ልጥፎች

ከማርች 25, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ታቅዶ ስለመከወኑ በማስተዋል ይመርመር፤

ምስል
 እንኳን በሰላም መጡልኝ!  ታ ቅዶ ስ ለመከወኑ  በማስ ተ ዋል  ይ መርመር ። „በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች፤ እንደዚሁ ክፉ ነገርም ለኃጢያተኞች ተፈጠረች“ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 25.03.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ·         ህልሜን የዛሬውን ላጋራችሁ … የት የት እንደሚወስደኝ መቼም የሚገርም ነው። አልኳችሁ የእኔዎቹ ህልም ማዬት እንጂ መፍታት አላውቅም። ዛሬ የሚገርም ህልም አዬሁኝ።  አብዝቼ ስለ አላዛሯ ኢትዮጵያ ስለመጨነቄ ሊሆንም ይችላል። ፈውስ የት ሊገኝ እንደሚችል  ይኸው እንደ ለመደበኝ እማስናለሁኝ በመንፈስ … ግን ተረጋግቼ ነው። እንደ ድሮው መባከን፤ መብከንንከን የለም።  ·          እንዲህ ም ሆነ .. አንድ ጨለማ ውስጥ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ጭንቅላት ብቻ ይታዬኛል። በሌላ አቅጣጫ አንድ የሰው ሙሉ ጥላው ብቻ ይታዬኛል። የዛ ሰው ጥላ ወደ ውጭ ብርሃን ስላለ ከዛ ላይ አጥልቷል። ከዛ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ በእጅ ስልክ ባትሪ ከአንገታቸው ጀምሮ በዛ ብርሃን ቴራፒ ይደርግላቸዋል። በዚህ ውስጥ ጆሯቸውን ወደ አንድ ጎን ሲያጋድሉት የዛ የእጅ ስልክ መብራት ብርሃን በውስጡ እንዲገባላቸው ይደረጋል። የቀኙን ጆሯቸው ሲያበቃ የግራ ጆሯቸው ይቀጥል እና ያ የእጅ ስልክ ብርሃን በጆሯቸው ይንቆረቆራል። ሲንቆረቆር የጆሯቸውን አፍ ሁሉ በብርሃኑ እዬታዳሰስ ነው።   እንደዛ እዬተደረገ አንገታቸውም ተራው ከደረሰው ...