ታቅዶ ስለመከወኑ በማስተዋል ይመርመር፤

እንኳን በሰላም መጡልኝ!
ቅዶ ለመከወኑ
 በማስዋል 
መርመር
„በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች፤
እንደዚሁ ክፉ ነገርም ለኃጢያተኞች ተፈጠረች“
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ?

·        ህልሜን የዛሬውን ላጋራችሁ … የት የት እንደሚወስደኝ መቼም የሚገርም ነው።
አልኳችሁ የእኔዎቹ ህልም ማዬት እንጂ መፍታት አላውቅም። ዛሬ የሚገርም ህልም አዬሁኝ። 
አብዝቼ ስለ አላዛሯ ኢትዮጵያ ስለመጨነቄ ሊሆንም ይችላል። ፈውስ የት ሊገኝ እንደሚችል 
ይኸው እንደ ለመደበኝ እማስናለሁኝ በመንፈስ … ግን ተረጋግቼ ነው። እንደ ድሮው መባከን፤ መብከንንከን የለም። 

·        እንዲህም ሆነ ..

አንድ ጨለማ ውስጥ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ጭንቅላት ብቻ ይታዬኛል። በሌላ አቅጣጫ አንድ የሰው ሙሉ ጥላው ብቻ ይታዬኛል። የዛ ሰው ጥላ ወደ ውጭ ብርሃን ስላለ ከዛ ላይ አጥልቷል። ከዛ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ በእጅ ስልክ ባትሪ ከአንገታቸው ጀምሮ በዛ ብርሃን ቴራፒ ይደርግላቸዋል።

በዚህ ውስጥ ጆሯቸውን ወደ አንድ ጎን ሲያጋድሉት የዛ የእጅ ስልክ መብራት ብርሃን በውስጡ እንዲገባላቸው ይደረጋል። የቀኙን ጆሯቸው ሲያበቃ የግራ ጆሯቸው ይቀጥል እና ያ የእጅ ስልክ ብርሃን በጆሯቸው ይንቆረቆራል። ሲንቆረቆር የጆሯቸውን አፍ ሁሉ በብርሃኑ እዬታዳሰስ ነው። 

እንደዛ እዬተደረገ አንገታቸውም ተራው ከደረሰው በኋዋላ አፋቸውን ከፍተው ያ ብርሃን በአፋቸውም እንዲገባ ተደረገ። ያም ብቻ አይደለም በሁለቱ የአፍንጫቸው ቀዳዳም እንዲሁ መሰሉ ተፈጸመ። ከዛ የገረምኝ ደግሞ እኛ ሴቶች ጸጉራችን ቅባት ለመቀባት ስንፈልግ  እዬተከፈለ በተከፈለው ልክ ቅባት ይቀባል። 

ልክ እንደዛ በራነታቸው ቀርቶ የጸጉር ቡቃያ ያለው ይመስለኛል። በራሱ ጊዜ ቡቃያው እራሱን እያከፈለ በተከፈለው ልክ ብርሃኑ እዬተላከ ሲደባብሰው አዬሁኝ። ወገባቸው አልታዬኝም፤ የሚታዬኝ ከአንገታቸው በላይ ያለው አካላቸው ብቻ ነው። በብርሃን ቴራፒ የሚአደርግላቸው የሰው ምስልም ጥላው ብቻ ነው እንጂ ሰውዬው አይታዬኝም .... ውዶቼ እሰኪ ፍቱት …

·        ጓደኛ ፍለጋ።

አንድ ዜና በዬሚዲያው አዳመጥኩኝ አዬሁኝ አነበብኩኝ። ግንቦት 7 በባህርዳር ስብሰባ እንደነበረው እና እንደተስተጓጎለበት። እኔ ይህ ታቅዶ የተከወነ ነው ብዬ ነው እማስበው። እምልበት ምክንያት ግንቦት 7 ከዚህ ቀደም እልል ኩልል እዬተባለለት ካባ እና ተክሊል እዬተሸለመ በባህርዳር፤ በጎንደር፤ በወሎ ህዝባዊ ስብሰባ በአዳራሽ እና በአደባባይ አድርጓል ካለ ችግር።

በሌላ በኩል በቅርቡም የተሰካ ስብሰባ ማርቆስ ላይ እንዳደረገ አዳምጫለሁኝ። እንዲያውም በሰጫኝ ስለሉ የአማራ አክቲቢስቶችም አንድ ደጎስ ያለ ጹሑፍ ጽፌ ነበር። ዜጋ በአገሩ ሊከለከል አይገባም ብዬ።

አሁን ይህ የሆነው እኔ አንደማስበው ጓደኛ ፍለጋ የቄሮን የሜንጫ ነገር የኦዴፓን ከታች ወርዶ የኮንዲሚኒዬም ቁብ ውስጥ መቀርቅር ለማመጣጠን ሆን ተብሎ ታቅዶ እንደተከወነ ነው የሚሰማኝ።  በአማራ ክልልም ይሄ ተፈጸመ ለማስባል። የ አማራ የጽናት ጉዞውም እያረደው ይመስለኛል አውራው ፓርቲ ኦዴፓ። ያው የጎንደር መፈናቀል ታቅዶ እንደተከወነው ማለት ነው። በሌላ በኩል ሰሞኑንም የጌዴኦ ህዝብ ሰቆቃ አልበቃ ብሎ የውጭ ዜጎችን የጨመረ የሰው ቃጠሎም ተከስቷል።

ስሊዘህ እኔ ይህ የትናንቱ ግርግር ከዛ አንጻር ነው እማዬው፤ በመጋቢት አንድም ባህርዳር ላይ የግንቦት 7 የሚዲያው የኢሳት ቡድን ነበር፤ በእልልታ በኩልልታ አሸብርቆም ቡድኑ በቀጣይ ቀናትም ጎንደር ላይም ነበር። ስለዚህ የግንቦት 7 መንፈስ እንዳሻው እንዲህ በሚዘናከትበት ብቸኛ ቦታ ይህ ነገር ይፈጠራል ተብሎ አይታሰብም። ተቃውሞ አይኖርም ማለቴ ግን አይደለም። ግንቦት 7 እና ታማኝነት ምን እና ምን ናቸው? ለግንቦት መድከም ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሁሉ ደርሶት አይቶታል... 

የሆነ ሆኖ ራሱ ግንቦት 7 ብሄራዊ ድርጅት ሆኖ አለኝ የሚለው ሰራዊት ደግሞ አማራ ክልል ወረታ እንዳለ ነው የሚደመጠው። ግንቦት 7 መቼም የአማራ ድርጅት አይደለም። እግረኛው ነው አማራ።
ብቻ ሆን ተብሎ እኛን ብቻ ወንጀለኛ አታድርጉን ቁስላችን እዩ ያሉት የጠ/ሚር አብይ አህመድ ቁስል ያለ መንፈስ አይዞህ ለማለት የተወሰደ እርምጃ ነው። „ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሕ“ እንደ ሆነው ማለት ነው።

ከዚህ ቀደም ሻሸመኔ ላይ ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል ያን እንዲያካክስ ተብሎ አማራ መሬት ላይ ለጥናት እና ለምርምር የሄዱ ወገኖች በድንጋይ ተወግረው እንዲገደሉ ተደርጓል። የመንጋ ህግ በሁሉም እንዲባል። አሁን የሆነው ይኸው ነው።

የዚህ ባላንባራሱ ደግሞ ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። ለዚህም ነው አምሳላቸውን የተኩለት ሚዲያ መግለጫ እንዲሰጥ የተደረገው። አንድ ሞገድ የሚባል መጽሐፍ ነበር አገር ቤት እያለሁ ያነበብኩት። በሁለት ሚሊዮን ዶላር ወንጀል እራሱ አቅዶ ያሰራና ወንጀሉ እንደተፈጸመ ቀድሞ ደግሞ እራሱ ሞገድ ጋዜጣ ያወጣል። በ5 ሚሊዮን ብር ይሸጥለታል። 3 ሚሊዮን ትርፍ ማለት ነው። 

ወንጀልን አቅዶ ማደራጃት፤ ያደራጁት ወንጀል ሲከወን ደግሞ መረጃው ቀድሞ ማውጣት። ልክ እንደ ሰኔ 16ቱ ታምረኛ አደጋ ማለት ነው። ወዲያው ወንጀሉ ተፈጸመ „የተደራጀ፤ የተቀነባባረ፤ የቀን ጅቦች ያዘጋጁት በሚል የውሳኔ ሃሳብን መንፈስ ያቀፈ መግለጫ ተሰጠ።"  ምንም ጥናት እና ምርምር ሳይደረገበት። „የተደራጀ የተቀነባበረ ስለመሆኑ“ በዛች ቅጽበት ማወቅ አይቻልም ነበር። እኔ እንደማስበው። ይህን ለማለት ቀን ይፈልግ ነበር። 

ጠ/ሚር አብይ አህመድ አሜሪካ ሲገቡ ቆሞስ ስመኘው በቀል ተገደለም ሌላው ዜና ነበር። አሁንም ባህርዳር ላይ የሆነው እንዲህ ነው። ግንቦት 7 ካለፈው ወዘተረፈ ድክመቱ ተምሮ ለዚህ መሰል ግጭት ሰለባ ላለመሆን በማስተዋል ቢራመድ መልካም ነው። ለነገሩ አይሰማም። አሁን ደግሞ በአዲስ ስልት ለአማራ ማገዶነት ሳቢያ ከመሆን ቢቆጠብ መልካም ነው። ይህ ቀጣዩ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል ምልክት ስለሚሰጥ። ከአዲስ አባባው ጭፍጨፋ እና ካቴና መማር ይገባል። 

ደግሜ ደጋሜ እኔ እመለው የዶር አንባቸው መኮነን ካቢኔ የሰከነ ተግባር መከወን ካስፈለገው  የኦዴፓውን የመንፈስ የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል፤ የጡት አባትን ከምክር ቤት አባልነት ያሳግድ - አቶ ንጉሡ ጥላሁንን።

ይህን ካደረገ ብቻ ነው በተረጋጋ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ሚስጢሩ ተጠብቆ ተግባሩን መከወን የሚችለው። ችካሉን ይንቀል ብአዴን። ይህ ደግሞ ከማንም ደጅ የሚያስጠናው አይደለም። ኦዴፓ መንፈስ አዛዥ ናዛዥነቱን ግባዕቱ ለመፈጸም እሳቸውን በአምሳያ ያስቀመጡትን አንደበተ ጨምሮ ይንቀል ልብ ከኖረው ብአዴን።

ሌላው ግን ግንቦት 7 ብሄራዊ ፓርቲ እንጂ የዞግ ስላልሆነ ቢያንስ ሌሎችንም ከተሞች ይሞካክር። ምን የተደገመበት ይመሰል ያን ብቻ ያስመለከተዋል። አዲስ አባባ እኮ ከአፍንጫው ላይ ያለ ከተማ ነው። ይልቅ አሁን ከ እስክንድር ንቅናቄ በሆዋላ ጠ/ሚር ቢሮ የባልራስን ጉዳይ ለተለጣፊው ትእግስቱ አውሉ መሸለሙን ዜና አዳምጫለሁኝ። ስለመፈጠሩም የከሰመ ድርሽ አልባ ድርጅት ለዚህ ለስንጠቃ ተግባር ተልዕኮ ተስጥቶታል። 

የሆነ ሆኖ ግንቦት 7 ደብረዘይት፤ ናዝሬት፤ ጅማ፤ አሰላ፤ አርባምንጭ፤ መቱ፤ ጅጅጋ፤ ድሬድዋ፤ ሻሸመኔ፤ ውልቅጤ፤ አዋሳ፤ ቃሊቲ፤ አቃቂ፤ ቡራዩ እነዚህን ከተሞች ቢያንስ ይጎብኛቸው። ግንቦት 7 የአማራ ድርጅት አይደለምና። በሌላ በኩል ለ አማራ ህስብም ጫናውንም ይቀንሳል፤ ማመጣጠንም ይኖራል። ፋታ አጣ እኮ ያ ህዝብ። እረፍት ተነሳ። በግራ በቀኝ ተወጥሮ የተያዘ ህዝብ ነው። ትንሽ እንደ ሰው ማሰብ ይጠይቃል።  

አሁን ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መንፈሱ በሚዲያውም በድርጅቱም እዛው ክልል መወጣት አልቻለም። በተከታታይ ማርቆስ ባህርዳር ጎንደር ኢሳትም ግንቦት 7 ነበሩ እዛው ክልል ነበሩ። የጎንደር ህብረትም፤ ሰማያዊ ፓርቲም ሌሎቹም አክቲቢስቶች … እዛው ክልል ናቸው … ህብራዊ ጥረት ማደረጉ  መልካም ሊሆን የሚችለው በሁሉም የ አገሪቱ ክፍሎች ማመጣጠን ሲቻል ነው።  ለኢትዮጵያዊነትም የሚበጀው እንደዛ የተመጣጠነ አትኩሮት እና የተመጣጠነ ሁኔታ ሲፈጠር ነው። 

በሌላ በኩል ፈሪነት ለድል አያበቃም። ሃሳብ ያለው ጠመንጃን መከታ ሊያደርግ አይችልም። ሃሳብ የሌለው ብቻ ነው ጠበንጃን ጉልበቴ፤ መመኪዬ የሚለው። ግንቦት 7 አማራን ካልወከለ፤ አማራን እወክለላለሁ የሚለው ደግሞ ሞግቶ በሃሳብ ይርታው። ሃይል ሳይሆን መንፈስን የሚገዛ አቅም ነው መንፈስን የሚገዛው።

ግንቦት 7 አማራን አይወክልም ከሆነ ትግሎ ሰላማዊ በሆነ መልኩ መሰለፍ ይቻላል፤ ካለ ጠበንጃ፤ ካለ ጡንቻ፤ ካለ ጉልበት። ግንቦት 7 ለሠራዊቱ የተገባውን እንክብካቤም ካላደረገ መሳሪያን አውልቆ በትህትና፤ በአክብሮት ጥያቄን ማቅረብ ይቻላል። በሰላም የሚገኘው ትርፍ በሃይል ከሚገኘው ትርፍ የበለጠ ዕዳ የለሽ ነው። ትወፊትንም መጣስ የተገባ አይደለም። ሰው ማከበር መለያችን ነው። እንግዳ ክብረታችን ነው። ይህን መተላላፍ አይገባም። 
 
በሌላ በኩል ሁልጊዜ የስሞታ ፖለቲካም ለአማራ ህዝብ የሚመጥን አይደለም። አቅሙን እኮ እዬታዬ ነው። ስንት ድርጅት፤ ስንት ግለሰብ፤ ስንት ሚዲያ ቆጠራው እንዲቀር ጻፈ፤ ተናገረ … እኔም ጠንከር ያለ ምርጫንም ቆጠራንም በሚመለከት ጽፌያለሁኝ። ነገር ግን የአማራ ወጣቶች ማስጠንቀቄያ በሰጡ ማግስት ግን የሆነውን አይተናል። ስለምን? አማራ ቅን እና ደግ ህዝብ ስለሆነ መንፈስ ቅዱስ ሃይሉን ስለሚሰጠው ብቻ ነው።

ውጪ አገር ገናና ድርጅት ነበር ግንቦት 7። በማይሆን ነገር አቲካራ ገጠመ። አገለለ፤ አወገዘ፤ ተቀናቀነ። እልፎ ተርፎ በሞፈር ዘመት መንፈሳችን አሳሰረ። ግን አቅሙ፤ ገናናቱ አልበረከተም። ለምስል እራፊ መንፈስ ያገኘው ያው የቅን ህዝብ ነው አክብሮ የተቀበለው።

 የፊቱ ላይበቃ ያ ሁሉ የአማራ ህዝብ ልጅ የተቀቀለበት በግንቦት 7 መፈጠር ነው። አሁን ደግሞ ያ ሁሉ አልፎ ጨዋነት በጎደለው ጉዳይ የአማራ ሥም መነሳቱ በግንቦት 7 ምክንያት ያማል። መዳህኒተ ዓለም መፍትሄ ይስጠው። አሜን!

አንዲት አራስ አንድ ወር በራሴ ወጪ አርሼ አንድ ቀን ብቀር ታኮርፈኛለች፤ በ6 ወር በወለደች መጥታ የምትጠይቃት ግን ከእኔ ይልቅ ትከበራለች። ቀደም ባለው ጊዜ አራሽ የሌላቸው በስደተኛ ካንፕ ውስጥ የሚገኙ እህቶቼን በምችለው አቅም አርስ ነበር። እና የምነግራችሁ የሆነውን ነው። የአማራ እጣ ፈንታም ይኽው ነው። የቅርብ „መዋዕት የቹቻ መንከሪያ“ ይሆናል እንደሚባለው ነው የሆነው አማራ።
ሥሙ መኖሩ እራሱ የግንቦት7 ተጀምሮ እስከሚጨረስ በአማራ መንፈስ መስዋዕትነት ውስጥ ነው።

 ቅንጣት ትንፋሽ ከትግራይ ግንቦት 7 አያገኝም። ስለሆነም በክፉም በደግሞ በግንቦት 7 ሳቢያ ትግራይ አይነሳም። ክውን ስላል። ስለማይለካለክ። ቢለካለክ እንኳን ውድ ነው። ተከብሮ ነግሶ ነው። አሁን አታዩንም ጠ/ሚር አብይ አህመድ በዬትኛውም ስብሰባ ትግራይን ሳያነሱ አይቀሩም። እራሳቸውን ስላስከበሩ።  

የሆነ ሆኖ ለግንቦት 7 እኔ የምነግረው ለወደፊቱም ፉከራ አያስፈልግም። ሃይልም አይበጅም። „የሚመካ ቢኖር በእግዚአብሄር ይመካ ነው።“ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ አቅም ካለው እስኪ በራሱ ክልል ቦታ ይክፈት እና ግንቦትን 7 ያሳትፍ። ጉባኤ ላይ ላመሳተፍ እንኳን አልተቻለም። እንኳንስ ለፖለቲካ ተሳትፎ መድረክ ለመፍጠር። ደቡብ ክልል ላይም ግንቦት 7 ለጉባኤው እንዲሳተፍ አልተደረገም።  በኢህአዴግ ጉባኤ ብቻ ነው እንዲሳተፍ የተደረገው። 

የዚህ ሚስጢሩን ጠለቅ ብሎ ማስብ ይገባል። አዋሳ ላይ፤ ትግራይ ላይ፤ ጅጅጋ ላይ፤ አፋር ላይ፤ አሶሳ ላይ፤ ገናቤላ ላይ እስኪ በጠባቂ ግንቦት 7 መንፈሱን የሚጋሩትን ቢሮ ከፍቶ እንዲያደራጅ ያስደርግ። 

ግንቦት 7 ከመንግሥት ጋር ተነጋግሮ መድረክ የሚያስከፍት ከሆነ ቢያንስ በመላ ኢትዮጵያ ከተሞች የሚሰራበት ሁኔታ እንዲመቻችልት ይታገል። የፊቱ ላይበቃ አሁንም አማራ መሬትን የጦር አውድማ ለማድረግ ከማሰብ መቆጠብም ይገባል። 

የአብይ ካቤኔ ይህን የሚፈልገበት የራሱ ምክንያት አለው። ይህን በማስተዋል ሆኖ መመርምር ያስፈልጋል። የአብይ ካቢኔ ሥራዬ ብሎ የያዘው አጀንዳ አለው። ለዛ አጀንዳ ደግሞ ውጋት እንዳይሆነው ብአዴንን ሰቅዞ መያዝ ይፈልጋል። ስለዚህ በዚህም በዚያም በጫና እንዲዋከብ ያደርገዋል።

·        ተጨማሪ ገፊ ምክንያት።

ሌላው ከዚህ ጋር የሚታዬው በሰሞናቱ የነበሩት ዜናዎችም ከዚህ ዕድምታ ጋር ይያዛሉ። የአቶ ዘመነ ካሴ መልዕክት ከአቶ ነአምን ዘለቀ ከግንቦት 7 መለዬት አስመልክቶ የሰጠው አስተያየት ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው፤ የጋዜጠኛ አበበ ገላው ስለ አቶ ነአምን ዘለቀ የሰጠው ምስክርነት ሌላው ጉልበታም ጫና ፈጣሪ ነው፤ የግንቦት 7 የጀርባ አጥንት የሆኑት የአቶ ነአምን ከግንቦት 7 አባልነት እና አካልነት እራሳቸውን በፈቀዳቸው ማግለል እና ለሠራዊቱ ያላቸውን ተቆርቋሪነት ለዚህ ሁሉ ገፊ ምክንያቶች ናቸው።
ቀደም ብዬ አንደ ገለጽኩት የአቶ ነ አምን ዘለቅ መንፈስ ጎጃም ላይ አለ። 

እንደ አንድ የጎጆ ቤት እሳር መመዝ አይታይ ያልኩት ለዚህ ነው። በቀድሞ ሠራዊትም ውስጥ ይኖራል። ምክንያቱም ወላጅ አባታቸው የወጣላቸው ታታሪ ሥመ ጥር ጀግና ነበሩና። "በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ቁጥር" ካልሆነ በስተቀር ቤተሰብም ቅርስ ውርስ እና ትውፊት ነው ለትውልድ። ይህም ተጽዕኖ አለው። እኔ እራሱ በግንቦት 7 ባላው ግድፈት በተደራቢነት ሲጨመሩ ዝም የምለው የወላጅ አባታቸውን መንፈስ በተለዬ ሁኔታ ስለማከብር ገፋ አድርጌ አልሞግታቸውም። እታቀባለሁኝ! 

አንድ አሉታዊ ውሳኔ ራሱን ችሎ አይቆምም። ብዙ ነገሮች ነው የሚነቃነቁት። አንድ በሁለገብ መልኩ ተቀባይነት እና ተደማጭነት የነበራቸው ከፍተኛ አማራር አካል ከሃላፊነትም፤ ከአባልነትም ራሰቸውን ሲያገሉ ይህን የሚያዳምጥ መነፍስ ሁሉ ቀልቡን ይሸልም እና ለምን የሚለውን ይመራመርበታል። መንፈስንም ልብንም ለማሸፈት አቅም ይኖረዋል።
  
በእነዚህ መሰረታዊ ምክንያቶች ያ ግርግር ተፈጥሯል ብዬ አስባለሁኝ። ቀጣዩም ቢሆን በሃይል የተደገፈ ከሆነ፤ በጫና ከሆነ ውጤቱ አያምርም። ግንቦት 7 ከዚህ ውጭ አገር ባለሥልጣን በነበረበት ጊዜ በነፍስ ወከፍ ሞክሮት አልተቻለውም። እልህ ሳይሆን ብልህነት ነው ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት ነፍሱን የሚያሰነብተው።

ለዛውም ግንቦት 7 መስሎት ነው እንጂ በተደጋጋሚ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ንግግር እንደሚያስገነዝብን ሥልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደለም ግንባራቸውም፤ ድርጃታቸውም፤ እሳቸውም። እና ቀጣዩ ምርጫ በርግጫነቱ ቀጣይ ነው።

እና ብዙም ተስፋ አያደርገው ግንቦት 7 የጠ/ሚር አብይን አህመድን የአሸጋጋሪነት የትናጋ መርህ። … አብንም ቀጣዩ የጠ/ሚር አብይ ዒላማ ነው። ይህን ጠብቃችሁ ያዩዘት። ለዚህ ነው በሰተጀርባ ኦዴፓ ያሰለፋቸው ሠረዊቶቹ የሚያብጠለትሉት አብን። 

መንግሥትም አሁን አዲስ የፈጠሯቸው ተለጣፊ ሚዲያዎች ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመን አክሎ ውስጥ ውስጡን እዬሠሩበት ነው። እሳቸውም በአደባባይ የቃልኪዳን ስምምነቱ ጊዜ በቀጥታ በድፍረት ወርፈወታል አብንም፤ ያከበራቸውን፤ ያነገሳቸውን፤ ተግቶ የሚጸልይላቸውን ህዝብ የአማራ ህዝብንም።

አብን መንግሥት እንሆናለን ማለቱን በአሽሙር፤ በማጣጣል ታገኛታልህ ዓይነት ብለውታል። እራሱ ከተፎካካሪ ፓርቲ አስፈላጋነት መርህ ጋር ሁሉ ተጣልተዋል። አንድ የፖለቲካ ድርጅት የሚያደራጀው ለሥልጣን ስለመሆኑ እራሱ የሚቀበሉት አይደለም። 

ለዚህ ነው አካላቸውን፤ ራሱን የሸለማቸውን፤ ታሪኩን ገጸበረከት ያደረገላቸውን ከማዕከላዊ መንግሥት ብአዴን አሽቀንጥረው በክልሉ እንዲወሰን ያደረጉት። ልብ የገጠሙላቸውን ደግሞ ጠቅልለው ብዙውን ሃላፊነት የሰጡ አስመስለው በበላይነት ከርችመውታል። የዋዛ አይደሉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ።  

ሌላውን አንተ ደግሞ ለምንግሥትን ልትባቃ ይህን እረም ያን እረም ብለዋል ሰው ዘቅዝቆ በሚሰቀል፤ ህዝብ በርሃብ እንዲያልቅ በወሰነ፤ አራስን በግሪደር የሚያርስ ድርጅት አመራር ተሸከመው … እሳቸውም ጠ/ሚር አብይ አህመድ የኦህዴድ ሊቀመንበር መሆናቸውን እራሱ ረስተውታል።

እነሱ መሆን ከቻሉ ሌላው መሆን እማይችልበት ምንም ነገር የለም። እሳቸውም ሰው ሌላውም ሰው። ሥልጣን መረካከብን በጣም ነበር ያጣጣሉት። መሪነቱን አትሰቡት ዓይነት ነው … እንደ ተለመደው አቅም ያለው መንፈስ ሲወጣ ምን ያህል አደባባይ ላይ በንዴት ጦፈው ሥም ጠርተው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እንደወረፉ እና እንዳስጠነቀቁ ደግሞ ከሰሞናቱ ተመልከተናል። አሁን የ አቶ ትእግስቱን አወሉን አንድነት በግንባር ቀደምትነት አሰለፈዋል። ስለዚህ ይህ ምርጫ የሚባለው ነገር የእንካ ስላንትያ የጊዜ ማማሻ ነው። እኔ ከቀደመው የሚሻል ነገር ይኖራል ብዬ አላስብም። 

እራሱ የእርቅ እና ይቅርታ፤ የማንነት እና የወሰን ኮሚሽን ያሉት ጊዜ ለመግዣ እና ለመተንፈሻ ብቻ ነው እንጂ የሚፈይደው ነገር አይኖርም … የማዘናጊ የፖለቲካ ተፎካካሪዎች እንቀልፍ ማስተኛ ቫልዬም ነው …  

እና ግንቦት 7 አይታክት። ጠ/ሚር አብይ አህመድ በዬንግግራቸው "እኔ በነገ ውስጥ ነኝ" ነው የሚሉት። እቅዳቸውን በቀጣይ ዓመታትም ይገልጻሉ በተከታታይ። እንሟሟታላን ብለው ደረታቸውን ነፍተው እዬተናገሩ ነው። እዬፎከሩም ነው። እያስፈራሩም ነው። 

በግንባሩ ሥም የኦነግን ፍላጎት ለመሳካት ነው ትልማቸው። ወጥ ፓርቲ የሚሉት ማዘያ ነው። አብሶ የአማራ ብሄርተኝነትን ለማረቅ ነው። የብአዴን መንገድን የአሁኑን ፈጽሞ አልወደዱለትም። እሳቸው የትግራይ ጉዳይ አይደለም የሚያስጨንቃቸው እንቅልፍ የሚነሳቸው የብአዴን ጉዳይ ነው። ጦርነት ቢጀምሩ ሁለቱ ክልሎች እራሱ ደስታውን አይችሉትም ...

ለዚህ ነበር እኔ የቆሞስ ስመኘውን ሞት ከተመለከትኩኝ በኋዋላ አገር አትግቡ ብዬ የነበረው ግንቦት 7። „እረጅም ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት“ እንዲሆን። ቢያንስ የአብይ መንግሥት የሚፈራው ቢኖር ይህን ያህል ማን አለብኝ ብሎ ኢትዮጵያን ርዕስ መዲና አልባ ለማድረግ አይተጋም ነበር። ዲሞግራፊ ለውጥ በከተሞች ፕሮጀክቱን እንዲህ በአደባባይ አና አይልም ነበር። 

ሌሎችም የ ኦሮሞ ድርጅቶች ይህን መሰል አሸባሪ ነፍስን ሰናጊ አስጨናቂ ማንፌሰቶ ባለወጡ ነበር። እነሱ ወደ አንድ ወጥ ፕሮጀክት እዬተሰባሰቡ ሌላውን እርስ በእርሱ ማፋጨት ጉዳያቸው ነው። በረባ በረባው አጀንዳ ጊዜ ከማባከን ዘላቂ የህልውና ተጋድሎ ለ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል። ቅንጥብጣቢ እና ጭፍጫፊ ተኮር ትግል ከማድረግ፤ አቅምንም በሆነ ባልሆነ ከማባከን። 

·        ሞክራሲና ሶሻሊዝም።

ሌላው ዴሞክራሲ በሚመለከት ግንቦት 7 „የዘራውን አጨደ“ የሚልም አዳምጫለሁኝ። የዴሞክራሲ ችግር የግንቦት 7 ብቻ አይደለም። የሶሻሊዝም ርዕዮት ችግር ነው። አሁን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስለ ዴሞክራሲ ሲናገሩ ይደመጣሉ። ከንቲባ ከሌላ ከተማ አምጥተው ያውም ለርዕሰ መዲና ሹመው። ታከለ ህግ አስወጥተው። አሁን እራሱ የካቢኔው አባላት በሳቸው መንፈስ ብቻ ነው የሚሾሩት ከጥቂቶች በስተቀር።

ሶሻሊዝም በተፈጥሮው ወቀሳ ባህሉ አይደለም። የወቀሰ አናርኪዝም ነው የሚባለው። የልዩነት ሃሳብ አለማስተናገድ ብቻ ሳይሆን የተሻለ ሰው ማዬት የሶሻሊዝም ራስ መርዘኑ ነው። ያን የተሻለ መንፈስ ያፈልሰዋል። በሶሻሊዝም በበታችንት ለመኖር መፍቀድ ብቻ ነው እንደ መርህ የሚወሰደው።

የኢትዮጵያው ሶሻሊዝም ደግሞ አማራ የሚባል ጨቋኝ አለ ነው ርዕዮቱ የተመሠረተበት አብይ ጉዳይ።
ስለዚህ ከዚህ የሚያመልጥ የለም። ሊኖርም አይችልም። ራሱ የአማርኛ ቋንቋ መፋፋቱ እረፈት አይሰጣቸውም። አማርኛ ቋንቋ ሥሙ ፊደል ቢባል ይሻላቸዋል አማርኛ ከሚባል። ግዕዝም ከ አማራ ጋር እኩል ለ እኩል ነው የሚታዬው። ኦርቶዶክስ ተዋህዶም እንዲሁ ...

ለዚህም ነው ግንቦት 7 የምክር ቤት አባል ለመሆን ሁለተኛ ቋንቋዋ ማወቅ ደንባቸው ይጠይቅ የነበረው። አንድ ሰው የምክር ቤት አባል ሳይሆን ከፍተኛ አመራር አካል መሆን አይችልም። አንድ ቋንቋ ብቻ ተናጋሪ ከሆነ ያው ግርድና ብቻ ይሆናል እጣ ፈንታውም። ራሱ የአማራው ሊሂቅ ራሱን ተቃርኖ ራሱን ሲያፈርስ እኮ ነው 50 ዓመት ሙሉ የኖረው። 

አሁንም አሉ እንዶድ አልጎበኛቸው። በዬዘመኑ በ አዲስ ካሊም ብቅ የሚሉ። ያልታደሉ። ባልዳነው ወደፊትም በማይደንው መንፈስ ውስጥ ይድናል ብሎ ከመማሰን የራስን አማራጭ ወስዶ ራስን ማዳን ብቸኛው መፍትሄ ነው። ይህ ሲባል ዴሞክራሲን በራስ ውስጥ መጀመር ማለት ነው። ዴሞክራሲ ከሌላው አለመኖሩ ሳይሆን ቁም ነገሩ ትንሽ ምናምን ድርጅት ነገር የጀመረ ሁሉ ዴሞክራሲን አያሞክራትም። ስለዚህ የሁሉ ችግር ነው። 

አዲስ መስዋዕትነት ለመክፍል መዘጋጀትን በጽኑ ይጠይቃል። ስለዚህ አማራ ጠልነት፤ አቅም ያለው ሲወጣ መፍራት እና ለማጥፍት መትጋት ከሚከተሉት ርዕዩት ተፈጥሮ የመጣ ነው። ጎንደሮች እንደሚሉት „ተፈጥሮን ተመክሮ አያድነውም“ ይባላል … በፈለገ መስፈርት በሶሻሊዝም የተቃኘ መንገድ ዲሞክራሲ መርዙ ነው። በስልጣኑ፤ በሥሙ ንግስና ከመጣ የሚተርፍ አይኖርም። „ከራስ በላይ ንፋስ“ እንዲሉ … ኢጎ መካብ መደርደር መለያውም ነው የሁሉም። እከሌ ተከሌ የለበትም።
·        ማራነት መፍራትም እንዲሁ።

ገና ከውጥኑ ነበር ያሳሰባቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የአማራነት መንፈስ። እኔም ሞግቻቸዋለሁኝ። አብይ ሆይ! በሚለው ማመልከቻዬ። ብዙም ሰርተውበታል በዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ በፕ/ አበባው አያሌው፤ በፈላስማው ዶር ዳኛቸው አማካኝነት … ግንቦት 7 ከዛ ብቻ እንዲያተኩር የሚፈልጉበት መሰረታዊ ምክንያት ለዛ ነው። አጋር እንዳገኙ ነው የሚቆጥሩት። ይህ ለሳቸው ሽልማት ነው። 

ለዚህም ነው ሁሉም ህብረ ብሄር ፓርቲ ነኝ የሚባለው ሁሉ ከአማራ ክልል ሌላ ቦታ ምርጫ እንዳይኖረው የሚደረገው። ግንቦት 7 ሆነ ኢህአፓ ከጉራጌ መሬት ይልቅ አማራ ክልል ይቀናዋል። እንዲሰዋ የሚፈለገው ይኸው ማህበረሰብ ነው። ቅራኔ ውስጥ እንደጨመር የሚፈገውም ይኸው ማህበረሰብ ነው። ለምን „ልብ ያለው ሸብ“

ስለ ሰብዕዊነት ግድ የሚለው ሰው ለምን ብሎ መጠዬቅ ይገባዋል። ይህ አማራነትም መሆንን አይጠይቅም። ሌላው የማይገሰሰው ታላቁ ሚስጢር ግን ኢትዮጵያዊነት ከመንፈሱ ያነገሰ ማህበረሰብ አማራ ስለሆነ ጭምር ነው።

በፈለገው መሰፈረት አማራነት ከኢትዮጵያውያዊነት በላይ ከፍ አድርጎ የሚያይ የአማራ ልጅ አይኖርም። ይህ ገናና መንፈስ ደግሞ አባቶቻችን እናቶቻችን የደከሙበትን ተገድሎ ከንቱ አለማደረጋችን፤ አደራ ጠባቂ መሆናችን ያመላክታል። የትኛውም ማህበረሰብ ጉዳት ጉዳታችን ነው። ዕንባውም ዕንባችን ነው። ይህን ጸጋ የሚጎናጸፍ መንፈስ ሰብዕዊ ተፈጥሯዊም ነው። ተመስገን!

ሌላው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊነት ሊሰበክ የሚፈልጉት አማራ ክልል ብቻ ነው። ኢትዮጵዮዊነትን ለአማራ ህዝብ ማሰተማር ደግሞ ወንዝ ወደ ላይ አሻቅቦ መፍሰስ የማለት ያህል ነው። አማራ በኢትዮጵያዊነቱ አይደራደርም። የ66ቱ ሊሂቃን ቀንዳቸው የሚቆመው  የአማራ ሊሂቃን ጎላ ብለው ሲወጡ ነው። ለዚህ ነው ሚዲያውም፤ ሊሂቃኑም በተባበረ ሁኔታ በደቦ አብን ላይ የሰፈሩት።

ሰሞኑንን የጉራጌም የጋሞም አዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች ተፈጥረዋል። እነሱን ነኪ የለም። ወራፊም የለም። ጫናም አካባቢያቸው ላይ የለባቸውም። ሰላማቸውም አይታወከም። ሊሂቅ ሆነው ጎልተው እንዲወጡም ድጎማ አለበት። ሲወጡም ምስጋናውም እልልታውም ልቅናውም ያኑ ያህል ነው። አማራ ሲሆን ግን በግራ ቀኝ ጦር ይታዘዝበታል። ይዘመትበታል።
  
አማራ አገልጋይ እንጂ በፖለቲካ ተሳትፎ ድርሻ እንዲኖረው አይፈለግም። ለዚህ ነው ሰሞኑን ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደነገሩን ፕ/ ብርሃኑ ነጋን፤ ፕ/ መራራ ጉዲናን እና ገዳይ ዶር አረጋይ በርሄ ጋር በራቸውን ዘግተው እየመከሩ ስለመሆናቸው ከሰሞናቱ ሚስጢሩን ያወጡት። ያው ሚስጢሩ አንድ እና አንድ ነው።

አንድም ቀን ከውጭ ከመጡ የአማራ ሊሂቅ ከሆኑ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጉዳይ ኖሯቸው አያውቅም። ተስቷቸውም ሥማቸውን አያነሱትም። የሚገረመው እንዲህ አርቀው እያዩን ኢትዮጵያ ስላሉ ብቻ እኛ ከጎናቸው ተለሰልፈን ሞገተን፤ ተፈለምን።

አሁን ጥላቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር፤ ቂማቸው ከእሷ ከእምዬ ጋር ሲሆን ደግሞ ታግሰን፤ ታግሰን፤ ታግሰን አንድ ቀን ይፈነዳል … ሌላ ሃጢያት የለበትም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ። አውነተኛዋን ኢትዮጵያን በነፍሱ ስለሰነቀ ብቻ ነው።

እንግዲህ ከገዳይ አረጋይ በርሄ ልምድና ተመክሮ ቀን ጡጦ ሲጠቡ ውለው የሚያድሩ ጠ/ሚር በርቀት ድምጹን ሰማሁኝ ብለው ያን ያህል የተበሳጩ። በቀጣይ ምን ሊያስደርጉት እንደሚችሉ መገመት አይቸግርም። 

 … መንገዱ እዬተከፈተ ነው አንባገነንት ጀባ ሊላት አላዛሯን ኢትዮጵያን በአዲስ ኦነጋዊ ቀለም።… ገንጣዮች አትበሉንም ብለዋል? እስካሁን እንዳከበራናቸው ነው። መቼም ህወሃትን የመሰለ ዕድለኛ የለም … ቁጭ አድርጎ ያሳዬዋል ከእሱ ተሽሎ መገኘት ተስኖት ይህ ሁሉ ሊሂቅ። ከዶር አረጋ በርሄ አሁንም ስለ አማራ ምክር ይጠየቃል … መደበኛ ሥራው የጠ/ሚር ቢሮ ይኸው ነው …

አሁን ላይ አንድነትን ሳስብ ዶር ነጋሶን ተሸክሞ ምን ሊያመጣ እንዳሰበ፤ መደረክን ሳስብ አቶ በቀለ ገርባን ተሸክሞ ምን እና ምን ከ አረና ጋር ሊሆን እንደነበረ፤ ግንቦት 7 ሳስብ አቶ አበባ ቦጋለን ይዞ፤ አሁንም ግንቦት 7 አገራዊ ንቅናቄ ተሳክቶለት ቢሆን አቶ ሌንጮ ለታን፤ ዶር ዲማ ነግዖን አሽኮኮ አድርጎ … ብአዴንም ሳስበው ኦህዴድን ንዳኝ ግራኝ ምራኝ ብሎ የጀመረው ጉዞ ሲሰላ ክህደት በምን ያህል ሂሳብ ሲዝመነመን እንደኖረ ማስተዋል ይቻላል። ነገስ? እዮር ይወቀው …

አሁን ሁሉ ሰው ብስጭት ላይ ነው በዚህም በዚያም። ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ ግን ሁሉ ነገር ለመልካም እና ለበጎ ነገር ነው ብዬ አስባለሁኝ። ሁሉም እንዲማር እዮርም ማዕቱን ልኮ አሳይቷል።

ግንቦት 7 እንዲማር ብዙ ዕድል ስለሚሰጠው እሚቀጥል ከሆነ ካልተዋህደ ከፈረሰው ኢህአዴግ ጋር መውደቁና መነሳቱን ሊማርበት ይገባ ይመስለኛል። አብሶ ነገረ አማራ እና ሚስጢራቱን። መዳፈሩን መቀናቀኑን - ማግለሉን - መሳሪያ ማደረጉን - መግፋቱን - ማስመሰሉን ያለፈበትን ግድፈት ሁሉ ጠረጴዛ ላይ ዘርግቶ ዘርግፎ የምርምር ማዕከል ቢከፍትበት መልካም ነው። ከደከመው ደግሞ ማረፍ … ልፋቱ ለስኬት አላበቃውም። ጥያቄቸውን በትክክል ቢያቀርቡ መልካም ሆኖ ሳለ ያን መሰል አስከፊ ድርጊት መፈጸም ግን የተጋባ አልነበረም። ኢትዮጵያዊ የሚል ዜጋ ደግሞ ዜግነት በእርቦ እና በሲሶ አይደለም። 

ኢትዮጰያን መውደድ ባህሏን፤ ትውፊቷን፤ ወግና ልማዷን፤ እምነቷን መቀበል ነው። ሰው ለሰው የተፈጠረ ነው። ሰው ለሰው ጌጡ ነው። ጌጡን ጌጥ የሚያስደርግ ማስተዋል ፈጣሪያችን ይስጠን። አሜን! ሰው ለመሆን ያብቃን አሜን! 

ሰውን ማክበር በእግዚአብሄር ዘንድ ታላቅ በርከት ያሰጣል!
ዜግነት ዳር ድንበር የለውም!
ኢትዮጵያዊነት ወሰንአልቦሽ አውራ ማንነት ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ክብረቶቼ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
     



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።