ልጥፎች

ከኖቬምበር 14, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኤርትራ እና የአማራ መሬት ጥሪኝ የምሥራች ብስራታዊ ዜና።

ምስል
እርጥቡ የአማራ መሬት ጉብኝት ስኬትን ለኤርትራ እንሆ አበሰረ።  ፍቅርንም በቅንነት  አስከበረ! „ምህረት እና እውነት ከአንተ አይራቁ  በአንገትህም እሰራቸው።“ መጽሐፈ ምሳሌ ፫ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ© ሥላሴ  114.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ  ባላፈው ሰንበት ላይ የኤርትራው መሪ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና አቻቸው የሱማሌው ፕሬዚዳት ሙሐመድ አብደላሂ በጎንደር እና በባህረዳር ይፋዊ ጉብኝት ማደረጋቸው ይታዋቃል። በዚህ ውስጥ ቅንነት እና ድንግልና ስለነበረ እንሆ የኤርትራ ምኞት ብቻ ሳይሆን የቀጠናውን ሰለምና አንድነት ሊያጠናክር የሚችለው በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገው ጥረት እና ልፋት ለውጤት ደርሶ ዛሬ ኤርትራ በተባበሩት ምንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት  ተጥሏበት የነበረው የኢከኖሚ ማዕቅብ የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ደምጽ ማጽደቁ ተደመጠ። እትጌ ኤርትራ እና መንግሥቷ እንዲሁም ህዝቧ እንኳን ደስ አላቸው፤ ጉልህ ሚና የተጫወቱት ጠ/ ሚ ር አብይ አህመድ እንኳን ደስ አላቸው። የሱማሌው ፕሬዚዳንትም በጎ መንፈስ በዚህ ውስጥ ስላለ እንኳን ደስ አለው። ደስታው የአፍሪካ ሰላም ነውና። ኢትዮጵያዊነት መንፈሱን ሲያቀርቡት ረቂቅ ጠጋኝ መንፈስ አለው።  ጥረቱ የተሳካው ቅንነት እንጂ የትርፍና የኪሳራ የብልጠት ስሌት ስላልነበረው ብቻ ነው። ይህን ማዕቀብ ለማስነሳት ብዙ ተሞክሮ „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር ሆናና“ ዛሬ የምሥራቹ ተደመጠ፤ እርጥብ እግር እና እርጥብ መሬት እንዲህ ሸክምን ያቃልላል። ለአብይ ካቢኔ ሉላዊ የዲፕሎማሲያው ዕውቅና እና ክብርም ደረጃውን በዚህ ውስጥ ማዬት ይቻላል። ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ ...

ሽብልል በሽብልል ቃለ ምልልሱ ከፖለቲካ ሳይንቲስቱ ጋር - በዋልታ።

ምስል
ሽብልል በሽብልል። „ስለ ራዕይ ሸለቆ የተደገረ ሸክም። እናንተ ሁላችሁ ምን ሆናችኋዋል?“ ትንቢተ ኢሳያስ ፳፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  14.11.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።                                                          ·     መነሻ። ሽብልል የሚለው ቃል አንዲት ሴት የገብስ እንጀራ ካሰኛት በወፍራሙ ትለውሰዋለች፤ ለረጅም ጊዜም ይቆይላታል። አገልግሎቱን ውጤቱን ሳያሳውቅ። እዬገነፈለም አያጨናናቃትም ቀኑ ሲደርስ አቅጥና ከሙገጎ ጋር ታገናኘው እና እንጀራ ይሆናል፤ እሰከዚህ ድርስ ግን ሽብልሉ የዳቦ ይሁን፤ የጠላ አብሽሎ ይሁን የእንጀራ ይሁን መለዬት አያቻልም። ያው ሽብልል ነው። እንደተሸፈነ ተሸብልሎ ይሰነባብታል። ቀኑ ሲደርስ ግን ተቀጥኖ ሲጋጋር የገብስ እንጀራ ይሆናል።  ሌላው ግምል የሚባል ደግሞ አለ። ግምል ደግሞ የማሽላ ነው። የደበር፤ የወድ አራባ፤ የወዳከር የቡሌ ወይንም የባህር ማሽላ ሊሆን ይችላል። ገምላ አስንብታ ልታጋግር ስታስብ ሴት ባለሙያ አቅጥና ትጋግራዋለች ማለት ነው። የጤፍ የቦካ በሌላ ዕቃ ከኖራትም አብራ አዋህዳ ትጋገረዋለች። የገብስ እና የማሽላ ልወሱ ለብቻ ነው የሚዘጋጀው። እንዲያውም በሰፊ ገበታ ነው የሚቀመጠው። የ ጤፉ ግን በማንኛውም ቡሆዕቃ ይሰናዳል፤ በቅልም በ እንስራም ትልቅ ቤተሰብ ካለም፤ ድግስም ከኖረ በጉርድ በርሚልም ሊሆን ይችላል። የማሽላው እንጀራ ፍርክ ፍር...