ ጫካ ለጫካ ማሰነ?
እዮዋት እሙኃይን። ፍርድ ለራስ ነውና። #ህሊናችሁን ጠይቁ ስንት ተስፋ እንደምትቀዱ? ስንት ተስፋ እንደምትገድሉ። ተው ያልኩት ለዚህ ነበር። የገጠሩን ኑሮ አታውቁትም እና።
የአርበኛ ዘመነ ካሴ እናት ኑሮ። መንግሥት እስከ ሠራዊቱ የዘመተበት ማህፀን። አልባሳቷን የእሙኃይን እዩት። ጎጇዋን እዩት። መኖሯን እዩት።
ጣልቃ ሲገባ ለእነኝህ ዕድሜ ልካቸውን እንዲህ ክልትምትም ያሉ የአማራ ልጆች እናትን ማሰብ ይገባ ነበር። ለስቃይ ጭማሬ ሽሚያ እና የፎቶ ኤግዚቢሽን ፋክክር?
እሱም ቢሆን ቁራሽ እንጀራ ለነፍሱ ሳያጣ እንዲህ ከኤርትራ በርሃ እስከ አሁን ክልትምትም አለ። ውስጤ ተቀዷል። ጭካኔ አይጠግቤው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ፍርድ እና ዳኝነት ፈጣሪ ይሰጣቸው ዘንድም አምላኬን እማፀነዋለህ።
ሙሉ አገር ተሰጥቶህ መምራት ተስኖህ በሲሶ ግዛት ላይ ይህን ያህል ያዙኝ ልቀቁኝ። ጀግንነቱ ይህቺን ደካማ መነኩሲት እናት ማሰቃዬት፣ ማሳቀቅ፣ እና በሃዘን ብዛት ሥር መንቀል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/05/2022
የአማራ እናቶች ሐሴት ቀኑ መቼ ይሆን?



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።