ጦርነት ትርፉ ሁለመናን ማሳጣት ነው።
ዎህ! በተመጠነ ሁኔታ! „ኖን። መንገዳችን እንመርምርና እንፈትን። ወደ እግዚአብሄር እንመለስ።“ ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፵ ከሥርጉተ©ሥላሴ 27.08.2018 ትውልዳዊ ድርሻ እንደ ወርቅ የሚፈተንበት አዲስ የተጋድሎ ዘመን። ምርኩዝ። https://www.youtube.com/watch?v=CrjLmBMoEUc Ethiopia: አብዲ ኢሌ በአዲስ አበባ ከተደበቀበት በይፋ በቁጥጥር ስር ዋለ · የወ ግ ገባታ። ከድካም የሚያሳርፍ ፈቃደ እግዚአብሄር ነው። የቅድመ ዓለም የማዕከለ ዓለም የድህረ ዓለም ንጉሥ ክርስቶስ በቃችሁ ሲል እንዲህ ቸር ወሬ ያሰደምጣል። የኢትዮ ሱማሌ ነገር የተከደነ የጭንቅ አውዴ ነበር። ምክንያቱም ልጅ እያለሁ ነበር የኢትዮጵያ እና የታላቋ ሱማሌ ህልምን እውን ለማድረግ ሲያድ ባሬ ጦርነት የከፈተብን። ያን ጊዜ ቀበሌ ላይ የእናቴ ተሳትፎ እጅግ የሚገርም ነበር። ከት/ቤት ስመለስ ቁልፍ ለማምጣት ወደ ቀበሌ ስሄድ የኢትዮጵያ እናቶች ትጋት እጅግ ድንቅ ነበር። አቤት እንዴት ደስ ይል እንደነበር የነፃነት መሻት ዓውደ ዝማሜው ... በመደዳ ምጣድ ተጥዶ ገብስ ሲቆላ፤ በመደዳ ሙቀጫ ተዘጋጅቶ ሲሾኮሾክ፤ በመደዳ ገብስ ተዘርግፎ ሲበጠር፤ ሲለቀም ታምር ነበር። ሌሎችም መሰናዶዎች ጎን ለጎን ሲከወኑ ... እናቶቻችን እኛን ወደ ት/ ቤት ሸኝተው እቃቸውን ይዘው በጥዋቱ ልክ እንደ መደበኛ ሥራ ወደ ቀበሌ ይገሰግሱ ነበር። ወንዶችም ገብሱን ከመኪና በማውረድ፤ ለሥራ በሚያመች መልኩ ከባባድ እቃዎቸን በማቀራረብ፤ በማደራጀት፤ በ እንጨት ፈለጣ፤ ውሃ በማቅረብ... ወዘተ ይሳተፉ ...